ሙስና የኢኮኖሚ ብልሽትን፣ የባህል ስብራትን እና የፖለቲካ ዝቅጠትን ያመጣል - አቶ ብርሃኑ ጎሽም
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያመከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በባህርዳር ከተማ በፓናል ውይይት አክብረዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም በመክፈቻ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት ይህንን ቀን ስናከብር በዋናነት ሙስናን የሚጠላ ትውልድ ለመፍጠር፣ የሙስና አስከፊነትን ለመረዳት እና ወንጀሉን ለመከላከል የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ነው ብለዋል።
ሙስና ከህግ ውጭ በመስራት ራስን ወይም ሌላውን መጥቀም ሲሆን፣ መንስኤዎቹ የሥነምግባር ዝቅጠትና ብልሽት ቢሆኑም ትልቁና ዋነኛው መንስኤ ግን የስብዕና መጓደል እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም የሰላምና የፖለቲካ አለመረጋት እና የኢኮኖሚ ዝቅተኛነት ሙስናን ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ሙስና የኢኮኖሚ ብልሽትን፣ የባህል ወለምታን እና የፖለቲካ ዝቅጠትን እንደሚያመጣ ገልፀው፥ የፀረ-ሙስና ትግላችን በመልካም መንገድ የሚሰራ ከሆነ ኢኮኖሚያችንና ባህላችን ያድጋል፣ ፖለቲካችንም የተረጋጋና ሁሉንም የሚያሻግር ይሆናል ብለዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ሙስናን ከመከላከል አኳያ ከሁሉም በፊት እኛ ራሳችን ንፁህ መሆን ይጠበቅብናል ብለው፥ የተጠያቂነትን ሚና በመወጣት የህዝብና የመንግስትን ሀብት ለታለመለት አላማ ለማዋል ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለመጭው ትውልድ ከወንጀል ነፃ እና የበለፀገች ሀገርን ለማስተላለፍ ከሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ራስን ንፁህ አድርጎ በሥነምግባር አርአያ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል ብለዋል።
አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በበዓሉ የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በየደረጃው የሚገኙ የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ይገኛል
**
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በየደረጃው የሚገኙ የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዓሉን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!” በሚል መሪ ቃል የአብጅታ ሻላ ሀይቆች፣ የባሌ ተራራዎች፣ የአልጣሽ እና የሰሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበራቸውን ከባለስልጣኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።