ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ ነው - ም/ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ
*********************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለፋይናንስ ዘርፍ አመራሮች ‘‘ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል ርዕስ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናዉ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ ሙስና ለመከላከል ትውልድን የሚገነባ የሥነምግባር ስልጠናዎችን ማብቃት ሲቻል እንደሆነ ጠቁመዋል።
ስልጠናው ሙስና ስጋት ዳሰሳዊ ጥናት ግኝት መነሻ ተደርጎ፣ የብልሹ አሰራር መገለጫዎችና ምልክቶቹን በማየት የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ አክለውም የፀረ-ሙስና ትግሉን ግንባር ቀደም ሆነን በማስተባበር በተለይም ተቋም ተኮር ችግሮችን ለመፍታት በየዘርፎቹ የሚሰጡ ስልጠናዎች በመውሰድ፣ ከብልሹ አሰራር የፀዳ አመራር እና ሰራተኛን በማብቃት፣ ንቅናቄ በመፍጠር እና በማነፅ ሀገራዊ ግዳታን መወጣት አለበት ብለዋል።
አመራሩ እራሱን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በማራቅ ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልኮ መወጣት እንደሚገባ አሳስበው፣ በተቋም ለሚፈጠሩ አስተዳደራዊ ችግሮች በራሱ አቅም እርምጃ የመውሰድ እና የማስወሰድ ግዴታ እንዳለውም ጠቁመዋል።
የሙስና መከላከል ስራው መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ 26 ዘርፎች ተለይተው የስነ ምግባር ግንባታ ስልጠናና አቅም መገንቢያ ማሰልጠኛ ሞጅሎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በጥቂት ግለሰቦች ብልሹ አሰራር ተቋማት እና የንፁሀን ግለሰቦች ስም መጥፋት እንደሌለበት ገልፀው፣ አመራሩ እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች በትኩረት በመውሰድ ተቋምን እና ሰራተኛውን በሥነምግባር ማብቃት አለበት ብለዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሩ አያይዘውም የተጀመሩ የሙስና መከላከል ስራዎች በማጠናከር ዘርፉን በግልፅነትና ተጠያቂነት ለመምራት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በሙስና መከላከል ሂደት ውስጥ አመራሩና ፈፃሚ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
ስልጠናው በዶ/ር ሀይለየሱስ ተሰማ እየተሰጠ ሲሆን፣ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ- ሙስና ቀን አከበሩ
*********************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት በፓናል ውይይት አከበሩ።
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን፣ መድረኩ በተለያዩ ትዕይንቶች በአማረና በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።