Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች ጠየቁ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ማጠቃለያ በዓል ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች ጠይቀዋል።

በክልሉ አለምዓቀፍ የሙስና ቀን በተከበረበት የተገኙ ተማሪዎች ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

ተማሪ በእምነት አትርሳው፣ ተማሪ ኤርሚያስ ቆጭቶና ተማሪ መልካሙ በለጠ ከሸኮ፣ ከጉራፈርዳ እና ከሚዛን አማን ከተማ ካሉት ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች በሚቋቋሙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት በመሳተፍ በሙስና መከላከል ስራ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በትምህርት ገበታ በሰዓቱ መገኘት፣ ኩረጃን በመጠየፍና ከመምህራን ጋር አባታዊ ግንኙነት በመፍጠር በሙስና መከላከሉ ስራ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያ አቶ ገብረዮሐንስ አብርሃ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ክበባትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ባለሙያው፣ ተከታታይነት ያለውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በተማሪዎች ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል።

በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ ትብለጥ እንግሊዝ ሙስናን ለመከላከል ከትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ወጣቶች ለብዙ ነገሮች ተጋላጭ መሆናቸውን የገለጹት ባለሙያዋ፣ ሙስናን በመጠየፍና ተዋናይ ከመሆን ወጣቶች እንዲታቀቡ አመለካከትና አስተሳሰብ ላይ የተጀመረው ስራ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሐሰተኛ የደረሰኝ ህትመትን ለመከላከል ያለመ ስምምነት ተፈረመ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ገቢዎች ሚኒስቴር እና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በደረሠኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ከታክስ ደረሰኝ ህትመት ጋር በተያያዘ ልዩ መለያ ኮድ ተካቶ ማተም፣ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ የሐሰተኛ ደረሰኝ ህትመት በግብር አሰባበሰቡ ላይ ፈተና ሆኖ መቆየቱን ገልጸው÷ ይህን ችግር ለመፍታት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ መፈረሙን አስረድተዋል፡፡

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽታሁን ዋለ ድርጅታቸው ሚስጥራዊ ህትመቶችን በማተም የካበት ልምድ እንዳለው ጠቅሰው÷ ደረጃውን የጠበቀ፣ ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት በማይቻል መልኩ የህትመት ሥራውን ለማከናወን ዝግጅት ማድረጉን መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ግብር ከፋዮች ለገቢዎች ሚኒስቴር በሚያቀርቡት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ መሠረት የሚቀርቡ የህትምት ትዕዛዞችን ተቀብሎ ደረሰኞችን ለማተም በቂ ዝግጅት ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት ያስፈልጋል - አቶ ጌታሁን አብዲሳ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ተናገሩ።

21ኛው የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ሰብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሐሳብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንዳሉት ሙስና እና ብልሹ አሰራር የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳና የመልካም አስተዳደር ችግርን የሚያስፋፋ ነው።

ይኸን ለማስቀረትም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋት እና ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የትምህርት ተቋማት በመልካም ሥነምግባር የታነፀ ትውልድ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ጌታሁን ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ በበኩላቸው ውስብስብ እየሆነ የመጣውን ሙስና መታገል ሀገርን ማዳን ነው ብለዋል።

ተቋማት በመልካም ሥነ-ምግባር የታገዘ አገልግሎት በመስጠት ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እና ብልሹ አሰራሮች እንዲቀረፉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነም ገልጸዋል።

ወጣቶችን ያሳተፈ የፀረ-ሙስና ትግል ለሀገር ዕድገት መሰረት ነው ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወጣት መሐመድ ሙሐሙድ ነው።

ሙስና ወጣቱን የሚያሸማቅቅ ነው ያለው ወጣት መሐመድ፥ በመሆኑም ሁሉም ሰው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን መታገል አለበት ብሏል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፁ ወጣቶችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም አክሏል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሀገርን እድገት ለማስቀጠል በሥነምግባር የታነፀ ወጣት ማፍራት ወሳኝ መሆኑን የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአለም ፀረ-ሙስና ቀን በአገርዓቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ግዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!'' በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አዳል ሙላቱ እንደገለፁት ሙስና የሀገር እድገትን ከሚያቀጭጩ ጉዳዮች ዋንኛው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ሙስናን በመጠየፍና በመከላከል ለሀገር እድገት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ሙስና የልማት ስራዎች እንዳይስፋፉ የሚያደርግ መሆኑን ገለፀው፥ በተለይም ስራ አጥነት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦው የጎላ በመሆኑ ሁሉም ሊረባረብበት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የወጣቶች ህልም እውን እንዲሆን ለወጣቱ ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሥነምግባር ያለው ወጣት በመፍጠር ወጣቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል ሁሉም በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢልያስ በበኩላቸው ወጣቱ ነገ የሚረከበውን ሀገር ዛሬ መገንባት እንደሚገባ ገልፀው፥ በሥነምግባር በመታነጽ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ብልሹ አሰራርን ማስወገድና ሕግ እንዲከበር ማድረግ የወጣቶች ተሳትፎ የሚፈልግ ጉዳይ ስለሆ፥ በዚህ ረገድ ተሳትፎአቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ሙስናንና መልካም ሥነምግባርን የሚመለከት ሰነድ ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት ያደረሰው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከ25 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ታክስ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ክስ የቀረበበት በረከት አለኸኝ በ10 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ ላይ በነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በሀሰተኛ ሰነድ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ በህገወጥ መንገድ ንግድ ፍቃድ ማውጣትና ማደስ፣ የታክስ አዋጁን መተላለፍ፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም፣ የገቢ ደረሰኞችን አትሞ ለተለያዩ ነጋዴዎች ማሰራጨት የሚል ተደራራቢ 7 ክሶች በዝርዝር ማቅረቡ ይታወሳል።

በተለይም በመስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም እና በመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም ፍቃድ በማሳደስ የተመዘገበዉ በአስመጪነት ንግድ ስራ ዘርፍ ሆኖ ሳለ ምንም አይነት እቃ ከዉጭ ሀገር ሳያስገባ እና የሀገር ዉስጥ የዕቃ ግዥ ሳይፈጽም ከወሰደው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ደረሰኞችን በማተም ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 ደረሰኞችን በማሰራጨት በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት ደርሷል በማለት ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ክሶች መካከል ጠቅሶ ነበር።

ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ 30 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል በማለት ያቀረበው ዝርዝር ክስ ለተከሳሽ ከደረሰው በኋላ ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ጠቅሶ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ህግ 13 የሰው ምስክሮችን እና 23 ገላጭና አስረጂ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ የተሰሙ የሰው ምስክሮችን ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን ሰጥቶም ነበር።

በዚህም ፍርድ ቤቱ በአንደኛና በሁለተኛ ክሶች ላይ ማለትም ሰለሞን ሙሉ ከውል በሚል የፈጠራ ስም በወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያና ሀሰተኛ ውክልና መሰረት የንግድ ፍቃድ በማውጣትና በማሳደስ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት ተብሎ የቀረበውን ክስ በሚመለከት፣ ንግድ ፍቃድ መውጣቱንና መታደሱን እንጂ ሰለሞን ሙሉ ከውን በተባለው ሰው ወይም በተወካይ ንግድ ቢሮ ቀርቦ ንግድ ፍቃዱን ማን አወጣ ማን አሳደሰ የሚለው አሳማኝ ማረጋገጫ ያልቀረበ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

በተጨማሪም ከምስክሮች ቃል አሰጣጥ አንጻር በሰነዶች ማረጋጋጫ ተቋም አንድ ሰው በአካል ሳይቀርብ የጣት አሻራ ሳይሰጥና ሳይፈርም ውክልና እንደማይሰጥ መረዳቱን በመጥቀስ ሰለሞን ሙሉ ከውን በሚባል ሰው አሻራ ሰጥቶ ፈርሞ፣ በአካል ቀርቦ ውክልና የሰጠና ንግድ ፍቃድም ያወጣና ያሳደሰ መሆኑን ግምት መያዙን በማብራራት ከ1ኛ እና ከ2ኛ ክስ ነጻ ብሎታል።

ፍርድ ቤቱ 3ኛ እና 4ኛ ክስን በሚመለከት በ2010 እና በ2011 ዓ.ም ከውጭ ሀገር እቃ ሳያስገባና ምንም አይነት ሽያጭ ሳያከናውን ሀሰተኛ የተጭበረበሩ ሰነዶችን የዓመታዊ የግብር ሪፖርትን ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማስገባቱ መረጋገጡን በመጥቀስ 3ኛ ክስ ከ4ኛ ክስ ጋር ተጠቃሎ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 የገቢ ደረሰኞችን አትሞ በማሰራጨት የንግድ ትርፍና የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ 25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ83 ሳንቲም ጉዳት መድረሱን በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ፣ 5ኛ ክስን ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።

6ኛ ክስን በሚመለከት ደግሞ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከራየው ሱቅ ውስጥ ህገወጥ እውቅና የሌለው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያና ኮምፒዩተሮች በገቢዎች ሰራተኞች ተገኝቷል ተብሎ የቀረበው ክስን በሚመለከት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያው ከጁፒተር ንግድ ስራዎች ድርጅት የተገዛና የተገጠመ መሆኑን መረጋገጡን ችሎቱ ጠቅሶ እውቅና የሌለው ህገወጥ መሳሪያ ተገኝቷል በሚል በዐቃቤ ሕግ የቀረበው ክስን በሚመለከት ግን ማስረጃ አለመቅረቡን ገልጾ፥ ተከሳሹን በ6ኛ ክስ ነጻ ነው ብሎታል።

7ኛ ክስን በሚመለከት የታክስ አስተዳደር አዋጅን በመተላለፍ ግብይት ሳይኖር ህገወጥ ደረሰኝ መጠቀም የሚለው ክስ ከ5ኛ ክስ ዝርዝር ጋር በተመሳሳይ በሀሳብ መደራረብ ያለው መሆኑን ጠቅሶ፤ ፍርድ ቤቱ 7ኛ ክስን በሚመለከት ነጻ በማለት ብይን ሰጥቷል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረበውን የመከላከያ ማስረጃ መርምሮና ከዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ጋር አመዛዝኖ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጡን ጠቅሶ በሙሉ ጥፋተኛ መባሉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት መርምሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተከሳሹ ያቀረበውን 5 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በእርከን 29 መሰረት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ3 ሚሊየን 8 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319