Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የንግድ ሥርዓቱን ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት ብልሹ አሰራርን በማስቀረት አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል - አቶ ገብረመስቀል ጫላ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት የዘርፉ አሰራር በማቀላጠፍና ብልሹ አሰራርን በማስቀረት አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ዓበይት ተግባራትን አስምልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ካለበት ቦታ ሆኖ በተንቀሳቃሽ ስልኩ የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድና የግብር ከፋይ ማረጋገጫ አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል። አሰራሩም ጉቦ፣ ምልጃና ብልሹ አሰራሮችን ማስቀረት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባሻገርም ለኢትዮጵዊያን ብቻ ክፍት የነበረውን የንግድ ምህዳር በነፃ የንግድ መርህ የውጭ ባለሃብቶች የሚሳተፉበትን ዕድል በመፍጠር የንግድ ሥርዓቱን እያዘመነ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም በጥናት ላይ በመመስረት ከ3 ሺህ 300 በላይ የደላላ የንግድ ፈቃድ በመሰረዝ ህብረተሰቡ በዕለት የሚጠቀማቸው የምርት አይነቶች ቀጥታ ለገበያ እንዲቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በንግድ ሥርዓቱ ላይ ሳንካ ሲፈጥሩ በነበሩ ደላሎች ላይ የንግድ ፈቃድ እግድ መደረጉም ምርትና አገልግሎትን ለሸማቹ በቀጥታ እንዲቀርብ ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የህገ-ወጥ ደላላ እንቅስቃሴን ከመሰረቱ ማጥፋት ባይቻልም የምርት ፍላጎትና አቅርቦቱን ለማጣጣም በሚደረጉ ጥረቶች የህብረተሰቡ እገዛ አይተኬ ነው ብለዋል።

የህገ-ወጥ ደላሎችን እንቅስቃሴ ለመግታትም ከወረዳ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የሸማቾች ጥበቃ ማህበር በማቋቋም ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ማህበሩም በግንዛቤ ፈጠራና ህገ-ወጥ ቁጥጥር ላይ ህብረሰተቡን በማስገንዘብ ውጤታማ ተግባር መሥራት እንደሚያስችል አንስተዋል።

ህብረተሰቡም በህገ-ወጥ ቁጥጥር ላይ በነፃ የስልክ ጥሪ ጭምር የራሱን ገንቢ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። ጎን ለጎንም የንግዱንና የሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚሳድጉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው ብለዋል።

የንግዱ ማህበረሰብም ለተገልጋዮቻቸው የዋጋ ዝርዝር በማሳወቅ ለሕጋዊ የንግድ ሥርዓት መጎልበት የራሳቸውን አዎንታዊ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 205 ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 205 ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

የደንበኞችን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ህትመት መከናወኑንም ነው አገልግሎቱ የገለጸው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የአገልግሎቱን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ባለፋት ስድስት ወራት 205 ከውጭ አገር ደላሎች ጋር ተመሳጥረው በህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከስራ እስከማባረር የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸውና ባልተፈቀደላቸው ስራ ላይ የተሰማሩ ከ10 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ምርመራ በማድረግ እንደ ጥፋት መጠናቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል። ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ሰነድ አሟልተው እንዲመዘገቡ መደረጉንም አገልግሎቱ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እና በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እና በመገልገል እንዲሁም በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ነጋሽ አሕመድ ረሺድ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው፥ ፖሊስ ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በቀጥታ የቀረበ ክስን መሠረት በማድረግ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 8 በሚገኙ የቢሮ ቁጥር 211 እና 104 ባደረገው ብርበራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሀሰተኛ ማሕተሞች፣ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የቀበሌ መታወቂያዎች፣ በተለያዩ ተቋማት የተፃፉ የሚመስሉ የስራ ልምዶች፣ እንዲሁም ይጠቀሙባቸው የነበሩ መሳሪያዎችን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ሀሰተኛ ሰነዶች በቢሮዎቹ ተከማችተው መገኘታቸው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ተጠርጣሪው ከሌሎች ግብረ-አበሮቹ ጋር በጥቅም በመመሳጠር፣ ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ፍቃድ ሳይሰጠው በተለያዩ ድርጅቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ኮሌጅ እና በሌሎች ከ80 በላይ በሚሆኑ ድርጅቶች ስም ማህተም እና ቲተር በማስቀረፅ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ መቆየቱ ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር ስም ታድሷል የሚል ቲተርና ማህተም በማስቀረፅ እንዲሁም ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት፣ የተለያዩ የኦዲት ሪፖርቶችን በመስራት በሀሰተኛ ማህተም እያረጋገጠ በመስጠት በሕዝብ እና በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የተፈፀመው ወንጀል ውስብስብና ምርመራው ሰፊ መሆኑን ጠቅሶ፥ በወንጀል መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀፅ 2 መሠረት የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከፍርድ ቤት ለማስፈቀድ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ጽፎ የፍርድ ቤቱን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚህ ግለሰብ ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ መጠየቁን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የመንግስት ተቋማት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ሊያደረጉ ይገባል - አቶ ደግፌ ኩድን

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደግፌ ኩድን ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ሚዛን ቅርንጫፍ ኤፍ ኤም 104.5 ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት የመንግስት ተቋማት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ሊያደረጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሁለት ዓመት ተኩል የፓርቲና የመንግስትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ገምግሞ ጥንካሬና ጉድለቶችን ለይቶ በቀጣይ ዕቅድ ውስጥ አካቶ ለመሥራት ወሳኝ በመሆኑ የሁሉም ትኩረትን እንደሚሻ የመንግስት ዋና ተጠሪው ተናግረዋል።

የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው ከኪራይ ሰብሳቢነትና ከእጅ መንሻ በፀዳ መልኩ ከማገልገል እንዲሁም ሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ተቋማትን ተደራሽ በማደረግ በኩል አመራሩ ተቀናጅቶ ግድፈቶችን ለማረም በዕቅድ ተካቶ እንደሚሰራ መግለፃቸውን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ ግለሰቦች ላይ የተላለፈ ውሳኔ

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኤጀንሲው የመንግሥት የግዥ ሥርዓትን ከሌብነት የጸዳና ውጤታማ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለፀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሲዳማ ክልል የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ ሥርዓትን ለመተግበር አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እየተሟሉ መሆኑን የክልሉ የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ቴፎ ለኢዜአ እንደገለጹት ኤጀንሲው የመንግሥት የግዥ ሥርዓትን ከሌብነት የጸዳና ውጤታማ ለማድረግ እየሰራ ነው።

ከክልሉ በጀት ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው ለግዥ እንደሚውል ጠቁመው፣ በጀቱ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት የግዥ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ለግዥ ሥርዓቱ ተግባራዊነት መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራ ከወዲሁ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ኤጀንሲው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

በተለይ ሂደቱን ለማፋጠን የመመሪያ፣ የህግ ማዕቀፍ እና አዋጅ የማሻሻል ሥራ ተከናውኖ በክልሉ ምክር ቤት ለማጸደቅ እየጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንዲሁም በሀገር ደረጃ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ሶፍትዌሩን ካበለጸገው ድርጅት ጋር ውል በመፈራረም አስፈላጊው መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል የሶፍትዌር ማበልፀግ እና የኔትዎርክ ዝርጋታ ሥራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የኤሌክትሮኒክ ግዥ አሰራር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ በመንግስት ግዥ ስርዓት ውስጥ ግልጽነትና ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን እንደሚያስቀር ተናግረዋል።

ይህም የግዥ ሥርዓትን አሳታፊና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ መፍትሄ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይ የወረቀት ጨረታንና የጥቅም ትስስርን ለማስቆም ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

የቅድመ ዝግጅት ስራውን ፈጥኖ በማጠናቀቅ ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ በዘጠኝ የክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት በሙከራ ደረጃ ይጀመራል።

በሙከራ ደረጃ የግዥ ሥርዓቱ ከሚተገበርባቸው ተቋማት መካከል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት እና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ይገኙበታል። ለእዚህም ለተለያዩ መስሪያ ቤቶች ባለሙያዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና መሰጠቱን ነው የጠቆሙት።

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ከፍተኛ የግዢ ባለሙያ አቶ ዘሪሁን አሰፋ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓቱ ተግባራዊ ሲደረግ በግዥ ስርዓቱ ላይ እየታዩ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ያስተካክላል።

እስካሁን ሲሰራበት የቆየው የማንዋል ግዥ አድካሚ፣ ብዙ ጊዜ የሚጠይቅ፣ ግልጽነት የጎደለው፣ ለሙስና የተጋለጠ እና የተደራሽነት ችግር ያለበት መሆኑን አስረድተዋል።

የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት የግዥ ሥርዓቱ ይህንን ችግር ሙሉ ለሙሉ ከማስወገድ ባለፈ የግዥ ስርዓቱን ወጤታማ እንደሚያደርግ መናገራቸውን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በመልካም ሥነምግባር የታነጸ ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል!