Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ከተቋማት የተደወለ በማስመሰል “የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ ነበሩ” ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከባንክ፣ ከኢትዮ-ቴሌኮም እና ከሌሎች ተቋማት የተደወለ በማስመሰል የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል ባላቸው 11 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን ጨምረ የክስ መዝገብ ለአቃቤ ህግ መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የማጭበርበር ወንጀሉን ሲፈጽሙ የነበሩት “በይቆጥቡ ይሸለሙ” የሎተሪ ገንዘብ እና ሌሎች ሽልማቶች “አሸንፈዋል” በሚል ማሳሳቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከግለሰቦች የባንክ አካውንት ገንዘብ ሲመዘብሩ የቆዩት “ሽልማቶቹን እንድታገኙ ሲቢኢ ዋሌት/CBE wallet / ክፈቱ“ ፣ “የሞባይል ባንኪንግ ኮዳችሁን ንገሩን“ እና “የምንልከውን ኮድ ያስገቡ“ በሚሉ ማጭበርበሪያዎች መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ 3 ወንድማማቾችን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ወንጀሉን ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ያያዛቸው ሲሆን የተቀሩትን ሁለት ተጠርጣሪዎችን ደግሞ በክትትል መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ ወንጀል ሲፈፅሙበት ነበረ የተባለ 176 ሲም ካርድ፣ 33 የሞባይል ቀፎዎች አንድ ተንቀሳቃሽ ዋይፋይ ራውተር፣ አንድ ተሽከርካሪ እና የተለያዩ የባንክ ደብተሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ህብረተሰብ ከባንክ አካውንት ጋር የተገናኘ ጥሪ ሲደርሰው ትክክለኝነቱን ደንበኛ ከሆነበት ባንክ ማረጋገጥ እና ጥርጣሬ ሲኖር ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለበትም ፖሊስ ማሳሰቡን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ ፍትህን የሚያዛባ በመሆኑ በጋራ ልንከላከለው ይገባል

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ እና ፍትህን የሚያዛባ በመሆኑ አንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉም አካል በጋራ ሊከላከል እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን።

ኮሚሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄዷል።

የሙስና ወንጀል ልማትን የሚያደናቅፍ፣ ፍትህን የሚያዛባ፣ የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያስከትልና ዲሞክራሲ እውን እንዳይሆን ማነቆ ከሆኑ ጉዳዮች ዋነኛዉ እንደሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የህግ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ ንጉሴ ወ/ሚካኤል ተናግረዋል።

የሙስና ወንጀሉን በመከላከል እረገድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተደራጀ ትብብርና ቅንጅት የሚፈልግ እንደሆነ ተገልጿል።

ኮምሽኑና በየደረጃው ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በዋናነት ሙስና እና ብልሹ አሰራር የማይሸከም ህብረተሰብ በመፍጠርና የግንዛቤ ስራዎችን በማስፋት ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን በጥናት መዝጋት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በፍትህና ልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ግዥ እንደተናገሩት አስቸኳይ ሙስና መከላከል ተግባራትን በመስራት የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከብክነት ማዳን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ክልላዊ የልማት ግቦቻችንን ወደማያደናቅፍ ደረጃ ማድረስ ይኖርብናል ማለታቸውን ሚዛን አማን ፋና ኤፍ ኤም ዘግቧል።

በኮሚሽኑና በየደረጃው ባሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የሚሰሩ የስራ አፈፃፀሞች ከጊዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች እንዳሉት በአፈፃፀም ግምገማው ላይ ተገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስናን በጽናት በመታገል መልካም አስተዳደርን እናረጋግጥ!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግምታቸው ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ ቆርቆሮና ቶንዲኖ ብረቶች ተያዙ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሀሰተኛ የጉምሩክ ሰነድ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግምታቸው ከ56.5 ሚሊየን ብር ዋጋ የሚያወጡ ቆርቆሮና ቶንዲኖ ብረቶች ተይዘዋል፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ቀናት ባደረገው የቁጥጥር ስራ ግምቱ 40 ሚሊየን ብር የሚሆን ቆርቆሮ እንዲሁም ግምታዊ ዋጋው 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሆነ ቶንዲኖ ብረት በድሞሩ 56 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ቆርቆሮና ብረት በሀሰተኛ የጉምሩክ ሰነዶች ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሀሰተኛ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህን እቃዎች ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናውን ማድረሱን ከገቢዎች ሚኒስቴር የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለባህልና ስፖርት ዘርፍ ሠራተኞች በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 4/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሚኒስቴሩ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ክንፌ የስልጠናው ዓላማ ሙያተኛው የሙያ ሥነምግባርን ተላብሶ ለተገልጋዩ ቀልጣፋና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ሙስና እና ብልሹ አሠራርን የሚፀየፍና የሚከላከል ሙያተኛ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ በአቶ ኪዳነ ምህረት እና በአቶ ካሳነው ጤናው የተሰጠ ሲሆን፤ በሥራ ሥነምግባር፣ በሙስና ጽንሰ ሀሳብና በመከላከያ ስልቶች እንዲሁም በግዥ ሂደት የሚፈጸም ሙስናን መከላከል ትኩረት ባደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡