Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በሐረሪ ክልል የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐረሪ ክልል ባለፉት አምስት አመታት የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7,493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ ለፍ/ቤት በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዩብ አህመድ ገልጸዋል።

በዚህም ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት የፍትህ ሥርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት አጥፊዎችን በፍርድ ቤት ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ጠቁመው፥ በክልል ደረጃ የወንጀል መዝገብ የማስቀጣት ምጠኔ 95 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ክሪምስ (CRIMS) የሚባል ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ እና ምዝገባ ስርዓት መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ለዚህም በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት አመታት መንግስት ሊያጣው የነበረን 231 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለመንግሰት ገቢ እንዲሆን መደረጉን ጠቁመዋል።

በክልሉ ህገወጥ የሰነድ ዝግጅትን ለመከላከል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃርም 51 ሺህ 418 ሰነዶችን የማረጋገጥ ስራ እንደተከናወነ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች ጠየቁ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ማጠቃለያ በዓል ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች ጠይቀዋል።

በክልሉ አለምዓቀፍ የሙስና ቀን በተከበረበት የተገኙ ተማሪዎች ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

ተማሪ በእምነት አትርሳው፣ ተማሪ ኤርሚያስ ቆጭቶና ተማሪ መልካሙ በለጠ ከሸኮ፣ ከጉራፈርዳ እና ከሚዛን አማን ከተማ ካሉት ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች በሚቋቋሙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት በመሳተፍ በሙስና መከላከል ስራ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በትምህርት ገበታ በሰዓቱ መገኘት፣ ኩረጃን በመጠየፍና ከመምህራን ጋር አባታዊ ግንኙነት በመፍጠር በሙስና መከላከሉ ስራ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያ አቶ ገብረዮሐንስ አብርሃ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ክበባትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ባለሙያው፣ ተከታታይነት ያለውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በተማሪዎች ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል።

በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ ትብለጥ እንግሊዝ ሙስናን ለመከላከል ከትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ወጣቶች ለብዙ ነገሮች ተጋላጭ መሆናቸውን የገለጹት ባለሙያዋ፣ ሙስናን በመጠየፍና ተዋናይ ከመሆን ወጣቶች እንዲታቀቡ አመለካከትና አስተሳሰብ ላይ የተጀመረው ስራ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሐሰተኛ የደረሰኝ ህትመትን ለመከላከል ያለመ ስምምነት ተፈረመ

*******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ገቢዎች ሚኒስቴር እና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በደረሠኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ከታክስ ደረሰኝ ህትመት ጋር በተያያዘ ልዩ መለያ ኮድ ተካቶ ማተም፣ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ የሐሰተኛ ደረሰኝ ህትመት በግብር አሰባበሰቡ ላይ ፈተና ሆኖ መቆየቱን ገልጸው÷ ይህን ችግር ለመፍታት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ መፈረሙን አስረድተዋል፡፡

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽታሁን ዋለ ድርጅታቸው ሚስጥራዊ ህትመቶችን በማተም የካበት ልምድ እንዳለው ጠቅሰው÷ ደረጃውን የጠበቀ፣ ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት በማይቻል መልኩ የህትመት ሥራውን ለማከናወን ዝግጅት ማድረጉን መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ግብር ከፋዮች ለገቢዎች ሚኒስቴር በሚያቀርቡት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ መሠረት የሚቀርቡ የህትምት ትዕዛዞችን ተቀብሎ ደረሰኞችን ለማተም በቂ ዝግጅት ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት ያስፈልጋል - አቶ ጌታሁን አብዲሳ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 30/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ተናገሩ።

21ኛው የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ሰብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሐሳብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንዳሉት ሙስና እና ብልሹ አሰራር የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳና የመልካም አስተዳደር ችግርን የሚያስፋፋ ነው።

ይኸን ለማስቀረትም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋት እና ቀጣይነት ያለው ትምህርት መስጠት እንደሚያስፈልግ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የትምህርት ተቋማት በመልካም ሥነምግባር የታነፀ ትውልድ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ጌታሁን ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ በበኩላቸው ውስብስብ እየሆነ የመጣውን ሙስና መታገል ሀገርን ማዳን ነው ብለዋል።

ተቋማት በመልካም ሥነ-ምግባር የታገዘ አገልግሎት በመስጠት ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እና ብልሹ አሰራሮች እንዲቀረፉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነም ገልጸዋል።

ወጣቶችን ያሳተፈ የፀረ-ሙስና ትግል ለሀገር ዕድገት መሰረት ነው ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወጣት መሐመድ ሙሐሙድ ነው።

ሙስና ወጣቱን የሚያሸማቅቅ ነው ያለው ወጣት መሐመድ፥ በመሆኑም ሁሉም ሰው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን መታገል አለበት ብሏል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፁ ወጣቶችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም አክሏል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319