Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.89K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን ለመከላከል ወጣቶች ላይ መስራት የተሻለ ውጤት ያመጣል ተባለ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞች 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ተወካይ አቶ ታረቀኝ ወዲ ቀደም ባሉ በርካታ ዓመታት ሙስናን ለመታገል ብዙ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ባለመምጣቱ በተለየ ሁኔታ ወጣቶች ላይ መስራት የተለየ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የዘድሮውን የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብሯል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ማክበሩን ገልጿል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንትና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ ሁላችንም የፀረ-ሙስና ትግል ንቁ ተሳታፊ እንድንሆንና ወጣቱ በስፋት ትግሉን እንዲቀላቀል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ ዘላለም ለማ በበኩላቸው የዘንድሮን በዓል ልዩ የሚያደርገው ከሀገራችን ሕዝብ አብዛኛው ወጣት ከመሆኑ የተነሣ ይህ ከፍተኛው ኃይል ለፀረ-ሙስና ትግል ቢሳተፍ ከፍ ያለ ዉጤት እንደሚያስመዘግብ በማመን ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱና ለማሣተፍ የእያንዳንዳችን ድርሻ የላቀ መሆኑን ማስገንዘቡ ነዉ ብለዋል።

ኮሚሽነሯ አክለዉም በዓሉን ስናከብር እንደልማድ ብቻ ሣይሆን ዓላማው ገብቶን የትግሉ ተጋሪና የሰላ ትግል ማድረግ ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር አጋርነታቸውን ላሳዩ ለተለያዩ መዋቅሮች የዕዉቅና ሽልማት የመስጠት ሥነሥርዓት መካሄዱ ተገልጿል።

ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ "ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ለመገንባት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረዉን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በክልሉ በተለያዩ ተቋማትና መዋቅሮች ከህዳር 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ተገልጿል።

የበዓሉ ማጠቃለያ በኮሚሽኑ አዘጋጂነት በምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን መቀመጫ በሆነችዉ በንሣ ዳዬ ከተማ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በርካታ ወጣቶች በተገኙበት በክልሉ ማርሽ ባንድ ከዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ ቅስቀሳና ድጋፍ በታገዘ ሁኔታ በተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ በሆኑ ድራማ፣ ጭውውትና በባለድርሻ አካላት ፓናል ዉይይት መከበሩ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319