Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.87K subscribers
10.4K photos
245 videos
32 files
3.05K links
Download Telegram
ለፀረ-ሙስና ትግሉ የሁሉም ማህበረሰብ አስተዋፅኦ ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 23/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለ21ኛ ግዜ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የክፍለ ከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የኪነ-ጥበብ እና የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም በጎ-ፈቃደኛ የሚዲያ አንቂዎች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በፓናል ውይይቱም የሙስና ምንነት፣ ባህሪያት፣ ሙስናን ለመከላከል የተሰሩ አሁናዊ፣ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች፣ በፀረ-ሙስና ትግል ላይ የዜጎች ሚና እና ኃላፊነት ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ የተገኙት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ቦጋለች ተድላ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ የክፍለ ከተማው አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል፣ የብልሹ አሰራር እና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ ባለው ስራ ሚናችሁ ከፍተኛ ነው፥ የፀረ-ሙስና ትግሉ ላይም ይህንን አስተዋፅኦ ማስቀጠል እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሃመድ የኃማኖት አባቶች ትውልድን በሥነምግባር ከመቅረፅ ባሻገር ህብረተሰቡ ሌብነትን እንዲጠየፍ በየኃይማኖት አስተምሮዎቻቸው የሚሰጡትን ትምህርት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የክፍለ ከተማው የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና መከታታያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ ስንታየሁ ወዳጆ በፀረ-ሙስና ትግሉ ሁሉም የማህበረሰብ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የበዓሉን የውይይት መድረክ የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን፣ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም፣ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤቶች በጋራ ማዘጋጀታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቷል የተባለውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገለፀ

*****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 23/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) አቶ በህረዲን ጀማል የተባለው ግለሰብ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረው አንድን ግለሰብ “ሁሉንም ነገር እኔ አስጨርሼ ወደ ዱባይ እልክሃለሁ” ብሎ ከ297 ሺህ በር በላይ እንደተቀበለው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

ጉዳይህ አልቆልሃል ተብሎ ከተጠርጣሪው የጉዞ ሰነድ የተሰጠው የግል ተበዳይም ወደ ዱባይ ለመሄድ ቦሌ አለምዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተገኘበት ወቅት ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑ እንደተገለፀለትና ከአየር መንገድ እንደተመለሰ ፖሊስ መምሪያው ጠቅሷል።

የግል ተበዳይን አቤቱታ የተቀበለው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር አውሎ የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ብርበራ ሀሰተኛ ሰነዶችና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምበትን ኮምፒውተር በኤግዚቢትነት ተይዞ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ተብሏል።

በተጠርጣሪው ተመሳሳይ የማታለል ወንጀል ተፈፅሞብናል የሚሉ ግለሰቦች ወደ ክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ተጨማሪ መረጃ መስጠት እንደሚችሉ መገለፁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።


#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ ነው - ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ስለሺ ግርማ ገልፀዋል።

ለቱሪዝም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች "ሥነምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ዘርፍ ተኮር የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና በዶ/ር ምህረተአብ አብርሃም እየተሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ስለሺ ግርማ ከሙስና የፀዳ ሀገራዊ መስተንግዶ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ በመሆኑ በሥነምግባራዊ አመራርነት ጎልቶ ሊታይ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ሙስና በጣም ፈታኝ የሆነበት ጊዜ እንደመሆኑ በቱሪዝሙ ዘርፍ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት አንፃር ሀገሪቷ ማግኘት ያለባትን ገቢ ሊያሳጣ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በጥናት በመደገፍ ዘርፍ ተኮር የስልጠና ሞጁል በማዘጋጀትና የመከላከያ ስልቶች በመለየት በዘርፎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው ለኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና ለኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች በቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ የሙስና እና ብልሹ አሰራሮች መከላከያ ስልቶች ላይ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ሙስና ሀገርን እና ዜጎችን የሚጎዳ የህዝብ ጠላት ድንበር ዘለል ወንጀል በመሆኑ በጋራ መታገል ይገባል

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች 21ኛው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።

አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀኑን አስመልክቶ የከንቲባ ጽ/ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ አዱኛ ሙስና አገርን እና ዜጎችን የሚጎዳ የህዝብ ጠላትና ድንበር ዘለል ወንጀል በመሆኑ በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል።

የከንቲባ ጽ/ቤት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ዳንደና ሙሰኝነት ከሥነ-ምግባር ውድቀት እና ከሞራል ዝቅጠት የሚመነጭ ዜጎችን ለረሃብ፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለስደት የሚዳርግ አደገኛ ወንጀል በመሆኑ ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት በመፍጠር ልንከላከለው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር የሺጥላ መንግስቴ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፥ በፕሮግራሙ ላይ ግንባር ቀደም የሆኑና ሰናይ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሰራተኞች በጽ/ቤቱ የዘርፍ ሃላፊዎች ተመርጠው በጥያቄና መልስ ውድድር በማሳተፍ ከአንድ እስከ አምስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሞባይል ሽልማት መሰጠቱ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
ኮሚሽኑ የ2017 ዓ.ም አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበረ

******

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ህዳር 24/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሲዳማ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሥራተኞች "ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕናን ለመገንባት!" በሚል መሪ ቃል 21ኛውን ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በዓሉን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ ዘላለም ለማ ሙስና ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በተለይ በወጣቱ ላይ እያደረሰ ያለዉ ተፅዕኖና አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቱን በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ በማሣተፍ ድርሻውን እንዲወጣና ከሙስና ተፅዕኖ ራሱን መከላከል እንዲችል ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።

በመድረኩ ወጣቱን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ለመገንባት! የሚል ሰነድ በኮሚሽኑ ሥልጠና ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወኔ ሀመሶ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ ከመድረኩ የተለያዩ ምላሾችና አቅጣጫዎች መቀመጡን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319