ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ ነው - ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ስለሺ ግርማ ገልፀዋል።
ለቱሪዝም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና በዶ/ር ምህረተአብ አብርሃም እየተሰጠ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ስለሺ ግርማ ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ በመሆኑ በሥነምግባራዊ አመራርነት ጎልቶ ሊታይ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ሙስና በጣም ፈታኝ የሆነበት ጊዜ እንደመሆኑ በቱሪዝሙ ዘርፍ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት አንፃር ሀገሪቷ ማግኘት ያለባትን ገቢ ሊያሳጣ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በጥናት በመደገፍ ዘርፍ ተኮር የስልጠና ሞጁል በማዘጋጀትና የመከላከያ ስልቶች በመለየት በዘርፎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው ለኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና ለኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች በቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች መከላከያ ስልቶች ላይ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319

ሙስና ሀገርን እና ዜጎችን የሚጎዳ የህዝብ ጠላት ድንበር ዘለል ወንጀል በመሆኑ በጋራ መታገል ይገባል
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።
አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀኑን አስመልክቶ የከንቲባ ጽ/ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ አዱኛ ሙስና አገርን እና ዜጎችን የሚጎዳ የህዝብ ጠላትና ድንበር ዘለል ወንጀል በመሆኑ በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል።
የከንቲባ ጽ/ቤት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ዳንደና ሙሰኝነት ከሥነ-ምግባር ውድቀት እና ከሞራል ዝቅጠት የሚመነጭ ዜጎችን ለረሃብ፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለስደት የሚዳርግ አደገኛ ወንጀል በመሆኑ ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት በመፍጠር ልንከላከለው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር የሺጥላ መንግስቴ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ በፕሮግራሙ ላይ ግንባር ቀደም የሆኑና ሰናይ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሰራተኞች በጽ/ቤቱ የዘርፍ ሃላፊዎች ተመርጠው በጥያቄና መልስ ውድድር በማሳተፍ ከአንድ እስከ አምስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሞባይል ሽልማት መሰጠቱ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኮሚሽኑ የ2017 ዓ.ም አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበረ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሥራተኞች "ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕናን ለመገንባት!" በሚል መሪ ቃል 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በዓሉን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ ዘላለም ለማ ሙስና ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በተለይ በወጣቱ ላይ እያደረሰ ያለዉ ተፅዕኖና አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቱን በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ በማሣተፍ ድርሻውን እንዲወጣና ከሙስና ተፅዕኖ ራሱን መከላከል እንዲችል ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።
በመድረኩ ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ለመገንባት! የሚል ሰነድ በኮሚሽኑ ሥልጠና ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወኔ ሀመሶ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ ከመድረኩ የተለያዩ ምላሾችና አቅጣጫዎች መቀመጡን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ የይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ መረጃ በማጉደል፣ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል እና ጉቦ በመቀበል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት የይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ የሆነው አሸብር አበባው ታደሰ የተባለ ግለሰብ ሆን ብሎ መረጃ በማጉደል፣ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል እና ጉቦ በመቀበል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የወ/ሮ ሙሉ ካህሺን ሕጋዊ ወኪል የሆኑት አቶ ደራራ ዲንሳ ኢረና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚገኝ የቦታ ይዞታቸው በመሬት ይዞታ ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲረጋገጥላቸው ለአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት አመልክተው፤ ተጠርጣሪው የማይገባ ጥቅም በመፈለግ ከአመልካች ማኅደር ላይ መረጃ በማጉደል እና ጉዳያቸውን በማጓተት ሲያጉላላቸው ከቆየ በኋላ መረጃውን አሟልቶ ወደሚመለከተው አካል ለመላክ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር ጉቦ መጠየቁን የምርመራ ቡድን ደርሶበታል፡፡
ባለጉዳዩ አቶ ደራራ ዲንሳ የተጠየቁትን ገንዘብ በአዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01320082310801 ወደ ተጠርጣሪው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000218526121 ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ያስገቡ መሆናቸውን ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለምርመራ ቡድኑ ጥቆማ አቅርበው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል፡፡
የምርመራ ቡድኑ የተጠርጣሪውን የእምነት ክህደት ቃል በመቀበል፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ10 ቀን የምርመራ ማጣሪያ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መፍቀዱ ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በምክር ቤት ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው ሰዒድ አሊን ጨምሮ 8 ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበ
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዲስ አበባ ምክር ቤት ያለመከሰስ መብቱ የተነሳው የልደታ ክ/ከተማ የቀድሞ ዋና ስራ አፈጸሚ አቶ ሰዒድ አሊን ጨምሮ ስምንት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበባቸው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ በተከሳሾቹ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ)፣ አንቀጽ 33 እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ)፣(ለ) እና ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ በሚል ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸዋል።
ክሱ የቀረበባቸው 1ኛ የልደታ ክ/ከተማ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰይድ አሊ፣ 2ኛ በክ/ከተማው ወረዳ 04 ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ደበላ ዳባ፣ 3ኛ በክ/ከተማው ወረዳ 04 መንግስት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አንድነት አብዩ፣4ኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ ቴዎድሮስ ፀጋዬ፣ 5ኛ በንግድ ስራ የሚተዳደረው ሀጂ በገን ኸይሩን ጨምሮ አምስት የመንግስት ሰራተኞች እና ሶስት በግል ስራ የሚተዳደሩ በአጠቃላይ ስምንት ግለሰቦች ናቸው።
በዚህም 1ኛ ክስ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን፤ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች እንደቅደም ተከተላቸው ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ በግል ስራ ከሚተዳደረው ከ5ኛ ተከሳሽ ጋር መመሳጠር የሚል ይገኝበታል።
በተለይም ከጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክ/ከተማው ውስጥ ከሜክሲኮ እስከ ቄራ ባለው ዋና መንገድ ማስፋፊያ የኮሪደር ልማት ጥናት መሰረት የሚሰራውን ፕሮጀክት ሽፋን በማድረግ በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 ሳልቫቶሬ ዴቪታ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ግለሰቦች ተከራይተው የሚገኙትን የቀበሌ ቤቶችን አፍርሰው ይዞታውን የ5ኛ ተከሳሽ ንብረት ለሆነው ዋይልድ አፓርትመንት ለተባለ ህንፃ መጠቀሚያ እንዲሆን ማመቻቸት የሚል በክሱ ይገኝበታል።
በዚህም ከኮሪደር ልማት መስመር ውጪ የሚገኙ ስድስት የመኖሪያ ቤቶች በውስጣቸዉ ግለሰቦች እየኖሩበት እና ንግድ እየተከናወነበት እያለና የከተማዉ ካቢኔ ቤቶቹ እንዲፈርሱ ባልወሰነበት፤ እንዲሁም ፕላን ፎርማት እና የካቢኔ ውሳኔ ባልተያያዘበት ሁኔታ 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ቤቶቹ በፍጥነት እንዲፈርሱ ለወረዳ አመራር ለሆኑት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችና ለሌሎችም ያለ አግባብ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ህገ-ወጥ ትዕዛዝ በመቀበል ቤቶቹ እንዲፈርሱ በቃለ ጉባኤ በመወያየት በሁለት ቀን ውስጥ ቤቶቹን ለማፍረስ የሚያስፈልገዉን የማፍረሻ ግምት በተመለከተም ለ4ኛ ተከሳሽ የማፍረሻ ግምት በሚል በግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፎ በመስጠት ቤቶቹ እንዲፈርሱ በማድረግ እንዲሁም በቤቶቹ ነዋሪ ለሆኑ ተነሺዎችም ያለአግባብ በተለያዩ ሳይቶች ምትክ ቤቶች እንዲያገኙ አድርገዋል የሚል ይገኝበታል።
መፍረስ የሌለባቸውን 6 የመኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት በማፍረስ የመንግስት ቤቶቹ ውስጥ በኪራይ ይኖሩ ለነበሩት ግለሰቦች አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 3 ሚሊየን 383 ሺህ 202 ብር ከ77 ሳንቲም 6 የጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየም እንዲሰጣቸው በማድረግ የሚል በክሱ ተካቷል።
እንዲሁም ቤቶቹ የፈረሱበት የቦታ ስፋቱ 503 ካሬ ሜትር ቦታ በህገ ወጥ መልኩ ለ5ኛ ተከሳሽ ንብረት ለሆነ ህንፃ አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ 1ኛ ተከሳሽ በአካል ቦታዉ ለይ በመገኘት “ተፈቅዶለታል እንዳትከለክሉት ያልማ” በሚል በቃል ለሁለት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ለሆኑ ባለሙያዎች ትዕዛዝ መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል።
1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ሊፈርሱ ማይገባቸዉ የመንግስት ቤቶች ያለአግባብ እንዲፈርሱ ትዕዛዝ በመስጠትና 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ይህንን ህገ-ወጥ ትዕዛዝ ተቀብለው ቤቶችን በማስፈረስ እና ለ5ኛ ተከሳሽ ምቹ በማድረግ ህገ-ወጥ ግንባታ እንዲገነባ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በመፍቀድ፣ 5ኛ ተከሳሽም በዚሁ ይዞታ ላይ ወይም ቤቶቹ በፈረሱበት ቦታ ላይ ያለአግባብ ህገ-ወጥ ግንባታ እና ማስፋፊያ ስራ መስራቱ በክስ ዝርዝር ላይ ተመላክቷል።
በተለይም ለተነሺዎች ያለአግባብ የመንግስት ጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) እንዲሰጣቸዉ በማድረግ፤ ተከራዮች ያለአግባብ ቤታቸው እንዲፈርስ በማድረግ በመንግስት ላይም የሊዝ ዋጋን ጨምሮ ብር 4 ሚሊየን 362 ሺህ 986ብር ከ89 የሚገመት ጉዳት ያደረሱ መሆናቸዉ በክሱ የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተገለፁት ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት እንዲሁም 5ኛ ተከሳሽ በልዩ ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በ2ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ላይ 1ኛ ክስ በተጠቀሰው መልኩ 6 ሚሊየን ብር ምንጩ እንዳይታወቅ እንዲሁም ወንጀል ፈፃሚው ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጥ ለማድረግ ገንዘቡን በባንክ ሂሳባቸው ያስቀመጡ እንዲሁም ያስተላለፉ መሆናቸው ተጠቅሶ ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በወንጀል የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል።
ክሱ ለተከሳሾች የደረሰ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በክሱ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም መቀጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ወጣቶች ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል ለሀገረ ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲያከናውናቸው በሕግ ከተሰጠው ተግባር ውስጥ የሥነምግባር ግንባታ፣ የተቋም የአሠራር ሥርዓት ጥናት፣ የሃብት ምዝገባ እና ማጣራት ሥራዎች ይገኙበታል።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተከሰተው የሰላም ችግር ምክንያት በተቋማቱ የታዩ ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመፍታት የለውጥ ሥራዎች መጀመራቸውን የአማራ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ገልጸዋል።
የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን በክልሉ በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በሙሉ አቅም ለመተግበር አሁንም ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ መኾኑን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
ከሚከናወኑት ሥራዎች መካከል ደግሞ የፀረ-ሙስና ቀን አንዱ ሲኾን፥ "ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል!" በሚል መሪ መልዕክት 21ኛው የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን እስከ ኅዳር/2017 ዓ.ም መጨረሻ የሚቆይ የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድም ነው ያስገነዘቡት።
በመርሐ ግብሩ "ሥነምግባር የተሞላበት አገልግሎት አሠጣጥ፣ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን በመከላከል የመንግሥት ተቋማት መሪዎች እና የባለሙያው ሚና" በሚል በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይቶች ይካሄዳሉ ብለዋል።
የመንግሥት ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች የሃብት ምዝገባ ሥራ እንደሚሠራም አስረድተዋል። የስፖርታዊ ውድድሮች፣ የጽዳት ዘመቻ እና ሌሎች ሥራዎችም እንደሚከናወኑ ነው ያብራሩት።
ሙስና ዓለም አቀፍ ወንጀል መኾኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ማኅበረሠቡ ተገንዝቦ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥ እንዲኾንም ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል።
"ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" የሚለውን ተገቢ ያልኾነ አባባል በመጸየፍ "ሲሾም ያልሠራ ሲሻር ይቆጨዋል" የሚለውን እሳቤ ባሕል ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል።
በሥነምግባር ግንባታ እና በፀረ-ሙስና ትግሉ የሃይማኖት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በተለይም ደግሞ ወጣቶች በሥነምግባር ተገዥ ኾነው ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን በመታገል የሀገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።