Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ለፍትህ ዘርፍ መካከለኛ አመራሮች የሙስና መከላከል እና ሥነምግባር ግንባታ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት መካከለኛ አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከያ ስልቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡

በስልጠናዉ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፈቃዱ ሰቦቃ ማስልጠኛ ሞጅሉ በ2016 በጀት አመት የተደረገን የሙስና ስጋት ዳሰሳዊ ጥናት ግኝትን መነሻ አድርጎ የብልሹ አሰራር መገለጫዎችና ምልክቶቹን በማየት መከላከያ ስልቶቹ ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

በተለይም ተቋማት ተኮር ችግሮችን ለመፍታት በየዘርፎቹ ሞጁሎች መዘጋጀታቸዉንም ተቁመዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አያይዘዉም ህዳር ወር አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን የሚከበርበት ወር በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ መዘጋጀቱን ጠቁመው፣ አመራሩ በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከያ ስልቶችን በመለየት ሰራተኞቹን የማነፅ፣ የመገንባትና ብልሹ አሰራር ክፍተቶችን እየለየና እየደፈነ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡርኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) በበኩላቸው በስልጠናዉ ተካፋይ የሆኑ አመራሮች ብልሹ አሰራርና ሙስና የሚያስከትለዉን አደጋ በመገንዘብ ወደተቋማቸዉ ሲመለሱ ሰራተኞቻቸዉን በማሰልጠን ዉጤታማ፣ ግልፅና አሳታፊ ስርዓትን እዉን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ዉጤታማና የተሳካ ስልጠና እንዲሆን በመመኘት ስልጠናዉን በጋራ ላዘጋጁት የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፣ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ለፀረ-ሙስና ፎረም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

የስልጠናዉ ዋና አላማ የፍትህ ዘርፍ እንደማንኛዉም ተቋም ለሙስና ተጋላጭ መሆኑን ተረድቶ በዘርፉ የሚፈፀመዉ ሙስና በዜጎችና በሀገር ላይ የሚያደርሰዉን ከፍተኛ ጉዳት በመገንዘብ በተቋሙ የሚከናወነዉን የስራ ሂደት ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ለማድረግ የራሳቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የሙስና ወንጀል ምንነትና አይነቶች፣ በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራር መከላከያ ስልቶች ላይ መግባባት ላይ መድረስ የሚሉ ይዘቶች ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319