ት/ቤቶች 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አክብረዋል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ከመርሀ ጥበብ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት በተለያዩ ሁነቶች አክብረዋል።
በዓሉ በተማሪዎች መካከል በጥያቄና መልስ ውድድር፣ በድራማና ሥነፅሁፍ እንዲሁም በባህላዊ ጭፈራዎች በማወዳደር በደማቅ ሁኔታ የተከበረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውድድሩም የተሻለ ውጤት በማምጣት አሸናፊ ለሆኑትና ከ1-4ኛ ደረጃ ለወጡት ተማሪዎች እና ለበዓሉ መሳካት አስተዋፅኦ ለአበረከቱ መምህራን በደሴ ከተማ አስስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ ሰይድ እሸቱ የመጽሐፍት እና ሰርትፍኬት ሽልማት የተበረከተ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሀሳብ 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዷል።
በዚሁ መርሀ-ግብር በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ሙስናን አውቆ የሚታገል ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ሀገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች ላይ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ፌኑስ አክለውም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የትውልድ ስብእና ግንባታ ላይ ያላቸው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑን አውቀው በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸውም ገልፀዋል።
በቀጣይም አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበር መገለፁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።