Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ሙስናን በመከላከል እና ህግን በማስከበር ዙሪያ የትስስር እና የቅንጅት አሰራርን ሊያጠናክር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ተፈራረመ

**************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን በመከላከል እና ህግን በማስከበር ዙሪያ የትስስር እና የቅንጅት አሰራርን ሊያጠናክር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ተፈራርሟል፡፡

በፊርማ ሥነስርዓቱ የተገኙት የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) ኮሚሽኑ ትውልዱን በሥነምግባር በማነፅና ሙስናን በመከላከል ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት መረጃና መስረጃን መሰረት በማድረግ ሙሰኞችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የዛሬው ስምምነት በሁለቱ ተቋማት ነባር የሥራ ትስስሮች ቢኖሩም በቀጣይ በሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ሥራ ላይ አጠናክሮ ለመቀጠል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአጭር ጊዜ ወስጥ እንደሀገር የሚያኮራ የዘመነ ተቋም እየገነባ መሆኑን ተናግረው፣ የመግባቢያ ስምምነቱ የሙስና ወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራን ዕውቀትና ብቃትን መሠረት ባደረገ መልኩ ለመስራት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው በመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ከሀገራዊ ሪፎርሙ በኃላ የመንግስት ተቋማት በጋራ ተቀራርበው እና ተቀናጅተው የመስራት ባህል በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የሙስና ወንጀልን ለመከላከል በሁለቱ ተቋማት የበለፀገውን ቴክኖሎጂ በጋራ አስተሳስሮ በመጠቀም የሚቀርቡ የሙስና መዝገቦች ላይ ጠንካራ ምርመራ በማድረግ ጠርተው ለአቃቢ ሕግ እንዲቀርቡ ስምምነቱ ትልቅ እድል ይፈጥራልም ብለዋል፡፡

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀልን በመከላከልና ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረስብ እንዲፈጠር በሀገራችን እየተደረገ ያለውን ርብርብ በማገዝ ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ባለሙያዎችን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በማሰልጠንና የተለያዩ ምርምርና ጥናቶችን በማካሄድ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319