Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
21ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) 21ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ተገልጿል።

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የሶማሊ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አብዲወሊ ጃማ ኮሚሽኑ ከለዉጡ ወዲህ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሙስናን በመከላከል ረገድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ አክለዉም ኮሚሽኑ በባለፈዉ አመት ያስጀመረውን የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች የሀብት ምዝገባ በ2017 በጀት ዓመት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ጠቁመው፥ ይህንን እንቅስቃሴ በክልል፣ ዞን እና ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ሙስና በሀገር ልማትና እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያስከትል በመሆኑ በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አራሮችን ለማስወገድ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ወጣቱን አሳታፊ ባደረገ መልኩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ ተመላክቷል።

በመርሀግብሩ ላይ የሶማሊ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ።

በጅግጅጋ ከተማ የተከበረዉ 21ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተመሳሳይ በክልሉ ቢሮዎች፣ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች መከበሩን የሶማሊ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሐረሪ ክልል የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐረሪ ክልል ባለፉት አምስት አመታት የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7,493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ ለፍ/ቤት በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዩብ አህመድ ገልጸዋል።

በዚህም ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት የፍትህ ሥርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት አጥፊዎችን በፍርድ ቤት ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ጠቁመው፥ በክልል ደረጃ የወንጀል መዝገብ የማስቀጣት ምጠኔ 95 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ክሪምስ (CRIMS) የሚባል ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ እና ምዝገባ ስርዓት መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ለዚህም በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት አመታት መንግስት ሊያጣው የነበረን 231 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለመንግሰት ገቢ እንዲሆን መደረጉን ጠቁመዋል።

በክልሉ ህገወጥ የሰነድ ዝግጅትን ለመከላከል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃርም 51 ሺህ 418 ሰነዶችን የማረጋገጥ ስራ እንደተከናወነ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319