Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.4K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ኮሚሽኑ ለ25 ዘርፎችና ለተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች፣ ለኮሚሽኑ ዓላማ ፈፃሚ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም አዳማ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለ25 ዘርፎችና ለተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎችና ባለሙያዎች፣ ለኮሚሽኑ ዓላማ ፈፃሚ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ወዶ አጦ እንደገለፁት የአቅም ግንባታ ስልጠናው የተሻላ ግንዛቤ የምናገኝበትና ለተልኳችን አቅም የምንወስድበት ነዉ ብለዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም የሥነምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ተግባራትን ለማከናወን ከዘርፍ ተቋማት ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር ወጥ የሆነ የአንድ እቅድ፣ የአንድ ሪፖርት አሰራርን በመከተል የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።

የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው ሥልጠናዉ መንግሥት የጀመረዉን አገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል በንቅናዌ መልክ መምራት እንዲያስችል ለማድረግ ያለመ መሆኑን በመገንዘብ፥ የስልጠና ተሳታፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ሥልጠናው አለምዓቀፍ የፀረ-ሙስና ህጎችን በተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት ተግባራዊነታቸውን ለመከታተል የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት ህብረተሰቡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የእጅ መንሻ እየሰጠ መቀጠል የለበትም ያሉት ም/ኮምሽነሩ፥ በተሰማራችሁበት የሥራ ዘርፍ ህብረተሰቡ ለብልሹ አሰራር እንዳይጋለጥ የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት ይኖርባችኃል ብለዋል።

ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ሀረጎት አብርሃ እየተሰጠ ሲሆን፥ የአለምዓቀፍ እና አህጉራዊ የፀረ-ሙስና ሥምምነቶች አፈፃፀም በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስልና አተገባበራቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ስልጠናዉ ለቀጣይ አራት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፥ በሙስና ወንጀል ሕጎች እና በሃብት ምዝገባና ማሳወቅ አዋጅ እንዲሁም በዋና ዋና ኮሚሽኑ በሚተገብራቸው ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት አድርጎ በኮሚሽኑ የዓላማ ፈጻሚ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚሰጥ ይሆናል። በስልጠናው ከ700 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች እየተሳተፋ ይገኛል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡