Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የባለስልጣኑ አመራርና ሰራተኞች የሙስናን ጉዳት በመረዳት ከችግሩ መራቅ እንደሚገባቸው ተገለፀ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አክብረዋል።

የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ የባለስልጣኑ አመራርና ሰራተኞች የሙስናን ጉዳት በመረዳት እራስን ከሙስና ችግር በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ማራቅ ይገባል ብለዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አሰግደዉ ኃ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ሙስናም ሆነ ብልሹ አሰራር የሀገርን እድገት የሚገታ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ህዝብ በህግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው የሚያደርግ ተግባር እንደመሆኑ የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የባለስልጣኑ ሰራተኞችም እለቱን አስመልክቶ የተላለፉ መልዕክቶችን መሰረት በማድረግ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የባለስልጣኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ሁንዳራ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።

የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በቀረበው የመወያያ ሰነድ መሰረት ሙስና እና ብልሹ አሰራር የሀገር ኢኮኖሚ በሚፈለገው የደረጃ እድገት እንዳያሳይም ሆነ የሥነምግባር ቀውስ እንዲባባስ የሚያደርግ ችግር በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል የተደነገጉ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በመጨረሻም የፀረ-ሙስና ቀንን የተመለከቱ የጥያቄና መልስ ዉድድር ተካሄዱ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በሚኒስቴር መስሪያቤቱ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ- ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች "ወጣቶችን ያማከለ የፀ-ረሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሃሳብ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በደማቅ ዝግጅት አክብረዋል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር ) ሙስና ለሀገራችን ሰላም እና ልማት ትልቅ ተግዳሮት ነው ያሉ ሲሆን፥ የፀረ-ሙስና ትግል የሁሉንም ተሳትፎና እርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

የዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን ወጣቶችን ያማከለ አድርጎ መከበሩ ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ክቡር ከይረዲን፥ ወጣቶችን ለፀረ-ሙስና ትግልና ለሀገር ግንባታ ስራችን ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ ''ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ'' የሚል ሰነድ የሰላም ሚኒስቴር የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ አበራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በበዓሉ ለተነሱ ሃሳቦችም የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ የአንድ ሀገር ቀጣይነት የሚረጋገጠው ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማት ሲኖሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የአገረ መንግስቱ አንዱ ቁልፍ ችግር ነፃ፣ ገለልተኛና ማህበረሰቡን የሚጠብቁ ተቋማት ሳይገነቡ መቆየታቸውን ገልፀው፥ በዚህ በኩል መንግስት ትልልቅ ሪፎርሞችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ሙስናን ለመታገል ጠንካራ ተቋማት እና የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ቸሩጌታ፥ ሙስናን መታገል ንብረትን ከዘረፋ እና ብክነት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሀገርን የመገንባት ስራ መሆኑን መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የኮሙኒኬሽን ተቋሙ የሰው ኃይል በፀረ-ሙስና ትግሉ ድርብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ተገንዝቦ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገለፀ

**

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 27/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የፀረ-ሙስና ቀን በጋራ አክብረዋል።

ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን በአለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ሰብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል ተቋማቱ በጋራ ያክብረዋል።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኀላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ የማህበረሰብና የሀገር እድገትና ልማት እንቅፋት የሆነውን የሙስና እሳቤና ድርጊት ከማውገዝ፣ መከላከል፣ መታገል አንፃር የኮሙኒኬሽን ተቋሙ የሰው ኃይል ድርብ ኀላፊነት ያለበት ነው ብለዋል።

እንደ ዜጋ ከዚህ አስነዋሪ ድርጊት ራስን ነፃ ከማድረግ ጀምሮ በመታገሉን ረገድ ያለብን ድርሻ ሳይዘነጋ በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ሥራችን የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ የሚያደርጉ ስራዎችን ማከናወን ይገባናልም ብለዋል።

የተቋማቱ ሠራተኞች ከሙስና ጋር የተገናኙ የሚታዩ አዝማሚያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ ችግሩ ማህበረሰባዊ የነቃ ተሳትፎ እንዲቀለበስም የድርሻቸውን እንደሚወጡ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ውይይቱን የኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ እና ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ ከህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኀላፊው አቶ አባይነህ ጌጡ ጋር በመሆን መርተዋል።

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319