Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብሯል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበሩን ገልጿል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንትና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ ሁላችንም የፀረ-ሙስና ትግል ንቁ ተሳታፊ እንድንሆንና ወጣቱ በስፋት ትግሉን እንዲቀላቀል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበኩላቸው የዘንድሮን በዓል ልዩ የሚያደርገው ከሀገራችን ሕዝብ አብዛኛው ወጣት ከመሆኑ የተነሣ ይህ ከፍተኛው ኃይል ለፀረ-ሙስና ትግል ቢሳተፍ ከፍ ያለ ዉጤት እንደሚያስመዘግብ በማመን ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱና ለማሣተፍ የእያንዳንዳችን ድርሻ የላቀ መሆኑን ማስገንዘቡ ነዉ ብለዋል።

ኮሚሽነሯ አክለዉም በዓሉን ስናከብር እንደልማድ ብቻ ሣይሆን ዓላማው ገብቶን የትግሉ ተጋሪና የሰላ ትግል ማድረግ ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር አጋርነታቸውን ላሳዩ ለተለያዩ መዋቅሮች የዕዉቅና ሽልማት የመስጠት ሥነሥርዓት መካሄዱ ተገልጿል።

ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ "ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ለመገንባት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረዉን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በክልሉ በተለያዩ ተቋማትና መዋቅሮች ከህዳር 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ተገልጿል።

የበዓሉ ማጠቃለያ በኮሚሽኑ አዘጋጂነት በምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን መቀመጫ በሆነችዉ በንሣ ዳዬ ከተማ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በርካታ ወጣቶች በተገኙበት በክልሉ ማርሽ ባንድ ከዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ ቅስቀሳና ድጋፍ በታገዘ ሁኔታ በተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ በሆኑ ድራማ፣ ጭውውትና በባለድርሻ አካላት ፓናል ዉይይት መከበሩ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የሥነምግባር ግንባታ ላይ የሚውል አቅም የሀገር ግንባታ ላይ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ወሳኝ ነው - ፎዚያ አሚን (ዶ/ር)

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፎዝያ አሚን (ዶ/ር) የሥነምግባር ግንባታ ላይ የሚውል አቅም የሀገር ግንባታ ላይ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የሥነ-ምግባር ግንባታ ብልሹ አሰራርን ከምንጩ ለመከላከል የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ፎዚያ አሚን፥ ለተቋም ስኬታማነት የተቋሙን ማህበረሰብ በሥነምግባር መገንባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሃረጎት አብርሃ ተቋማት ከሥነምግባር ግንባታ ጎን ለጎን የሙስና መከላከል ስራን ለመስራት ለተቋማት የሙስና ተጋላጭነት ስጋት የሚፈጥሩ አሰራሮችን በጥናት መለየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙስና መከላከል ስራን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለመስራት ከሚንስቴር መስርያቤቱ ብዙ እንደሚጠብቅና በግልጽ የተጀመሩ የሙስና መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የዘርፉ ተቋማት አመራሮች በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አቶ ሃረጎት አንስተዋል።

ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ስልጠና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣ የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አመራሮች እየወሰዱ ይገኛል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319