Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የኮሚሽኑ ተልዕኮ የመንግስትና የህዝብን ሀብት ማዳን እንደመሆኑ የህዝቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አበረታች ተግባራት ተሰርተዋል - ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን የ2016 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ስትራቴጂካዊ ግቦች አፈፃፀምን በዝርዝር መገምገሙ ተገለጿል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንደገለፁት የኮሚሽኑ ዋና ተልዕኮ የመንግስትና የህዝብን ሀብት ማዳን ስለሆነ ይህንኑ ተረድቶ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀዉ፥ በኮሚሽኑ የተሰሩ ስራዎች ያመጡት ዉጤቶች በጊዜዉ በጥናት እያረጋገጡ መሄድ ይገባል ብለዋል፡፡

ክብርት አፈ-ጉባኤ አክለውም በኮሚሽኑ በርካታ ተግባራት መሰራታቸዉን ገልፀዉ፥ በተለይ በትግበራ ሂደት ቅድሚያ መሰራት ያለባቸዉን አውቆ ችግሮችን በጥናት ለመለየት የተሞከረበት ሂደት ጥሩ ሆነዉ በተመሳሳይ ሌሎች ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ተቋማት ላይም መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ የከተማው የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የሆኑት አቶ አስፋ ቶላ የተቋሙን የስትራቴጂክ ግቦች አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፥ በተቋሙ የሙስና መከላከል፣ ግንዛቤ ፈጠራ እና የክትትልና የመረጃ ማጣራት ሂደቱም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማድረግም በርካታ ተግባራት እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራትን አድንቀው በቀጣይ በከተማችን በሚስተዋለው የሙስና ችግሮች በሚመጥን ልክ የግንዛቤ ፈጠራ እና ሙስና መከላከል ስራዎችን በስፋት ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል መረጃ ሰብስቦ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ከማስተላለፍ ባሻገር ሂደቱን እስከመጨረሻ መከታተል ላይ ቢተኮር፣ የሙስና ምንጭ የሆኑ ተቋማትን ለይቶ ማጥናት ላይ ጅምር ቢሆንም በጥልቀት ፈትሾ ማየት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ከሀብት ምዝገባና ከሙስና መከላከል ስራ ጋር ተያይዞ ከክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሥነምግባርና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ለምክር ቤት አመራርና ሰራተኞች፣ ለክፍለ ከተማ ምክርቤት አፈ ጉባዔዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በ6 ወራት በርካታ ተግባራት ሲሰሩ የሰራተኛው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ በሥነምግባር የታነፀ አመራርና ሰራተኛ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በሥነምግባር የታነፀ አመራርና ሰራተኛ ለመፍጠር እንዲህ አይነቱ ስልጠና አስፈላጊ በመሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰጥ ም/አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሪት ፋኢዛ ሙሀመድ ገልፀዋል።

ስልጠናው መልካም ሥነምግባርን የተላበሰ አመራርና ሰራተኛ በመፍጠር ለመልካም አስተዳደር መስፈን እና ሙስናን ለመታገል ያለውን ገንቢ አስተዋጽኦ የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጀ ግርማ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት መጥቀሳቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሀሰተኛ ሠነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሀሰተኛ ሠነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቦቹ የተለያዩ ሀሰተኛ የመንግስትና የግል ተቋማት ሠነዶችን እንደሚያዘጋጁ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና ሃሰተኛ ሰነዱን በሚያዘጋጁበት መኖሪያ ቤት በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ ልዩ ልዩ ሃሰተኛ ሠነዶች፣ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው ሃሰተኛ ማህተም እና ቲተሮች እንዲሁም ሁለት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተይዘዋል፡፡

ሰነዶቹን በማዘጋጀት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት አራት ግለሰቦች ላይ በምርመራ የማጣራት ስራው መቀጠሉን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በህዝብና በሃገር ላይ የሚፈፀምና ዘርፈ ብዙ ጉዳት የሚያስከትል ወንጀል በመሆኑ ሃሰተኛ ሰነዶችን የሚያዘጋጁም ሆኑ በሃሰተኛ ሰነድ የሚገለገሉ ግለሰቦችን በህግ አግባብ ተጠያቂ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።
የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈፀሙ 114 ተፈታኞች ውጤት መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን ነው ሚኒስቴሩ ዛሬ ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ያስታወቀው፡፡

የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሰረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ ተመልክቷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119 ሺህ 145 ተፈታኞች መፈተናቸውን ከሚኒስቴሩ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ከኢንዶኔዥያ የሙስና ማስወገድ ኮሚሽን ጋር የተደረገው የልምድና የተሞክሮ ልውውጥ ላይ በቂ ግባቶች ተገኝተውበታል - የኮሚሽኑ የልዑካን ቡድን አባላት

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ዴኤታ እና የኦሮሚያ፣ የአማራና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮች እንዲሁም የፌደራል አራት የሥራ ኃላፊዎችን የያዘ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር በአቶ ወዶ አጦ የተመራ ልዑካን ቡድን እ.ኤ.አ ከማርች 5 እስከ 9 ቀን 2024 ድረስ የኢንዶኔዥያ የሙስና መከላከል ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ልምድና ተሞክሮ በመቅሰም ተመልሷል፡፡

የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ ዓላማው የሀገራችንን ብሔራዊ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ፖሊሲ ዝግጅት የሚያግዙ ልምዶና ተሞክሮ ለመቅሰም ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በኢንዶኔዥያ የሙስና ማስወገድ ኮሚሽን ቆይታ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ተደራሽ የሚያደርጋቸውን የሥነምግባር ሥልጠናና ትምህርት አሰጣጥ፣ የፀረ-ሙስና ትግልና የህብረተሰብ ትስስርና አጋዥነት፣ ዘርፈ ብዙ የሙስና መከላከል ዘዴዎች፣ የሀብት ምዝገበና ትክክለኛነት ማጣራት፣ የጥቅም ግጭት መከላከል፣ በፀረ-ሙስና ትግል የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ፋይዳ፣ የሙስና ወንጀል ቅድመ ምርመራ፣ የሙስና ወንጀል ምርመራ እንዲሁም የማስቀጣት ምጣኔ፣ በፀረ-ሙስና ትግል የባለድርሻ አካላት ትስስርና ሚና እንዲሁም በሙስና የተመዘበረ ሀብት ለማስመለስ ከሀገር ውስጥና ከውጪ አገር ስለሚደረገው ትስስር፣ በሙስና የተመዘበረ ሀብትና ንብረት የማሳገድ፣ የመንከባከብና የማስመለስ ሂደቶች ላይ ያተረኮሩ መሆኑን ከልዑካን ቡድኑ አባላት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የተገኙ መልካም ልምዶችና ተሞክሮዎች ለሀገራችን የፀረ-ሙስና ትግል በሚያመች መልኩ በመቀመርና በማስፋፋት እንዲሁም ይህንኑ በዝግጅት ሂደት የሚገኘውን የብሔራዊ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ፖሊሲ አካል በማድረግ ለማስፀደቅ እንደሚሠራ የልዑካን ቡድኑ ተልዕኮ ማሳካት እንደሆነም ግንዛቤ የተወሰደ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ልምዶችና ተሞክሮዎች ለኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ ተግባራዊ ለሚያደርጋቸው የሪፎርም ሥራዎች ዕገዛ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ተልዕኳቸውን ለማሳካት ሚና ለነበራቸው የኢንዶኔዥያ የሙስና ማስወገድ ኮሚሽን የበላይ አመራሮችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በኢንዶኔዥያ ለኢትዮጵያ ኢምባሲ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሁለት ሲኖ ትራኮች እንዲሰረቁና እንዲሰወሩ አድርገዋል የተባሉ የቀድሞ የፖሊስ አባላት እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች እንዲሰረቁና እንዲሰወሩ አድርገዋል የተባሉ ሶስት የአዲስ አበባ የቀድሞ ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች በተከሰሱበት ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ።

ችሎቱ በክስ መዝገቡ የተካተቱ ሌሎች ሶስት ተከሳሾችን በሚመለከት ደግሞ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።

ተከሳሾቹ 1ኛ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአራዳ ክ/ከተማ አራት ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ የቀድሞ የፖሊስ አባልና የወንጀል መከላከል ቡድን መሪ የነበረው ዋና ሳጅን ትግሉ ሰቦቃ፣ 2ኛ እና 3ኛ ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጊቢ ጥበቃ አባላት የነበሩት ኮ/ብል ዘነበ ኩማ እና ኮ/ብል መንግስቱ እንቻሌ እንዲሁም 4ኛ አቶ ላዕከ ተስፋ ገ/ስላሴ፣ 5ኛ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ድርጅት ውስጥ የቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 13 ጥበቃ የነበረው መልካሙ አያና፣ 6ኛ መላኩ ካላዩ፣ 7ኛ ከበደ ገ/እየሱስ፣ 8ኛ ወንዶሰን ወይም ኢብራሂም ረጋሳ ገለታ እና 9ኛ ሮቤል ሙሉአለም ሃይሉ ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል በ2015 ዓ.ም በተከሳሾች ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በክስ ዝርዝሩ ላይ እንዳመላከተው፤ ተከሳሾቹ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በጥቅም በመመሳጠር በዋና እና በልዩ ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ላይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ የፖሊስ አባላት ፖሊሳዊ ኃላፊነታቸውን ያለአግባብ በመገልገል በአዲስ አበባ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቦሌ አራብሳ ሳይት ውስጥ በመግባት በጥበቃ ስራ ላይ የነበረ (የዐቃቤ ሕግ ምስክር) ግለሰብን “ለወንጀል ምርመራ ትፈለጋለህ" በማለት 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ከጥበቃ ስፍራው ወደ ሌላ ቦታ ወስደዋል።

2ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ደግሞ በቦታው የነበሩ ንብረቶችን እንዲያወጡ በመርዳት 11 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ሁለት ማለትም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 03-95058 ኢት የሆነ እና የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 03-16409 ኢት የሆኑ ሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎችን 6ኛ ተከሳሽ ሞተሩን በካቻቢቴ በማስነሳት ከ9ኛ ተከሳሽ ጋር ተሽከርካሪዎችን ይዘውና ሌሎቹ ደግሞ አጅበው ወደ አዳማ በመውሰድና በመሰወር፣ 8ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከሌሎች ግብረዓበሮቹ ጋር በመሆን አንደኛውን ተሽከርካሪ ለግለሰብ በ600 ሺህ ብር በመሸጥና ገንዘቡን በ7ኛ ተከሳሽ ስም በተከፈተ በአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ በማስገባትና በተለያዩ መጠኖች ገንዘቡን መከፋፈላቸው ተጠቅሶ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ ሙስና ወንጀል ተከሰው ነበር።

ከተከሳሾቹ መካከል ስድስቱ ችሎት ቀርበው ክስ ዝርዝሩ የደረሳቸው ሲሆን÷ ቀሪ ሶስት ተከሳሾች ግን በተደጋጋሚ መጥሪያ ተደርጎላቸው ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ተከትሎ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ተደርጓል።

ችሎት የቀረቡ ስድስቱ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው የዕምነት ክህደት ቃላቸውን በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ገላጭ ማስረጃዎችን እና ስምንት የሰው ምስክሮችን ቃል አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ዛሬ በዋለው ችሎት 1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ማስረጃ በወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ፣ አንቀጽ 33 እንዲሁም የሙስና አዋጅን ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 2 መሰረት እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቷል።

5ኛ፣ 8ኛ እና 9ኛ ተከሳሾችን ደግሞ በዚሁ ድንጋጌ ስር በሌሉበት የጥፋተኝነት ፍርድ መተላለፈባቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተከላከሉ የተባሉ ተከሳሾችን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ለሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠ ሲሆን÷ በዚህ ቀን ዐቃቤ ሕግ የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ሶስት ተከሳሾችን በሚመለከት የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡