አገር የምታድገው በሚሰሩ ንፁህ እጆች ነው - ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር)
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አገር የምታድገው በሚሰሩ ንፁህ እጆች መሆኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች “ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት!” በሚል መሪ ቃል በንግድ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር) በንግድ ዘርፍ ያለውን ብልሹ አሰራር ከራስ በመጀመርና መልካም ሥነምግባርን ማዕከል በማድረግ ተግቶ በመስራት፣ ከአገልጋይነት፣ ከወገንተኝነት፣ ከጥቅመኝነት፣ ከአድሎ የጸዳ እና ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ አገለግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የተሻለ እውቀት ይዞ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተቀናጅቶ መስራት እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነትን በመፍጠር የተሻለ ውጤት ማምጣት አስፈላጊ በመሆኑ በንግዱ ዘርፍ የሚታየው የብልሹ አሰራር ችግር ህዝብን በመጉዳት የምንፈልገውን እድገት እንዳናመጣ የሚያደርግ ወንጀል መሆኑን ተናግረዋል።
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው መልካም ሥነምግባርን በመላበስ ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ የሁሉም ዜጋ ግዴታ እንደሆነ ገልፀዋል።
እንደ ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ዘርፍ ኢ-ሥነምግባራዊ አመራር ቢኖር ውጤቱ ማህበረሰብን እና ሀገርን ሊያናጋ የሚችል ስለሆነ ህዝብን፣ መንግስትንና ዜጋን የማገልገል ኃላፊነት አለብን ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ሁላችንም ከተጠያቂነት እና ከችግሩ ለመራቅ ኃላፊነታችንን በመወጣት ከስልጠናው ብዙ ትምህርት ወስዳችሁ ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ስልጠናው በዶ/ር መኮንን ቦጋለ እና በዶ/ር አወቀ አሸናፊ እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ወጣቶች ሙስና እና ብልሹ አሰራር በከተማዋ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመቀነስ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን 21ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል፡፡
በክብረ በዓሉ ወቅት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ጋትዌች ቱት ባስተላለፉት መልዕክት የሰለጠነ ህሊና እና አመለካከት ሲኖረን ሙስናን መከላከል እንችላለን ብለዋል፡፡
አቶ ጋትዌች አክለውም ሁላችንም በምንሰጠው አገልግሎት ውስጥ ስለ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በቂ ግንዛቤ በመያዝ የምንሰጠውን አገልግሎት ከእጅ መንሻ የጸዳ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የባለስልጣኑ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ተሾመ ወጣቶችን ያማከለ የበለፀገች የኢትዮያን ለማየት እያንዳንዱ ሰው አስተዋጽኦ በማበርከት የሀገር እድገት ጸር የሆነውን ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ሀገራችን ወደፊት አንድ እርምጃ ማስቀደም አለብን ብለዋል፡፡
የባስልጣኑ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ መስፍን ደገፉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል ለማክበር የተዘጋጀ መነሻ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣቶች ሙስና እና ብልሹ አሰራር በከተማዋ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በመቀነስ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻልና የፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ ዋና አላማ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም የጥያቄና መልስ ውድድር የተከናወነ ሲሆን፥ በውድድሩ ለተሳተፉ ሰራተኞችም ሽልማት ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ መበርከቱን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሌላ አካል ይዞታን በሀሰተኛ ሰነድ በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ የተደራደረው አትሌት በ3 ዓመት ከ4 ወር እስራት ተቀጣ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሌላ አካል ይዞታን በሀሰተኛ ሰነድ በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ በመደራደር የተከሰሰው አትሌት ድሪባ መርጋ በ3 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወሰነ።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ 1ኛ አትሌት ድሪባ መርጋ እና 2ኛ በግል ስራ የሚተዳደሩት ወ/ሮ መንበረ አበበ ገብረጻዲቅ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸዋል።
በዚህም በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስ ቀርቦበታል።
ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነውንና በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 08 ስር የሚገኘውን 4 ሺህ 972 ካሬ ሜትር ይዞታን በመጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሚመለከተው ተቋም እንደተሰጠ በማስመሰል ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሶስተኛ ወገን ለሽያጭ ማቅረቡን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።
በተጨማሪም ተከሳሹ በውል ቁጥር 2036/2012 ዓ.ም ደግሞ በውል ሰጭ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ እና በውል ተቀባይ ናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል የተፈረ በማስመሰል የተዘጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተሰጠ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኮድ ቁጥር 2929/2929/2015 የሊዝ ውልን በማሻሻል እንደላከ በማስመሰል የተጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል ለሽያጭ አቅርቧል።
በተጨማሪም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ውክልና ባልሰጠችበት ሁኔታ ላይ በህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ1ኛ ተከሳሽ ይዞታውን በሽያጭ እስከ ማስተላለፍ ድረስ እንዲያስተዳድር ውክልና እንደሰጠች ተደርጎ የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ ማቅረቡ በክሱ ላይ ተመላክቷል።
1ኛ ተከሳሽ በታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በይዞታው ላይ የተጠቀሱ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማቅረብ ይዞታውን በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ ሲደራደር የመያዙን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።
ሁለተኛ ክስ ላይ ደግሞ ከዚህ በፊት እስኪያዝ ድረስ ለጊዜው ክሱ በተቋረጠለት ማለትም ስዩም አሰፋ ወንድማገኝ በተባለ ግለሰብ ላይ የቀረበ ክስ ነበር።
ይኸውም ክስ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል የሚል ነው።
በዚህም 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስበው በ1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በሆነው እና በስራ አስኪያጅነት የሚተዳደረው ናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞታ ላይ ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ ካርታ፣ የሊዝ ውልና የውክልና ሰነድ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ቀርቦባቸዋል።
3ኛ ክስ ደግሞ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 390 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን መተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል።
በዚህም በታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው አረንጓዴ ሰፈር ተብሎ ከሚታወቀው ቦታ አካባቢ በሚገኘው የስራ ቦታዋ ውስጥ በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት በተደረገ ብርበራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በልደታ ክ/ከ ትምህርትና ስልጠና ጽ/ቤት የዕውቀት ለህብረት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ካርድ እና በትምህርት ሚኒስቴር አባይ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ውጤት መግለጫ ካርድ የተገኘባት በመሆኑ የሐሰት ስራ ለመፈጸም የሚያገለግሉ መሳርያዎችና መስርያዎች ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሳለች።
በዚህ መልኩ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የቀረበባቸው ክስ ዝርዝር በችሎት እንዲደርሳቸው የተደረገ እና ክሱን በንባብ እንዲሰሙ ተደርጓል።
3ኛ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 1 በሌለበት ሊታይ የማይችል በመሆኑ ምክንያት እስኪያዝ ድረስ ለጊዜው ክሱ እዲቋረጥ ተደርጓል።
ከዚህም በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የእምነት ክህደት ቃል በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ሲሆን ተከሳሾቹ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ 1ኛ ተከሳሽ አትሌት ድሪባ መርጋን በ3 ዓመት ከ4 ወራት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ሁለተኛ ተከሳሽን በሚመለከት የጤና እክል እንዳለባት፣ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኗንና ሌሎች ያቀረበችውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በ2 ዓመት ከ9 ወራት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የተጣለው ቅጣት እንዲገደብ አድርጓል።

አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር ይቻላል - የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ
******************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር እንደሚቻል የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ ገልፀዋል፡፡
የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከኮምበልቻ ከተማ አስስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ጋር በመተባበር አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአራት መቶ በላይ ሃብት አስመዝጋቢዎችን ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል፡፡
የኮምበልቻ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አቢ መዋቅራዊ ሌብነት አደገኛ መሆኑን ገልፀው፣ አገልጋይ የሆነው የመንግስት መዋቅር ሙስናን ከታገለ በተወሰነ መልኩ ችግሩን መሻገር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ሌሎችን ሳያስቡ ሃብት ማግበስበስ ብቻ ለመኖር ዋስትና አለመሆኑንና በንጽህና ህዝብን ማገልገል በምድርም ሆነ በፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሃብት ምዝገባ ባለሙያ አቶ አህመድ ይመር የምዝገባው አላማ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የጥቅም ግጭት ማስወገድ ነው ብለዋል፡፡
ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአራት መቶ በላይ በመምሪያዎች እና በተጠሪ ጽ/ቤቶች ስር ያሉ ተሻሚዎች፣ ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሃብታቸውን ማስመዝገባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡