በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን የክልሉ ፍትህ ቢሮ እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሰራተኞች በጋራ አክብረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አማር ረጀብ ዛሬ ላይ የሚደረግ የፀረ-ሙስና ትግል ለነገ ወጣቶች የተሻለ ነገን ስለሚፈጥር ወጣቶችን የትግሉ አካል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ኃሳብ ሰነድ በክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባር ግንባታ ስልጠና ባለሙያ በአቶ ገዛኽኝ የኔው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪነት የዘንድሮው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በክልሉ በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በጋምቤላ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጋምቤላ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮች 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡሎክ ለክልላችን ከሙስና የራቀ ልማት ፈላጊ አመራረ ያስፈልገዋል ብለዋል።
በተለይም በክልሉ ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች እንደ የክልሉ ስታዲየምና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የት ደረሱ የሚል ቁርጠኛ መሪ የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልፀው፥ ከአመራሩ ጎን ባለሙያዎችም ሥነ-ምግባራዊ ሥራ መሥራትና ለተቋማቸው ታማኝ መሆን እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልል ደረጃ የተቋቋመው የፀረ-ሙስና ዐቢይ ኮሚቴ ከተመሠረተ ጀምሮ በክልሉ ልማት ላይ ያበረከተው አስተዋፅኦ ለሕዝብ ግልፅ እንዳልሆነ አሳስበው፥ ወደፊትም በመንግስትና ሕዝብ ላይ ይበልጥ አመኔታ ለመፍጠር ለሕዝብ ግልፅ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ተገልጿል።
በክልሉ 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሙስና የኢኮኖሚ ብልሽትን፣ የባህል ስብራትን እና የፖለቲካ ዝቅጠትን ያመጣል - አቶ ብርሃኑ ጎሽም
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 28/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያመከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በባህርዳር ከተማ በፓናል ውይይት አክብረዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም በመክፈቻ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት ይህንን ቀን ስናከብር በዋናነት ሙስናን የሚጠላ ትውልድ ለመፍጠር፣ የሙስና አስከፊነትን ለመረዳት እና ወንጀሉን ለመከላከል የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ነው ብለዋል።
ሙስና ከህግ ውጭ በመስራት ራስን ወይም ሌላውን መጥቀም ሲሆን፣ መንስኤዎቹ የሥነምግባር ዝቅጠትና ብልሽት ቢሆኑም ትልቁና ዋነኛው መንስኤ ግን የስብዕና መጓደል እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም የሰላምና የፖለቲካ አለመረጋት እና የኢኮኖሚ ዝቅተኛነት ሙስናን ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ሙስና የኢኮኖሚ ብልሽትን፣ የባህል ወለምታን እና የፖለቲካ ዝቅጠትን እንደሚያመጣ ገልፀው፥ የፀረ-ሙስና ትግላችን በመልካም መንገድ የሚሰራ ከሆነ ኢኮኖሚያችንና ባህላችን ያድጋል፣ ፖለቲካችንም የተረጋጋና ሁሉንም የሚያሻግር ይሆናል ብለዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ሙስናን ከመከላከል አኳያ ከሁሉም በፊት እኛ ራሳችን ንፁህ መሆን ይጠበቅብናል ብለው፥ የተጠያቂነትን ሚና በመወጣት የህዝብና የመንግስትን ሀብት ለታለመለት አላማ ለማዋል ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለመጭው ትውልድ ከወንጀል ነፃ እና የበለፀገች ሀገርን ለማስተላለፍ ከሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ራስን ንፁህ አድርጎ በሥነምግባር አርአያ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል ብለዋል።
አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በበዓሉ የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።