Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት ክልላዊ የፀረ-ሙስና ቀን ማጠቃለያ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሔደ ነው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ሙስናን ለመዋጋት ወጣቱን ባለቤት ማድረግ ፣ ነገን መገንባት!" በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በቡታጅራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319