በየደረጃው የሚገኙ የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ይገኛል
**
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በየደረጃው የሚገኙ የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዓሉን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!” በሚል መሪ ቃል የአብጅታ ሻላ ሀይቆች፣ የባሌ ተራራዎች፣ የአልጣሽ እና የሰሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበራቸውን ከባለስልጣኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቀነስ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው - ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር)
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስቴሩ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቀነስ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው ብለዋል። በቀጣይም ስልጠና በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች የሠውን ህይወት የሚጎዱ መሆኑን ገልፀው፥ በተለይ የመድሃኒት አቅርቦት ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል ብለዋል። ስለሆነም ለማህበረሰባችን የምንሰጠው አገልግሎት ከብልሹ አሰራር የፀዳ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ ካልሆነ ግን ችግሮች ተባብሰው ትውልዱን ይጎዳል ብለዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በጤና ሴክተሩ የዲጂታል አሰራርን በመከተል ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ኮሚሽኑ የሚሰጣቸው የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎች በዘርፋ የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተመረጡ ከፍተኛ ሙሁራን የማሰልጠኛ ሞጅሎችን በማዘጋጀት ዘርፍ ተኮር ስልጠናውን እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ፍቃዱ አክለውም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ እንቅፋት የሆነውን ሙስና ለመከላከል መንግስት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ በትውልድ የሥነምግባር ግንባታ ላይም ትኩረት አድርገን መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ ለዚህም ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ለጤና ዘርፍ አመራሮች ለሁለት ቀናት የተሰጠውን ስልጠና በበቃና ፈኬቻ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን፥ በቀጣይም ለሌሎች ዘርፎች ስልጠናው የሚሰጥ ይሆናል።