Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ሙስናን በመከላከል እና ህግን በማስከበር ዙሪያ የትስስር እና የቅንጅት አሰራርን ሊያጠናክር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ተፈራረመ

**************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን በመከላከል እና ህግን በማስከበር ዙሪያ የትስስር እና የቅንጅት አሰራርን ሊያጠናክር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ሥነስርዓቱ የተገኙት የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) ኮሚሽኑ ትውልዱን በሥነምግባር በማነፅና ሙስናን በመከላከል ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት መረጃና መስረጃን መሰረት በማድረግ ሙሰኞችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የዛሬው ስምምነት በሁለቱ ተቋማት ነባር የሥራ ትስስሮች ቢኖሩም በቀጣይ በሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ሥራ ላይ አጠናክሮ ለመቀጠል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአጭር ጊዜ ወስጥ እንደሀገር የሚያኮራ የዘመነ ተቋም እየገነባ መሆኑን ተናግረው፣ የመግባቢያ ስምምነቱ የሙስና ወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራን ዕውቀትና ብቃትን መሠረት ባደረገ መልኩ ለመስራት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ከሀገራዊ ሪፎርሙ በኃላ የመንግስት ተቋማት በጋራ ተቀራርበው እና ተቀናጅተው የመስራት ባህል በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የሙስና ወንጀልን ለመከላከል በሁለቱ ተቋማት የበለፀገውን ቴክኖሎጂ በጋራ አስተሳስሮ በመጠቀም የሚቀርቡ የሙስና መዝገቦች ላይ ጠንካራ ምርመራ በማድረግ ጠርተው ለአቃቢ ሕግ እንዲቀርቡ ስምምነቱ ትልቅ እድል ይፈጥራልም ብለዋል፡፡

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀልን በመከላከልና ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረስብ እንዲፈጠር በሀገራችን እየተደረገ ያለውን ርብርብ በማገዝ ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባለሙያዎችን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በማሰልጠንና የተለያዩ ምርምርና ጥናቶችን በማካሄድ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
መንግስትና ፓርቲ ያቀዷቸው ትላልቅ የልማት ህልሞች እንዲሳኩ በጽናትና በመርህ ሙስናን መከላከል ይገባል - ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው መንግስትና ፓርቲ ያቀዷቸው ትላልቅ ህልሞች እንዲሳኩ የተጠናከረ የፀረ-ሙስና ትግል መደረግ እንዳለበት አሳሰቡ።

ክቡር ፕሬዚዳንቱ ቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የፀረ-ሙስና ቀን በዓል ላይ እንዳስታወቁት፣ ሙስና የብዙ አገሮችን ህልምና ትልም ያመከነና ለብዙ ቀውሶች መንስኤ ሆኗል።

ለሙስና ምክንያት ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከልም የመልካም አስተዳደር መጓደል፣ አላግባብ የመጠቀም ፍላጎት፣ ስልጣንን ለማቆየትና ወደስልጣን ለመውጣት ያሉ ፍላጎቶች እንደሆኑም አንስተዋል።

የሙስና መገለጫ ከሆኑት መካከልም ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ አሰራሮችን መጣስ፣ በቀጥታ ጥቅም ማግኘት፣ የፍትሀዊነት መጓደል፣ ፍትህን ማጣመም፣ የመንግስትን ጥቅም አሳልፎ መስጠት እና የመሳሰሉ ጉዳዮች እንዳሉም ርዕሰ መስተዳደሩ አብራርተዋል።

አገራችን ላይ አሁን ከሚታዩ ችግሮች ከ50 እስከ 60 ከመቶ የሚሆኑት ዋነኛ ምንጫቸው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች እንደሆኑም አመልክተዋል።

ሙስናን በወሳኝ መልኩ ለመከላከል በመርህ ላይ የተመሰረተ ትግል ማድረግ፣ ጽናት፣ የጋራ መግባባት፣ ህብረተሰብን በየደረጃው ማሳተፍ ቁልፍ ተግባራት መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው አሳስበዋል።

የህዝቡ እርካታ እስኪረጋገጥ የፀረ-ሙስና ትግሉን ማጠናከር፣ ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤትና የሀይማኖት ተቋማት አካባቢ በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ ለመቅረጽ ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በጉዳዩ ላይ መግባባትና ሀሳቡን ተግባራዊ ማድረግ፣ በቂ ትግል ማድረግ፣ ተቀናጅቶ መስራት፣በየሴክተሩ የፀረ-ሙስና ትግል ማጠናከር፣ ህግን ተግባራዊ ማድረግ፣ ከህዝቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለቅሞ መመለስ ዋነኛ የፀረ-ሙስና ትግሉ አጀንዳዎች መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው አሳውቀዋል።

ኮሚሽኑ በእጁ የሚገኙ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ ቶሎ ወደስራ እንዲገባም አሳስበው ስራዎች በሚዲያ እየታጀቡ መሄድ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ በበኩላቸው የፀረ-ሙስና ቀን የመከበሩ ዋነኛ አላማ ሙስና እያስከተለ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመከላከል እና በዘርፉ የሚደረገውን ትግል ለማጠናከር ነው ብለዋል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ግንዛቤ በመፍጠር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሙስናን ችግር መቅረፍ እንደሚያስችልም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

በሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት ወጣቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ ተጎጂ ነው ያሉት ኮሚሽነር ማሞ የዘንድሮው የጸረ ሙስና ቀን ሲከበር የወጣቶችን ሥነምግባር እና ታማኝነትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

በክልሉ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚያስችል የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በመስራት የአሰራር ጥናቶችን ማካሄድ፣ ለሚቀርቡ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት ከመከላከል ያለፉ የሙስና ወንጀል ጉዳዮችን ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ማስተላለፍ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319