Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ለ25 ዘርፎች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች፣ ለኮሚሽኑ ዓላማ ፈፃሚ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እየተሰጠ ያለው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም አዳማ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለ25 ዘርፎችና ለተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች፣ ለኮሚሽኑ ዓላማ ፈፃሚ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየሰጠ ያለው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ይገኛል።

የዕለቱ ስልጠና በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ገዛኸኝ ጋሻው እየተሰጠ ሲሆን፥ በሙስና ወንጀል ሕጎች ምንነትና አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ስልጠናዉ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን፥ በሃብት ምዝገባና ማሳወቅ አዋጅ እና በዋና ዋና ኮሚሽኑ በሚተገብራቸው ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት አድርጎ በኮሚሽኑ ዓላማ ፈጻሚ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ተባለ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ፡፡

ድርጊቱን የፈፀሙት የኮሚሽኑ ሠራተኞችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ የኢሚግሬሽን፣ የጉምሩክ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ነው ያሉት፡፡

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መሰል ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ነው የገለፁት።

አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተው፥ በቅርቡ የአዳዲስ አውሮፕላኖች ግዥ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡