Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በትምህርት ተቋማት የተደራጀ የግብረ ገብነትና ፀረ-ሙስና ክበባትን የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የግብረ-ገብና ፀረ-ሙስና ክበባት አደረጃጀትና የሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ለክበባቱ አስፈፃሚዎች ስልጠና መስጠቱን ገልጿል።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ እንደገለፁት በትምህርት ተቋማት የተደራጀ የግብረ-ገብነትና ፀረ-ሙስና ክበባትን በማጠናከር ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም የክበባት አስፈፃሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት ከልብ እንዲወጡ አሳስበው፥ የኮሚሽኑ ድጋፍም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዳ/ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ በበኩላቸው በሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት አደረጃጀትና የሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል። ኮሚሽኑ ካሉት ዓላማዎች አንዱ የትውልድ ሥነምግባርና የሞራል እሴቶችን መገንባት በመሆኑ የሞራልና ሥነምግባር ግንባታ ዋነኛ ማዕከል በሆነው ትምህርት ቤት ክበባትን የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ አቶ ጀንበሩ ተናግረዋል።

በስልጠናው ታማኝነት፣ ፍታዊነት፣ ሰላማዊነት፣ ገለልተኛነት፣ እራስን መግዛት፣ ሀቀኝነት፣ ታታሪነት፣ የሀገር ፍቅር፣ ለህዝብ ንብረት ተቆርቋሪነት እና የቡድን መንፈስ መላበስ ተማሪዎች ሊያጎለብቷቸው የሚገቡ እሴቶች መሆናቸው መጠቀሱን ከኮሚሽኑ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በስልጠናው የተሳተፉ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት አመራር መምህራንና ተማሪዎች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት የትምህርት ጥራትና ሥነምግባርን ለማሻሻል ወሳኝ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ስልጠናው ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ከባለፈው ሳምንት በቀጠለው ስልጠና አቃቂ ቃሊቲ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ክበባት አስፈፃሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡