Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የክልሉ ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016 ጨምሮ የቀረቡለትን 5 አዋጆች እና 1 ደንብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016 ጨምሮ የቀረቡለትን 5 አዋጆች እና 1 ደንብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የክልሉ ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 32/2016፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ ቁጥር 33/2016፣ የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ስልጣንና ተግባሩን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 35/2016 እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ኦዲት ሪፖርት በመስራት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለተለያዩ ድርጅቶች ዓመታዊ ሀሰተኛ ኦዲት ሪፖርት በመስራትና ሀሰተኛ ሰነዶችን አዘጋጅተው በመጠቀም ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ ነጋሽ አህመድ እረሽድ፣ ቅድስት ሙሉጌታና ናርዶስ ብርሃኑ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋለው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሲሆን÷ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

በተለይም ነጋሽ አህመድ እረሽድ በተባለው ተጠርጣሪ ላይ በተሰራው ኦፕሬሽን ስራ ግለሰቡ ‘የሂሳብ አዋቂ ነኝ’ በማለት ብቻ ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ፍቃድ ሳያገኝ በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 2 እና ወረዳ 8 ስር ቢሮ በመክፈት የተለያዩ ድርጅቶች ዓመታዊ ኦዲት ሪፖርት በመስራትና ለገቢዎች ቢሮ እንዲቀርብ በማድረግ በህዝብና በመንግስታዊ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ሙስና ወንጀል መጠርጠሩን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጠርጣሪው የስራ ቦታ በተደረገ ብርበራ በንብ ባንክ፣ በንግድና በኮንስትራክሽን ባንክ በሚል የተዘጋጀ ሀሰተኛ 3 ጥራዝ ቼክ፣ ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዳይሬክተር በነበሩት በአቶ የማነ ደስታ ስም ቲተርና ማህተም በማዘጋጀት፣ ሀሰተኛ ኦዲቶች እንደታደሱ ተብለው የተዘጋጁ ሰነዶች፣ ከ60 በላይ የተለያዩ ድርጅቶች ስም የተቀረጹ ማህተሞችና ቲተሮች፣ የተለያዩ የስራ ልምዶች፣ የዩኒቨርሲቲና በኮሌጆች ስም የትምህርት ማስረጃዎች ጭምር እንደተገኙ ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።

ከተጠርጣሪው ጋር ሲሰሩ ነበር የተባሉ ግብረዓበሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አስታውቋል።

በተጨማሪም ቅድስት ሙሉጌታ የተባለች ተጠርጣሪን የሂሳብ ሰራተኛ ሆና የተለያዩ አመታዊ ኦዲቶች ለድርጅቶች በማድረስ ጭምር ተሳትፎ አላት በማለት መጠርጠሩን የገለጸው ፖሊስ፤ ናርዶስ ብርሃኑን በሚመለከት ደግሞ ለግል ድርጅት በሚል ኦዲት ሪፖርት በማሰራት ረገድ ተሳትፎ እንዳላት ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል የጣት አሻራ የማስነሳት ስራ ማከናወኑን የጠቀሰው መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ማለትም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የምስክርነት ቃል መቀበልና ቀሪ ማስረጃ የማቅረብ ስራ እንደሚቀረው ጠቅሶ፤ ከወንጀሉ ውስብስብነትና ከምርመራው ስፋት አንጻር ፍርድ ቤቱ ተገንዝቦ በወ/መ/ስ/ህ ቁጥር 59/2 መሰረት የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹም ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ እንደማይገባ ገልጸው የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው መጠየቃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን እና የፖሊስ ምርመራ መዝገብን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፖሊስ እንደሚያስፈልገው ከግምት ውስጥ በማስገባት የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሳውላ ከተማ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት ያሳዩ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ ተደረገ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የመንግስትን ህጋዊ አሰራር ባለመጠበቅ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብና የመንግስት ገንዘብ ጉድለት ያሳዩ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን የሳውላ ከተማ ገቢዎች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ የአሰራር ጉድለቶችን የማጥራት ሥራ እየሰራ የቆየ ሲሆን፥ በዚህም በኦዲት ሥራዎች ላይ የሰነድ ማበላለጥ፣ በተመሳሳይ ንምራ ቁጥር የተለያዩ የገቢ ርዕሶች እንዲሁም የገንዘብ መጠንና የከፋይ ስም በበራሪና በቀሪ ደረሰኝ ላይ አለመጣጣምና ማጭበርበር፣ ወደ ግል አካውንት ገንዘብ ማስገባት፣ ካርኒ አላግባቢ መቁረጥ ፣ ወጭ የሆኑ ደረሰኞችን ተመላሽ ያለማድረግ የተስተዋለ የአሰራር ችግሮች መሆኑን የሣውላ ከተማ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ኩማ ገልጸዋል። ።

በዚህ መነሻነት በሁለት ግለሰቦች የተስተዋለው የኦዲት ግኝት በጠቅላላው ስልሳ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺ ዘጠና አራት ብር ከስልሳ ዘጠኝ ሣንቲም ግኝት ሆኖ የተረጋገጠ ሲሆን ይህም ለህግ ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን አቶ ጌታሁን አስረድተዋል ።

ይህን ተከትሎ በውስጥም በውጭም የሚስተዋሉ ሌብነቶችን በአሰራር ትግል በማድረግ የማጥራት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው መረጃ በመስጠትና ደረሰኞችን በማቅረብ ትብብር ላደረጉ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

መንግሥት ሌብነትን በመታገል የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ ከፍፃሜ የሚያደርስ መሆኑን በመገንዘብ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር ያለምንም ስጋት እንዲከፍሉ ኃላፊው ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች በመንግስት የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዘርፎች የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄዱ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በመንግስት የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዘርፎች የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት በመንግስት የተከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም፣ የኢኮኖሚ ዘርፎች፣ የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ ልማት ዘርፎች አፈፃፀም እንዲሁም የአስተዳደር ዘርፎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

በቀረበው የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በሥራ ኃላፊዎችና በሰራተኞች ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ቀርበው በኮሚሽኑ የበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የንግድ ሥርዓቱን ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት ብልሹ አሰራርን በማስቀረት አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል - አቶ ገብረመስቀል ጫላ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት የዘርፉ አሰራር በማቀላጠፍና ብልሹ አሰራርን በማስቀረት አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ዓበይት ተግባራትን አስምልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ካለበት ቦታ ሆኖ በተንቀሳቃሽ ስልኩ የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድና የግብር ከፋይ ማረጋገጫ አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል። አሰራሩም ጉቦ፣ ምልጃና ብልሹ አሰራሮችን ማስቀረት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባሻገርም ለኢትዮጵዊያን ብቻ ክፍት የነበረውን የንግድ ምህዳር በነፃ የንግድ መርህ የውጭ ባለሃብቶች የሚሳተፉበትን ዕድል በመፍጠር የንግድ ሥርዓቱን እያዘመነ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም በጥናት ላይ በመመስረት ከ3 ሺህ 300 በላይ የደላላ የንግድ ፈቃድ በመሰረዝ ህብረተሰቡ በዕለት የሚጠቀማቸው የምርት አይነቶች ቀጥታ ለገበያ እንዲቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በንግድ ሥርዓቱ ላይ ሳንካ ሲፈጥሩ በነበሩ ደላሎች ላይ የንግድ ፈቃድ እግድ መደረጉም ምርትና አገልግሎትን ለሸማቹ በቀጥታ እንዲቀርብ ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የህገ-ወጥ ደላላ እንቅስቃሴን ከመሰረቱ ማጥፋት ባይቻልም የምርት ፍላጎትና አቅርቦቱን ለማጣጣም በሚደረጉ ጥረቶች የህብረተሰቡ እገዛ አይተኬ ነው ብለዋል።

የህገ-ወጥ ደላሎችን እንቅስቃሴ ለመግታትም ከወረዳ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የሸማቾች ጥበቃ ማህበር በማቋቋም ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ማህበሩም በግንዛቤ ፈጠራና ህገ-ወጥ ቁጥጥር ላይ ህብረሰተቡን በማስገንዘብ ውጤታማ ተግባር መሥራት እንደሚያስችል አንስተዋል።

ህብረተሰቡም በህገ-ወጥ ቁጥጥር ላይ በነፃ የስልክ ጥሪ ጭምር የራሱን ገንቢ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። ጎን ለጎንም የንግዱንና የሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚሳድጉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው ብለዋል።

የንግዱ ማህበረሰብም ለተገልጋዮቻቸው የዋጋ ዝርዝር በማሳወቅ ለሕጋዊ የንግድ ሥርዓት መጎልበት የራሳቸውን አዎንታዊ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡