በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቀነስ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው - ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር)
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስቴሩ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቀነስ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው ብለዋል። በቀጣይም ስልጠና በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች የሠውን ህይወት የሚጎዱ መሆኑን ገልፀው፥ በተለይ የመድሃኒት አቅርቦት ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል ብለዋል። ስለሆነም ለማህበረሰባችን የምንሰጠው አገልግሎት ከብልሹ አሰራር የፀዳ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ ካልሆነ ግን ችግሮች ተባብሰው ትውልዱን ይጎዳል ብለዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በጤና ሴክተሩ የዲጂታል አሰራርን በመከተል ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ኮሚሽኑ የሚሰጣቸው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎች በዘርፋ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተመረጡ ከፍተኛ ሙሁራን የማሰልጠኛ ሞጅሎችን በማዘጋጀት ዘርፍ ተኮር ስልጠናውን እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ፍቃዱ አክለውም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ እንቅፋት የሆነውን ሙስና ለመከላከል መንግስት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ በትውልድ የሥነምግባር ግንባታ ላይም ትኩረት አድርገን መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ ለዚህም ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ለጤና ዘርፍ አመራሮች ለሁለት ቀናት የተሰጠውን ስልጠና በበቃና ፈኬቻ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን፥ በቀጣይም ለሌሎች ዘርፎች ስልጠናው የሚሰጥ ይሆናል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክኒያት በማድረግ "በሥነምግባር ግንባታና በሙስና መከላከል ረገድ የሀይማኖት ተቋማት ሚና" በሚል ርዕስ ከኃይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክኒያት በማድረግ "በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ረገድ የኃይማኖት ተቋማት ሚና" በሚል ርዕስ ከኃይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ኮሚሽኑ በዋናነት በሥነምግባር ግንባታና በሙስና መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ስለሆነም የዛሬው መድረክ ዋና አላማ 21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መልክት ቀኑን የምናስብበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የሥነምግባር ግንባታ ስራ የሀይማኖት ተቋማትን በቀጥታ የሚመለከት በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን በጋራ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች በመንግስት ተቋም ብቻ ሳይሆን በሀይማኖት ተቋምም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አውስተው፥ ኮሚሽኑ ብቻውን መከላከልና መቆጣጠር ስለማይችል የሀይማኖት ተቋማት በጋራ በሥነምግባር ግንባታ ላይ በመስራት በሥነምግባሩ የታነፀ፣ ሰላምን የሚሻ፣ በእኩልነትና በፍትሀዊነት የሚያምን ትውልድ ልንፈጥር ይገባል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ማሩ ቸኮል በበኩላቸው ለብልሹ አሰራሮች ሁሉ ትልቁ ችግር የሥነምግባር ችግር ነው። በሥነምግባር ችግር እሴቶቻችን ተሸርሽረው መከባበርና መተባበር እየጠፋ ነው ብለዋል።
ስለሆነም ለሥነምግባር ግንባታ የእምነት ተቋማት ቅርብ ስለሆኑ የእምነት አባቶች በአስተምህሯችው በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ ተጋግዘን ልንሰራ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ አቶ ዘላለም ንጉሴ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበው የመወያያ ሰነድ እጅግ ሳቢና ችግሮችን ነቅሶ ያሳየ መሆኑንና ኮሚሽኑም የምክክር መድረኩን ማዘጋጀቱ እጀግ ሊቀጥልና ሊበረታታ ይገባል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የፀረ-ሙስና ቀን አከበሩ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአለምዓቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያመከለ የፀረ- ሙስና ትግ፣ የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን የፀረ-ሙስና ቀን የሁለቱም ተቋማት ሰራተኞች አክብረዋል።
የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አስር ኢብራሂም ሁለቱ ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆናቸውን በመጥቀስ ሁሉም ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ ዘርፍ በአግባቡ አገልግሎት በመስጠት ሀላፊነታቸውን በመወጣት ብልሹ አሰራሮችን መታገል እንዳለባቸው ገልፀዋል።
አክለውም የፀረ-ሙስና ትግሉን በመታገል በጥሩ ሥነ-ምግባር የተገነባ ትውልድን መቅረፅ አሰፈላጊ ስለሆነ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተቋሙ አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ባለጉዳዮችን ባለማጉላላት ፈጣን የሆነ አገልግሎት በመሰጠት የተቋሙን ገፅታ መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ጭምር አሳውቀዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ኢንጂነር ቢፍቱ ጎሹ በበኩላቸው ተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እያንዳአንዱ ባለሙያ በተመደበበት ቦታ ላይ በአግባቡ እየሰራ ስለመሆኑ እራሱን ሊፈትሽ እንደሚገባ በማንሳት ሁሉም ባለሙያ የተሰጠውን ሀላፊነት በመወጣት ሙስናን መታገል እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የሥነ-ምግባር መከታተያ ባለሙያ ወ/ሮ አየለች ቄጡ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሩብ ዓመቱ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል የተባሉ 46 ባለሙያዎች እና ተገልጋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል ያላቸውን ባለሙያዎች እና ባለጉዳዮች ተጠያቂ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከሚሰጣቸው የመታወቂያ የልደት ካርድ እና ሌሎችም የኩነት ምዝገባ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሌብነት፣ የሥነ-ምግባር ጉድለት እንዲሁም ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ 46 ባለሙያዎች እንዲሁም ግለሰቦችን ከቀላል እስከ ከባድ የሥነ-ምግባር እና የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ነው የገለጸው፡፡
ከእነዚህም መካከል በቀላል ዲሲፕሊን 17፣ በከባድ 9 እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ 9 እንዲሁም፤ በማዕከሉ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት የመጡ 11 ባለጉዳዮች በጥቅሉ 46 ባለሙያዎችና ባለጉዳዮች በሩብ ዓመቱ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነስቷል።
የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክፍለ ሀገር በመሸኛ የሚመጣን ነዋሪ በተመለከተ፤ "መረጃዎች ተጣርተው ወረፋ እየጠበቁ ካሉት ከ42 ሺሕ በላይ አገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ትክክለኛ መረጃ ያላቸውን ከሕዳር አንድ ጀምሮ አስተናግዳለሁ" ያለ ቢሆንም እስካሁን አለመጀመሩም ይታወቃል።
አሐዱም "ይህን አገልግሎት ለምን ሕዳር አንድ ማስጀመር አልተቻለም?" ሲል የኤጀንሲውን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ጀሚላ ረዲን ጠይቋል፡፡
"አገልግሎቱን ለማስጀመር የተገልጋዮችን ማስረጃ የማጣራቱ ሠራ እየተሰራ ነው። ተጣርተው የመጡ ማስረጃዎችም አሉ" ብለው፤ ነገር ግን በተባለበት ቀን ለማስጀመር የሲስተም ብልሽት እንዳጋጠመ እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን አሻራ መውሰድ ባለመቻሉ እንደዘገየ ገልጸዋል፡፡