Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 21ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሴክተር፣ የወረዳና የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ሰብእና ይገነባል!“ በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ሙስና የሀገርን እና የህዝብን ውስን ሀብት እንዲመዘበር ከማድርጉም በላይ ዜጎች ማግኘት ያለባቸውን ጥቅምና መብቶቻቸውን ጭምር ያላግባብ እንዲያገኙና እንዳይጠቀሙ በማድረግ ጥቂቶች ያልተገባቸውን እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።

ስለሆነም ልንጸየፈው ብቻ ሳይሆን ከመፈጸሙ በፊት በመከላከልና ማንኛውንም ህግንና ደንብን ያልተከተለ አሰራርንና ለሙስና ድርጊት በር ከፋች የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እንዳይፈጸሙ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አጥብቆ መታገል የሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎች ኃላፊነትና ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የአስተዳደሩ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመበ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል።

በተለይም ያለ እውቀት ክህሎትና በቂ የትምህርት ዝግጅት በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሰራተኛ ቅጥር ህጉንና መስፈርቱን ያልተከተሉ አሰራሮች ለኮሚሽኑ የደረሱ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ማስቆም መቻሉን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የመንግስትና የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን ከህጉ ውጪ ወደ ግለሰብ ለማዞርና ካርታ ለማሰራት የተደረጉ ጥረቶችን ማክሸፍ እንደተቻለ አክለው፥ ይህም ብልሹ አሰራሮችን ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም በታገሉ ዜጎች የነቃ ተሳትፎና ትብብር የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሙስና ተግባራት የሚፈጸሙባቸውን ውስብስብና ህቡእ አካሄዶችን የተሳታፊዎቹን የአደረጃጀት ሰንሰለቶችን የሚያደርሰውን ጉዳትና የሚያስከትላውን አስከፊ ቀውሶች ሚዳስሱ ነጥቦች የተካተቱበት መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት መደረጉን የአስተዳደርሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ተሳታፊዎቹ በየተቋሞቻቸው ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለማቀፉን የፀረ-ሙስና ቀን ሲያከብሩ ይህንኑ ግንዛቤ በማስጨበጥና የፀረ-ሙስና ትግሉን በቁርጠኝነትና በጋራ በንቃት ልንሳተፍበት ይገባል ሲሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319