Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ ፍትህን የሚያዛባ በመሆኑ በጋራ ልንከላከለው ይገባል

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ እና ፍትህን የሚያዛባ በመሆኑ አንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉም አካል በጋራ ሊከላከል እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን።

ኮሚሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄዷል።

የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ፣ ፍትህን የሚያዛባ፣ የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያስከትልና ዲሞክራሲ እውን እንዳይሆን ማነቆ ከሆኑ ጉዳዮች ዋነኛዉ እንደሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የህግ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ ንጉሴ ወ/ሚካኤል ተናግረዋል።

የሙስና ወንጀሉን በመከላከል እረገድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተደራጀ ትብብርና ቅንጅት የሚፈልግ እንደሆነ ተገልጿል።

ኮምሽኑና በየደረጃው ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በዋናነት ሙስና እና ብልሹ አሰራር የማይሸከም ህብረተሰብ በመፍጠርና የግንዛቤ ስራዎችን በማስፋት ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን በጥናት መዝጋት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በፍትህና ልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ግዥ እንደተናገሩት አስቸኳይ ሙስና መከላከል ተግባራትን በመስራት የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከብክነት ማዳን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ክልላዊ የልማት ግቦቻችንን ወደማያደናቅፍ ደረጃ ማድረስ ይኖርብናል ማለታቸውን ሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም ዘግቧል።

በኮሚሽኑና በየደረጃው ባሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የሚሰሩ የስራ አፈፃፀሞች ከጊዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች እንዳሉት በአፈፃፀም ግምገማው ላይ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስናን በጽናት በመታገል መልካም አስተዳደርን እናረጋግጥ!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግምታቸው ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ ቆርቆሮና ቶንዲኖ ብረቶች ተያዙ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሀሰተኛ የጉምሩክ ሰነድ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግምታቸው ከ56.5 ሚሊየን ብር ዋጋ የሚያወጡ ቆርቆሮና ቶንዲኖ ብረቶች ተይዘዋል፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ቀናት ባደረገው የቁጥጥር ስራ ግምቱ 40 ሚሊየን ብር የሚሆን ቆርቆሮ እንዲሁም ግምታዊ ዋጋው 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሆነ ቶንዲኖ ብረት በድሞሩ 56 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ቆርቆሮና ብረት በሀሰተኛ የጉምሩክ ሰነዶች ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሀሰተኛ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህን እቃዎች ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናውን ማድረሱን ከገቢዎች ሚኒስቴር የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለባህልና ስፖርት ዘርፍ ሠራተኞች በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሚኒስቴሩ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ክንፌ የስልጠናው ዓላማ ሙያተኛው የሙያ ሥነምግባርን ተላብሶ ለተገልጋዩ ቀልጣፋና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን የሚፀየፍና የሚከላከል ሙያተኛ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ በአቶ ኪዳነ ምህረት እና በአቶ ካሳነው ጤናው የተሰጠ ሲሆን፤ በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች እንዲሁም በግዥ ሂደት የሚፈጸም ሙስናን መከላከል ትኩረት ባደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ግብር በማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመስጠት ከ100 በላይ ግብር ከፋዮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን መምሪያው አስታወቀ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በተደረገው የህግ ማስከበር ሥራ ግብር በማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመስጠት ከ100 በላይ ግብር ከፋዮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቋል።

የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌቱ ታምሩ እንደተናገሩት መምሪያው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ኦፕሬሽን 6 ግብር ከፋዮች ግብር በማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመስጠት በህግ ቁጥጥር ሥር ውለው የምርመራ ሥራ እየተከውነ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተደረገው ድንገተኛ የታክስ ኦፕሬሽን በ107 ግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን ጠቁመው፣ ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የግብር ማጭበርበር ባደረጉ ግብር ከፋዮች ላይ በተደረገው የህግ ማስከበር ተግባር 1 ሚሊዮን 830 ሺህ 60 ብር ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ተደርጎል ነው ያሉት፡፡

የክትትልና ህግን የማስከበሩ ሥራ በዞኑ ዲላ፣ ይርጋጨፌ እና ገደብ ከተሞች ላይ መካሄዱን ገልጸው፣ ህብረተስቡ ግብር የሚሰውሩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ጥቆማ በመሰጠት የተጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በቅንጅት መሥራት ይጠበቅብናል ማለታቸውን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከኢንፔሪያልና ሪቨራል ሆቴል ግዢ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባሉ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከኢንፔሪያል እና ሪቨራል ሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ በ2011 ዓ.ም ከህግ ውጪ በተፈጸመ ኢንፔሪያል እና ሪቨራል በተባሉ ሁለት ሆቴሎች ግዢ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል በማለት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቧል።

ይህንን ተከትሎ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው በሰጡት የዕምነት ክህደት ቃል መነሻ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ የሰነድና የሰው ምስክሮችን በችሎት አቅርቦ አሰምቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ሜጀር ጀነራል ክንፈ በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ በተገቢው መከላከል አለመቻላቸውን ዛሬ ፍርድ ቤቱ ገልጾ፤ በወንጀል ህግ አንቀጽ 407 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ንዑስ ቁጥር 2 መሰረት የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

በተላለፈው የጥፋተኝነት ፍርድ በአንደኛው የሆቴል ግዢ በሙሉ ድምጽ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን፣ በሌላኛው የሆቴል ግዢ ክስ ደግሞ በአብላጫ ድምጽ በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት ጥፋተኛ ተብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን መርምሮ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለመጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከዚህ በፊት ከ111 የራዳር ግዢ ጋር ተያይዞ በ3 ዓመት ከ7 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በ4ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ውሳኔ መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።

በአሁን ወቅትም በሜጀር ጀነራል ክንፈ ላይ የመርከብ ግዢን ጨምሮ ሶስት ቀሪ የሙስና የክስ መዝገቦች በፍርድ ቤት በሂደት ላይ ይገኛሉ።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የክልሉ ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016 ጨምሮ የቀረቡለትን 5 አዋጆች እና 1 ደንብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016 ጨምሮ የቀረቡለትን 5 አዋጆች እና 1 ደንብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የክልሉ ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 32/2016፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ ቁጥር 33/2016፣ የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ስልጣንና ተግባሩን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 35/2016 እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ደንብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ደ.ሬ.ቴ.ድ ዘግቧል።