Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የፀረ-ሙስና ቀን አከበሩ

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአለምዓቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያመከለ የፀረ- ሙስና ትግ፣ የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን የፀረ-ሙስና ቀን የሁለቱም ተቋማት ሰራተኞች አክብረዋል።

የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አስር ኢብራሂም ሁለቱ ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆናቸውን በመጥቀስ ሁሉም ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ ዘርፍ በአግባቡ አገልግሎት በመስጠት ሀላፊነታቸውን በመወጣት ብልሹ አሰራሮችን መታገል እንዳለባቸው ገልፀዋል።

አክለውም የፀረ-ሙስና ትግሉን በመታገል በጥሩ ሥነ-ምግባር የተገነባ ትውልድን መቅረፅ አሰፈላጊ ስለሆነ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተቋሙ አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ባለጉዳዮችን ባለማጉላላት ፈጣን የሆነ አገልግሎት በመሰጠት የተቋሙን ገፅታ መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ጭምር አሳውቀዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ኢንጂነር ቢፍቱ ጎሹ በበኩላቸው ተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እያንዳአንዱ ባለሙያ በተመደበበት ቦታ ላይ በአግባቡ እየሰራ ስለመሆኑ እራሱን ሊፈትሽ እንደሚገባ በማንሳት ሁሉም ባለሙያ የተሰጠውን ሀላፊነት በመወጣት ሙስናን መታገል እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የሥነ-ምግባር መከታተያ ባለሙያ ወ/ሮ አየለች ቄጡ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሩብ ዓመቱ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል የተባሉ 46 ባለሙያዎች እና ተገልጋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል ያላቸውን ባለሙያዎች እና ባለጉዳዮች ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል።

ኤጀንሲው ከሚሰጣቸው የመታወቂያ የልደት ካርድ እና ሌሎችም የኩነት ምዝገባ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሌብነት፣ የሥነ-ምግባር ጉድለት እንዲሁም ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ 46 ባለሙያዎች እንዲሁም ግለሰቦችን ከቀላል እስከ ከባድ የሥነ-ምግባር እና የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ነው የገለጸው፡፡

ከእነዚህም መካከል በቀላል ዲሲፕሊን 17፣ በከባድ 9 እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ 9 እንዲሁም፤ በማዕከሉ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት የመጡ 11 ባለጉዳዮች በጥቅሉ 46 ባለሙያዎችና ባለጉዳዮች በሩብ ዓመቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነስቷል።

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክፍለ ሀገር በመሸኛ የሚመጣን ነዋሪ በተመለከተ፤ "መረጃዎች ተጣርተው ወረፋ እየጠበቁ ካሉት ከ42 ሺሕ በላይ አገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ትክክለኛ መረጃ ያላቸውን ከሕዳር አንድ ጀምሮ አስተናግዳለሁ" ያለ ቢሆንም እስካሁን አለመጀመሩም ይታወቃል።

አሐዱም "ይህን አገልግሎት ለምን ሕዳር አንድ ማስጀመር አልተቻለም?" ሲል የኤጀንሲውን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ጀሚላ ረዲን ጠይቋል፡፡

"አገልግሎቱን ለማስጀመር የተገልጋዮችን ማስረጃ የማጣራቱ ሠራ እየተሰራ ነው። ተጣርተው የመጡ ማስረጃዎችም አሉ" ብለው፤ ነገር ግን በተባለበት ቀን ለማስጀመር የሲስተም ብልሽት እንዳጋጠመ እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን አሻራ መውሰድ ባለመቻሉ እንደዘገየ ገልጸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
21ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) 21ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ተገልጿል።

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የሶማሊ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አብዲወሊ ጃማ ኮሚሽኑ ከለዉጡ ወዲህ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሙስናን በመከላከል ረገድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ አክለዉም ኮሚሽኑ በባለፈዉ አመት ያስጀመረውን የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች የሀብት ምዝገባ በ2017 በጀት ዓመት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ጠቁመው፥ ይህንን እንቅስቃሴ በክልል፣ ዞን እና ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ሙስና በሀገር ልማትና እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያስከትል በመሆኑ በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አራሮችን ለማስወገድ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ወጣቱን አሳታፊ ባደረገ መልኩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ ተመላክቷል።

በመርሀግብሩ ላይ የሶማሊ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ።

በጅግጅጋ ከተማ የተከበረዉ 21ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተመሳሳይ በክልሉ ቢሮዎች፣ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች መከበሩን የሶማሊ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሐረሪ ክልል የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሐረሪ ክልል ባለፉት አምስት አመታት የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ መከናወኑን የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7,493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ ለፍ/ቤት በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዩብ አህመድ ገልጸዋል።

በዚህም ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት የፍትህ ሥርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት አጥፊዎችን በፍርድ ቤት ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ጠቁመው፥ በክልል ደረጃ የወንጀል መዝገብ የማስቀጣት ምጠኔ 95 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ክሪምስ (CRIMS) የሚባል ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ እና ምዝገባ ስርዓት መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ለዚህም በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 7493 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ በማቅረብ አጥፊዎች በወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት አመታት መንግስት ሊያጣው የነበረን 231 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለመንግሰት ገቢ እንዲሆን መደረጉን ጠቁመዋል።

በክልሉ ህገወጥ የሰነድ ዝግጅትን ለመከላከል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃርም 51 ሺህ 418 ሰነዶችን የማረጋገጥ ስራ እንደተከናወነ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319