Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር ይቻላል - የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር እንደሚቻል የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ ገልፀዋል፡፡

የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከኮምበልቻ ከተማ አስስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ጋር በመተባበር አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአራት መቶ በላይ ሃብት አስመዝጋቢዎችን ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ መዋቅራዊ ሌብነት አደገኛ መሆኑን ገልፀው፣ አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ሌሎችን ሳያስቡ ሃብት ማግበስበስ ብቻ ለመኖር ዋስትና አለመሆኑንና በንጽህና ህዝብን ማገልገል በምድርም ሆነ በፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሃብት ምዝገባ ባለሙያ አቶ አህመድ ይመር የምዝገባው አላማ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የጥቅም ግጭት ማስወገድ ነው ብለዋል፡፡

ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአራት መቶ በላይ በመምሪያዎች እና በተጠሪ ጽ/ቤቶች ስር ያሉ ተሻሚዎች፣ ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሃብታቸውን ማስመዝገባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ እና ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በጋራ አከበሩ

******************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ እና ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ቃል በጋራ አክብረዋል፡፡

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ማህዲያ አልበሽር እንደተናገሩት ሙስና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው በመተባበር መንፈስ መታገልና መከላከል አለባቸው ብለዋል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሀሰን እንደገለፁት ሙስና አደገኛ ወንጀል በመሆኑ ልንፀየፈውና እስከመጨረሻው ልንታገለው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ ወ/ሮ በድሬ እስማኤል በበኩላቸው ውጤታማ አስተዳደርና ፍትሐዊ የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሙስና እንቅፋት በመሆኑ ሠራተኞች ሙስናን መከላከልና መጸየፍ እንዳለባቸው ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ አመላክተዋል፡፡

ሙስና ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን የሚያስከትል በመሆኑ በተቀናጀ መልኩ በመከላከልና በመቆጣጠር ፍትሐዊነትን ማስፈን ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመካላከል የአመራሩና የሠራተኛው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሰገንዝበዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
በክልሉ 21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ሰብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እየተከበረ ይገኛል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሀረሪ ክልል 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በማስመልከት በክልሉ በሚገኘዉ በራስ መኮንን ትምህርት ቤት ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በጥያቄና መልስ ዉድድር መከበሩ ተገልጿል።

በዉድድሩም አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮች የማበረታቻ ሽልማት መስጠታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም የበዓሉ አከባበር በተለያዩ ዝግጅቶች በሌሎች ትምህርት ቤቶች እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319