Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.88K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ነው

*******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራር፣ ዳኞችና ሰራተኞች በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የፀረ-ሙስና ቀን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!” በሚል መሪ ቃል በድምቀት መከበሩ ተገልጿል።

የዉይይት መድረኩን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሠንበታ ቀጀላ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ነጅመዲን አልማሃዲ በጋራ መርተውታል።

በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሠንበታ ቀጀላ ሙስና እድገትን የሚያቀጭጭ በህዝቦች መካከል መተማመንን የሚሸረሽር እኩይ ተግባር ነው ብለዋል።

ይህንን እኩይ ተግባር አምርሮ መታገል እንደሚገባ አስታዉሰዉ፥ በተለይም በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ እና ሙስናን የሚፀየፍ ትዉልድ ማፍራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዉይይቱ ላይም የፀረ-ሙስና ቀንን አስመልክቶ የመስሪያቤቱ የሥነ-ምግባር መከታተያ ባለሙያ ወ/ሪት ሰሚራ ኡስማን ሠነድ አቅርበው ዉይይት መደረጉን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በዉይይቱ ሙስና የመንግስትን ሥራን ሥነምግባራዊ እና ህጋዊ መሠረት ባለዉ መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ ማከናወን አለመቻል የሚፈጠር የሞራል ዝቅጠት፣ የመልካም አስተዳደር ጉድለት፣ ስግብግብነት፣ ራስወዳድነት እና በአቋራጭ የመበልፀግ አባዜ ሲሆን፣ የሀገርን ዕድገት የሚገታ መርዛማ በሽታ በመሆኑ በጋራ መከላከል እንደሚገባ መነሳቱ ተገልጿል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር የመንግስትን የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና፣ ታማኝነት እና ፍትሃዊነትን በእጅጉ የሚጎዳ፣ የዕድገት ነቀርሳ መሆኑን በመገንዘብ የመንግስት ሠራተኞች እና አመራሮች እነዚህን ተግዳሮቶች በመዋጋትና በመታገል አገልግሎቶችን ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ይገባልም ተብሏል።

የዉይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት አንዱ የሙስና አይነት የመንግስት ስራ ሰዓት አለማክበርና አድሎዊ አሰራር በመሆኑ ሁሉም ሠራተኞች በአግባቡ የመንግስት ስራ ሰዓት በማክበር በተመደቡበት ሙያ ፍትሃዊ አገልግሎት ለማህብረሰቡ መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
አገር የምታድገው በሚሰሩ ንፁህ እጆች ነው - ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር)

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 25/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አገር የምታድገው በሚሰሩ ንፁህ እጆች መሆኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች “ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት!” በሚል መሪ ቃል በንግድ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች መከላከያ ስልቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱላኪም ሙሉ (ዶ/ር) በንግድ ዘርፍ ያለውን ብልሹ አሰራር ከራስ በመጀመርና መልካም ሥነምግባርን ማዕከል በማድረግ ተግቶ በመስራት፣ ከአገልጋይነት፣ ከወገንተኝነት፣ ከጥቅመኝነት፣ ከአድሎ የጸዳ እና ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ አገለግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የተሻለ እውቀት ይዞ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተቀናጅቶ መስራት እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነትን በመፍጠር የተሻለ ውጤት ማምጣት አስፈላጊ በመሆኑ በንግዱ ዘርፍ የሚታየው የብልሹ አሰራር ችግር ህዝብን በመጉዳት የምንፈልገውን እድገት እንዳናመጣ የሚያደርግ ወንጀል መሆኑን ተናግረዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው መልካም ሥነምግባርን በመላበስ ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ የሁሉም ዜጋ ግዴታ እንደሆነ ገልፀዋል።

እንደ ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ዘርፍ ኢ-ሥነምግባራዊ አመራር ቢኖር ውጤቱ ማህበረሰብን እና ሀገርን ሊያናጋ የሚችል ስለሆነ ህዝብን፣ መንግስትንና ዜጋን የማገልገል ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም ሁላችንም ከተጠያቂነት እና ከችግሩ ለመራቅ ኃላፊነታችንን በመወጣት ከስልጠናው ብዙ ትምህርት ወስዳችሁ ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ስልጠናው በዶ/ር መኮንን ቦጋለ እና በዶ/ር አወቀ አሸናፊ እየተሰጠ ሲሆን፥ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319