በምክር ቤት ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው ሰዒድ አሊን ጨምሮ 8 ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ምክር ቤት ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው የልደታ ክ/ከተማ የቀድሞ ዋና ስራ አፈጸሚ አቶ ሰዒድ አሊን ጨምሮ ስምንት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበባቸው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ በተከሳሾቹ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣(ለ) እና ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ በሚል ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸዋል።
ክሱ የቀረበባቸው 1ኛ የልደታ ክ/ከተማ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰይድ አሊ፣ 2ኛ በክ/ከተማው ወረዳ 04 ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ደበላ ዳባ፣ 3ኛ በክ/ከተማው ወረዳ 04 መንግስት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አንድነት አብዩ፣4ኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፣ 5ኛ በንግድ ስራ የሚተዳደረው ሀጂ በገን ኸይሩን ጨምሮ አምስት የመንግስት ሰራተኞች እና ሶስት በግል ስራ የሚተዳደሩ በአጠቃላይ ስምንት ግለሰቦች ናቸው።
በዚህም 1ኛ ክስ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን፤ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች እንደቅደም ተከተላቸው ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ በግል ስራ ከሚተዳደረው ከ5ኛ ተከሳሽ ጋር መመሳጠር የሚል ይገኝበታል።
በተለይም ከጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክ/ከተማው ውስጥ ከሜክሲኮ እስከ ቄራ ባለው ዋና መንገድ ማስፋፊያ የኮሪደር ልማት ጥናት መሰረት የሚሰራውን ፕሮጀክት ሽፋን በማድረግ በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 ሳልቫቶሬ ዴቪታ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ግለሰቦች ተከራይተው የሚገኙትን የቀበሌ ቤቶችን አፍርሰው ይዞታውን የ5ኛ ተከሳሽ ንብረት ለሆነው ዋይልድ አፓርትመንት ለተባለ ህንፃ መጠቀሚያ እንዲሆን ማመቻቸት የሚል በክሱ ይገኝበታል።
በዚህም ከኮሪደር ልማት መስመር ውጪ የሚገኙ ስድስት የመኖሪያ ቤቶች በውስጣቸዉ ግለሰቦች እየኖሩበት እና ንግድ እየተከናወነበት እያለና የከተማዉ ካቢኔ ቤቶቹ እንዲፈርሱ ባልወሰነበት፤ እንዲሁም ፕላን ፎርማት እና የካቢኔ ውሳኔ ባልተያያዘበት ሁኔታ 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ቤቶቹ በፍጥነት እንዲፈርሱ ለወረዳ አመራር ለሆኑት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችና ለሌሎችም ያለ አግባብ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ህገ-ወጥ ትዕዛዝ በመቀበል ቤቶቹ እንዲፈርሱ በቃለ ጉባኤ በመወያየት በሁለት ቀን ውስጥ ቤቶቹን ለማፍረስ የሚያስፈልገዉን የማፍረሻ ግምት በተመለከተም ለ4ኛ ተከሳሽ የማፍረሻ ግምት በሚል በግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፎ በመስጠት ቤቶቹ እንዲፈርሱ በማድረግ እንዲሁም በቤቶቹ ነዋሪ ለሆኑ ተነሺዎችም ያለአግባብ በተለያዩ ሳይቶች ምትክ ቤቶች እንዲያገኙ አድርገዋል የሚል ይገኝበታል።
መፍረስ የሌለባቸውን 6 የመኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት በማፍረስ የመንግስት ቤቶቹ ውስጥ በኪራይ ይኖሩ ለነበሩት ግለሰቦች አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 3 ሚሊየን 383 ሺህ 202 ብር ከ77 ሳንቲም 6 የጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም እንዲሰጣቸው በማድረግ የሚል በክሱ ተካቷል።
እንዲሁም ቤቶቹ የፈረሱበት የቦታ ስፋቱ 503 ካሬ ሜትር ቦታ በህገ ወጥ መልኩ ለ5ኛ ተከሳሽ ንብረት ለሆነ ህንፃ አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ 1ኛ ተከሳሽ በአካል ቦታዉ ለይ በመገኘት “ተፈቅዶለታል እንዳትከለክሉት ያልማ” በሚል በቃል ለሁለት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ለሆኑ ባለሙያዎች ትዕዛዝ መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል።
1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ሊፈርሱ ማይገባቸዉ የመንግስት ቤቶች ያለአግባብ እንዲፈርሱ ትዕዛዝ በመስጠትና 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ይህንን ህገ-ወጥ ትዕዛዝ ተቀብለው ቤቶችን በማስፈረስ እና ለ5ኛ ተከሳሽ ምቹ በማድረግ ህገ-ወጥ ግንባታ እንዲገነባ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በመፍቀድ፣ 5ኛ ተከሳሽም በዚሁ ይዞታ ላይ ወይም ቤቶቹ በፈረሱበት ቦታ ላይ ያለአግባብ ህገ-ወጥ ግንባታ እና ማስፋፊያ ስራ መስራቱ በክስ ዝርዝር ላይ ተመላክቷል።
በተለይም ለተነሺዎች ያለአግባብ የመንግስት ጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) እንዲሰጣቸዉ በማድረግ፤ ተከራዮች ያለአግባብ ቤታቸው እንዲፈርስ በማድረግ በመንግስት ላይም የሊዝ ዋጋን ጨምሮ ብር 4 ሚሊየን 362 ሺህ 986ብር ከ89 የሚገመት ጉዳት ያደረሱ መሆናቸዉ በክሱ የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተገለፁት ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት እንዲሁም 5ኛ ተከሳሽ በልዩ ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በ2ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ላይ 1ኛ ክስ በተጠቀሰው መልኩ 6 ሚሊየን ብር ምንጩ እንዳይታወቅ እንዲሁም ወንጀል ፈፃሚው ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጥ ለማድረግ ገንዘቡን በባንክ ሂሳባቸው ያስቀመጡ እንዲሁም ያስተላለፉ መሆናቸው ተጠቅሶ ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በወንጀል የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል።
ክሱ ለተከሳሾች የደረሰ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በክሱ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም መቀጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ወጣቶች ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል ለሀገረ ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲያከናውናቸው በሕግ ከተሰጠው ተግባር ውስጥ የሥነምግባር ግንባታ፣ የተቋም የአሠራር ሥርዓት ጥናት፣ የሃብት ምዝገባ እና ማጣራት ሥራዎች ይገኙበታል።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተከሰተው የሰላም ችግር ምክንያት በተቋማቱ የታዩ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመፍታት የለውጥ ሥራዎች መጀመራቸውን የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ገልጸዋል።
የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በክልሉ በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በሙሉ አቅም ለመተግበር አሁንም ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ መኾኑን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
ከሚከናወኑት ሥራዎች መካከል ደግሞ የፀረ-ሙስና ቀን አንዱ ሲኾን፥ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት 21ኛው የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን እስከ ኅዳር/2017 ዓ.ም መጨረሻ የሚቆይ የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድም ነው ያስገነዘቡት።
በመርሐ ግብሩ "ሥነምግባር የተሞላበት አገልግሎት አሠጣጥ፣ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በመከላከል የመንግሥት ተቋማት መሪዎች እና የባለሙያው ሚና" በሚል በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይቶች ይካሄዳሉ ብለዋል።
የመንግሥት ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች የሃብት ምዝገባ ሥራ እንደሚሠራም አስረድተዋል። የስፖርታዊ ውድድሮች፣ የጽዳት ዘመቻ እና ሌሎች ሥራዎችም እንደሚከናወኑ ነው ያብራሩት።
ሙስና ዓለም አቀፍ ወንጀል መኾኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ማኅበረሠቡ ተገንዝቦ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ እንዲኾንም ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል።
"ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" የሚለውን ተገቢ ያልኾነ አባባል በመጸየፍ "ሲሾም ያልሠራ ሲሻር ይቆጨዋል" የሚለውን እሳቤ ባሕል ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል።
በሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ የሃይማኖት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በተለይም ደግሞ ወጣቶች በሥነምግባር ተገዥ ኾነው ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የሀገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበር ተገለፀ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሀሳብ 21ኛውን የአለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበር የአስተዳደሩ የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በህዳር ወር ለተከታታይ ቀናት በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ቀደም ተብሎ መከበር መጀመሩን ኮሚሽነሩ ተናግረው፥ በኮሚሽኑ አስተባባሪነትም በሁሉም የመንግስት ሴክተር ተቋማት፣ በከተማ፣ ወረዳዎችና የገጠር ክላስተሮች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
የዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን በተለይም ወጣቶች ላይ ትኩረት ማድረጉ ሙስና በሀገር እድገት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለነገ ሀገር ተረካቢዎች በቂ ግንዛቤ ይዘው እንዲያድጉ እንደሚያስችል አቶ ፌኑስ ተናግረዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ላይም በተለያዩ ደረጃዎች የተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁበት፣ የአሰራር ስርዓቱን ጠብቆ በታነፁ ሙያተኞች ሰፊ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ማስታወቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ያሳተፈ የጥያቄና መልስ ውድድርም ከማካሄዱም በላይ በሙስና ምንነት፣ ባህሪያት፣ ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የተሰሩ አሁናዊ፣ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች፣ በፀረ-ሙስና ትግል ላይ የዜጎች ሚና እና ኃላፊነት ዙሪያ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚካሄድም ገልፀዋል።

ት/ቤቶች 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አክብረዋል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ከመርሀ ጥበብ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት በተለያዩ ሁነቶች አክብረዋል።
በዓሉ በተማሪዎች መካከል በጥያቄና መልስ ውድድር፣ በድራማና ሥነፅሁፍ እንዲሁም በባህላዊ ጭፈራዎች በማወዳደር በደማቅ ሁኔታ የተከበረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውድድሩም የተሻለ ውጤት በማምጣት አሸናፊ ለሆኑትና ከ1-4ኛ ደረጃ ለወጡት ተማሪዎች እና ለበዓሉ መሳካት አስተዋፅኦ ለአበረከቱ መምህራን በደሴ ከተማ አስስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ ሰይድ እሸቱ የመጽሐፍት እና ሰርትፍኬት ሽልማት የተበረከተ መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ ሀሳብ 21ኛውን አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዷል።
በዚሁ መርሀ-ግብር በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ሙስናን አውቆ የሚታገል ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ሀገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች ላይ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ፌኑስ አክለውም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የትውልድ ስብእና ግንባታ ላይ ያላቸው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑን አውቀው በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸውም ገልፀዋል።
በቀጣይም አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበር መገለፁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።