Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሴክተር፣ የወረዳና የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ሰብእና ይገነባል!“ በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ሙስና የሀገርን እና የህዝብን ውስን ሀብት እንዲመዘበር ከማድርጉም በላይ ዜጎች ማግኘት ያለባቸውን ጥቅምና መብቶቻቸውን ጭምር ያላግባብ እንዲያገኙና እንዳይጠቀሙ በማድረግ ጥቂቶች ያልተገባቸውን እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።

ስለሆነም ልንጸየፈው ብቻ ሳይሆን ከመፈጸሙ በፊት በመከላከልና ማንኛውንም ህግንና ደንብን ያልተከተለ አሰራርንና ለሙስና ድርጊት በር ከፋች የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እንዳይፈጸሙ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አጥብቆ መታገል የሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎች ኃላፊነትና ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የአስተዳደሩ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመበ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል።

በተለይም ያለ እውቀት ክህሎትና በቂ የትምህርት ዝግጅት በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሰራተኛ ቅጥር ህጉንና መስፈርቱን ያልተከተሉ አሰራሮች ለኮሚሽኑ የደረሱ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ማስቆም መቻሉን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የመንግስትና የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን ከህጉ ውጪ ወደ ግለሰብ ለማዞርና ካርታ ለማሰራት የተደረጉ ጥረቶችን ማክሸፍ እንደተቻለ አክለው፥ ይህም ብልሹ አሰራሮችን ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም በታገሉ ዜጎች የነቃ ተሳትፎና ትብብር የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሙስና ተግባራት የሚፈጸሙባቸውን ውስብስብና ህቡእ አካሄዶችን የተሳታፊዎቹን የአደረጃጀት ሰንሰለቶችን የሚያደርሰውን ጉዳትና የሚያስከትላውን አስከፊ ቀውሶች ሚዳስሱ ነጥቦች የተካተቱበት መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት መደረጉን የአስተዳደርሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ተሳታፊዎቹ በየተቋሞቻቸው ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለማቀፉን የፀረ-ሙስና ቀን ሲያከብሩ ይህንኑ ግንዛቤ በማስጨበጥና የፀረ-ሙስና ትግሉን በቁርጠኝነትና በጋራ በንቃት ልንሳተፍበት ይገባል ሲሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የህይወታችን ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የሞራል ፈተና ነው - ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በሚዛን አማን ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የበዓሉ መከበር አስተሳሰቦቻችን ሙስናን በወሳኝ መልኩ ሊያርም በሚችል ወጣቱን ባለቤት በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ቀኑ በሁሉም መልክ ሙስናን ለመዋጋት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ታማኝነትን ለማጎልበት ያለን የጋራ ኃላፊነት ጠንካራ ማስታወሻ ሆኖ ያገልግላል ሲሉም ኮሚሽነር ሙሉሰው ተናግረዋል።

ሙስና የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ በሁሉም የህይወታችን ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የሞራል ፈተና ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ዛሬ እዚህ በምንሰበሰብበት ወቅት እያንዳንዳችሁ በተለይም ወጣቶች አቅማችሁን እንደ የለውጥ ፈላጊዎች እንድትገነዝቡ እጠይቃለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

በትምህርትና በአስተዳደር ሂደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ እኩዮቻችሁንና ማህበረሰቡ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ የማድረግ ችሎታ አላችሁ፣ ሙስናን በጋራ በመቆም፣ ታማኝነት ከምንም በላይ የሚከበርበትን የወደፊት ጊዜ ለመቅረጽ መርዳት ትችላላችሁ ሲሉም ኮሚሽነር ሙሉ ሰው ዘውዴ ለወጣቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሙስና በጉቦ፣ ገንዘብ በማጭበርበር፣ ወገንተኝነት እና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም ከመገለጫዎቹ ጥቂቶች መሆናቸውን ያስታወሱት ኮሚሽነር ሙሉሰው፣ እነዚህ ተግባራት ተቋማትን ያዳክማል፣ የኢኮኖሚ ልማትን ያቀዘቅዛል፣ ለመንግስታዊ አለመረጋጋት አስተዋጽኦ ያደርጋል፣ በህብረተሰቡ ውስጥ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን እንደሚጎዳም ገልጸዋል።

ሙስናን ለመዋጋት በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ኃላፊነት ለሚሰማው ዜግነት ማዘጋጀት እንዳለባቸው አመላክተዋል።

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ማህበረሰቡን በሥነምግባር አስተምህሮዎች ላይ የተመሰረተ ታማኝነትና ሙስና የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመረዳት ትውልዱ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ በሥነግጥም፣ በድራማ፣ በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር እየተከበረ ሲሆን፣ ዕለቱን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቴክኖሎጂ የታገዘ ዌብሳይት አልምቶ ስራ ላይ ማዋሉንም በዕለቱ ገለጻና ማብራሪያ በአቶ ሙባረክ አበበ መቅረቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

በበዓሉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ቡድን አስተባባሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319