ኮሚሽኑ “ሥነ ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አደረገ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር "ስነ ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጁት የፓናል ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሌብነት እና ብልሹ አሰራር የሀገር እድገት ጸር መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ ደረጃ እንዳትደርስ ካደረጓት ችግሮች አንዱ ሙስና ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው፥ በአዲስ አበባ ሙስናን የመከላከል ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ ገለጹ።
ኮሚሽነር ጀማል አክለውም ሙስና ሀገር እና ህዝብን አደጋ ላይ የሚጥል እኩይ ተግባር መሆኑን መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መቅደስ ተስፋዬ በበኩላቸው በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። አያይዘውም የጸጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባም አመላክተዋል።
ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ትውልድን በስነ ምግባር መገንባት እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ(ዶ/ር) ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።
መድረኩ ከሙስና የጸዳ ከተማ እና ሀገር ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡ ሙስናን ለመከላከል አጋዥ እንዲሆን የጋራ አረዳድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ እናትአለም መለሰ በበኩላቸው፥ መገናኛ ብዙሃን ሙስናን መታገል የዘውትር ተግባራቸው መሆን አለበት ብለዋል።
የስነ ምግባር ግንባታና ሌሎች ተግባራትን በሙያቸው አርዓያ በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

በአማራ ክልል 21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ በፓናል ውይይት መከበሩ ተገለፀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ መልዕክት የአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የተቋማት ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፓናል ውይይት አክብሯል።
በመድረኩ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ስናከብር መሪ ቃሉን በዕለቱ ከማሰብ ባለፈ የሙስናን አስከፊነትና በሀገራችን ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዩች ላይ እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት ህብረተሰቡ በመረዳት በየደረጃው ያለው የክልላችን ነዋሪዎች በተለይም የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤትና ቁርጠኛ ሁነው ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመታገል ቃል የምንገባበት ቀን ነው ብለዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም ሙስና ግለሰብን፣ ቤተሰብንና ተቋማትን የሚጎዳና የሀገርን አንድነትና ህልውና የሚያናጋ ውስብስብ አደገኛ ወንጀል ከመሆኑም ባሻገር ልማት በሚፈለገው ልክ እንዳይፈጥን መሰናክል በመሆን ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝል ገልፀዋል፡፡
ቀጣይ በሚደረገው የሥነ-ምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ትግል የትምህርት ተቋማት፣ የዲሞክራሲ ተቋማት፣ የፍትህ ተቋማት፣ የሚዲያ አካላት፣ የሲቪል ማህበራትና የሐይማኖት ተቋማት ሁሉም የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበው ፣ ሙሰኞችንና ሌቦችን በመጠቆም ብሎም ማስረጃና ምስክር በመሆን ረገድ መላው የክልሉ ህብረተሰብ የበኩላችውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አድርገዋል።
የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣት በቁጥርም ሆነ በአቅም በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካውና በማህበራዊ ጉዳይ የሚኖራቸው ተሳትፎ ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን የፀረ ሙስና ትግል ወጣቱን ያሳተፈ ማድረግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አደለም ብለዋል።
የቢሮ ኃላፊው አያይዘውም ሙስና በመቀበልም ሆነ በመስጠት ረገድ ወጣቶች ተጋላጭ ናቸው ተብሎ ስለሚታመን በአቋራጭ ሂወታቸውን ለመምራት በሚያደርጉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን እንዲታገሉ ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኮሚሽኑ የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ ወ/ሪት መስከረም አዲስ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው ወጣቱ ትውልድ በፀረ ሙስና ትግሉ ተሳታፊ እንዲሆን የማደራጀትና በልማቱም ግንባር ቀደም ሁነው እንዲታገሉ የሚመለከተው አካል ድጋፍና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል በማለት አስተያየታቸውን ሰጠዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን የክልሉ ፍትህ ቢሮ እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሰራተኞች በጋራ አክብረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አማር ረጀብ ዛሬ ላይ የሚደረግ የፀረ-ሙስና ትግል ለነገ ወጣቶች የተሻለ ነገን ስለሚፈጥር ወጣቶችን የትግሉ አካል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ኃሳብ ሰነድ በክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባር ግንባታ ስልጠና ባለሙያ በአቶ ገዛኽኝ የኔው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪነት የዘንድሮው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በክልሉ በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በጋምቤላ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጋምቤላ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮች 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡሎክ ለክልላችን ከሙስና የራቀ ልማት ፈላጊ አመራረ ያስፈልገዋል ብለዋል።
በተለይም በክልሉ ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች እንደ የክልሉ ስታዲየምና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የት ደረሱ የሚል ቁርጠኛ መሪ የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልፀው፥ ከአመራሩ ጎን ባለሙያዎችም ሥነ-ምግባራዊ ሥራ መሥራትና ለተቋማቸው ታማኝ መሆን እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልል ደረጃ የተቋቋመው የፀረ-ሙስና ዐቢይ ኮሚቴ ከተመሠረተ ጀምሮ በክልሉ ልማት ላይ ያበረከተው አስተዋፅኦ ለሕዝብ ግልፅ እንዳልሆነ አሳስበው፥ ወደፊትም በመንግስትና ሕዝብ ላይ ይበልጥ አመኔታ ለመፍጠር ለሕዝብ ግልፅ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ተገልጿል።
በክልሉ 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።