Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.9K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
በጋምቤላ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በጋምቤላ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን የፀረ-ሙስና ቀን በማስመልከት "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል! የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በክልሉ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በሥነ-ምግባር ላይ ትኩረት ያደረገ ትምህርት እና ቅስቀሳ ከህዳር 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዳይሬክተር በኩል በቀረበ ሰነድ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ሥነ-ምግባር ተኮር የማሰልጠኛ ሞጁል ተማሪዎች በሥነ-ምግባር የታነፁ፣ መልካም ስዕብናን የተላበሱ መምህራኖቻቸውን፣ ወላጆቻቸውን፣ ታላላቆቻቸውንና አረጋዊያንን በማክበር እንዲታዘዙ፥ የፈተና ኩረጃን እንዲጠየፉ፣ በሥነምግባራቸው ለሌሎች አርዓያ እንዲሆኑ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በትውልድ ላይ መሥራት በይደር የማይታለፍ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም አካላት ለነገው ትውልድ ምን አስተዋፅኦ ላድርግ ብለው ራሳቸውን መጠየቅ፣ ማዘጋጀት እና ማብቃት እንዳለባቸው መጠቆሙን ከኮሚሸኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት ክልላዊ የፀረ-ሙስና ቀን ማጠቃለያ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሔደ ነው

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 26/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ "ሙስናን ለመዋጋት ወጣቱን ባለቤት ማድረግ ፣ ነገን መገንባት!" በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በቡታጅራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319