ወጣቶች ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል ለሀገረ ግንባታ በትጋት እንዲሰሩ የሀረሪ ክልል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአለም አቀፍ ጀረጃ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀንን በማስመልከት የውይይት መድረክ መካሄዱ ተገልጿል።
በሀረሪ ክልል 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ለማክበር ዝግጆቶች መደረጋቸውን የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑም በዓሉ አከባበር በተያዙ ኹነቶች ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሒዷል።
በመድረኩ የሀረሪ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አዳል ሙላቱ እንደገለፁት ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል ለሀገር ግንባታ በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሙስና ዓለም አቀፍ ወንጀል መኾኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ማኅበረሠቡ ተገንዝቦ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ እንዲሆንም ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል።
በክልሉ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር መታቀዱን ገልፀው፥ ለአብነትም የተማሪዎች ጥያቄና መልስ፣ ከወጣት ሊጎች ጋር የውይይት መድረክ፣ የሀብት ምዝገባ ስራና የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለህብረተሰቡ ለመስጠት መታቀዱን ገልፀዋል ።
በሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ የሃይማኖት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ ተቋማትና የሲቪክ ማኅበራት ህብረተሰቡ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የዘንድሮው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሀሳብ ለ21ኛ ግዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን ለመከላከል ወጣቶች ላይ መስራት የተሻለ ውጤት ያመጣል ተባለ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞች 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡
በውይይቱ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ተወካይ አቶ ታረቀኝ ወዲ ቀደም ባሉ በርካታ ዓመታት ሙስናን ለመታገል ብዙ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ባለመምጣቱ በተለየ ሁኔታ ወጣቶች ላይ መስራት የተለየ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የዘድሮውን የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።