Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በኮሚሽኑ የሚዘጋጀው የየካቲት ወር 20ኛ ዕትም ወርሃዊ ዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ

****

የዲጂታል ፀረ-ሙስና ጋዜጣ ሙሉ መረጃን ለማግኘት ሊንኩን ያስፈጥሩ...https://drive.google.com/file/d/14KL-Pndw540Up3UotUEijGY15lBo4Y8P/view?usp=drivesdk

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሃይማኖት አባቶች መልካም ሥነምግባርን የተላበሰ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ትውልድ በመፍጠር ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው!

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ የለሚኩራ ክ/ከተማ የቀድሞ 3 ሠራተኞች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዘዘ

************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ አስተባባሪና የሊዝ ውል ባለሙያ የነበሩ ሦስት ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።

ተከሳሾቹ÷ 1ኛ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አሥተዳደር ጽ/ቤት የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ሥራዎች የቀድሞ አስተባባሪ አቶ ዘውዱ ኤርጆቦ፣ 2ኛ በዚሁ ክፍለ ከተማ የቦታ ማስከበርና ሊዝ ክትትል ቡድን ተወካይ አስተባባሪ የነበሩት አቶ እንግዳ ሙሉነህ እና የሊዝ ውል የቀድሞ ባለሙያ አቶ ፍፁም ደምሴ ናቸው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በማለት የማይገባ ጥቅም መቀበል ከባድ ሙስና ወንጀል ከሷቸዋል፡፡

በዚህም አቾንቴን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማኅበር የይዞታ ስፋቱ 1 ሺህ 22 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ የሊዝ ጨረታ አሸንፎ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ወደ ግንባታ ያልገባበትን ምክንያት ጠቅሶ የሊዝ ውሉ እንዲራዘምለት በወኪሉ አማካኝነት ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም የአገልግሎት ጥያቄ ሲያቀርብ "የሊዝ ውሉ እንዲራዘምለት ከፈለገ ለሥራው ማከናወኛ ለሰባት ሠራተኞች የሚከፋፈል ሦስት ሚሊየን ብር ይክፈል" የሚል ጥቅም ተከሳሾቹ መጠየቃቸው በክሱ ተመላክቷል፡፡

በ2ኛ እና በ3ኛ ተከሳሾች አማካኝነትም የገንዘብ መጠን ሲደራደሩ ከቆዩ በኋላ÷ 1 ሚሊየን 500 ሺህ ብር ለመቀበል በመስማማት፣ 1ኛ ተከሳሽ ደግሞ ጉዳዩን ለክፍለ ከተማው ፕሮሰስ ካውንስል አስቀርቦ ለማስወሰን የሊዝ ውል እንዲሻሻል ለማድረግ በመስማማትና ካውንስሉ እንዲወስን በማድረግ፣ 3ኛ ተከሳሽም ተወስኖ ያለቀለት መሆኑን ለግል ተበዳይ በመግለጽና በእህቱ ስም በንግድ ባንክ በተከፈተ አካውት ገንዘቡን አስገብቶ ወረቀቱን እንዲወስድ እንደተጠየቀ በክሱ ተገልጿል፡፡

የግል ተበዳይ በተጠየቀው መሰረትም ታኅሣስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም 1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር መክፈሉንና በተጨማሪም የቀድሞ መሬት አሥተዳደር ሕንጻ ላይ በሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ 3ኛ ተከሳሽ 200 ሺህ ብር ተቀብሎ ሊሄድ ሲል በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዙን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡

በዚሁ መሠረትም ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የማይገባ ጥቅም መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ለተከሳሾቹ ክሱ እንዲደርስ ከተደረገና በንባብ ከተሰማ በኋላ ክሱ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያ በጽሑፍ ማቅረባቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የሕግ መሰረት አለመኖሩን ጠቅሶ መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡

ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮም ተከሳሾቹ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ የጠቀሱት ፍሬ ነገር የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ የሚመረመር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ የክስ መቃወሚያቸውም ውድቅ ተደርጓል።

ተከሳሾቹም በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት እንዳልፈጸሙ በመግለጽ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ቃል እንዲሰማለት መጠየቁን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ ለዐቃቤ ሕግ ምስክሮች መጥሪያ እንዲደርስ በማዘዝ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለመጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተከሳሾቹም በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ፤ የለሚ ኩራ ፖሊስም ተከሳሾቹን ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ ተልዕኮ የመንግስትና የህዝብን ሀብት ማዳን እንደመሆኑ የህዝቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አበረታች ተግባራት ተሰርተዋል - ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን የ2016 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ስትራቴጂካዊ ግቦች አፈፃፀምን በዝርዝር መገምገሙ ተገለጿል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንደገለፁት የኮሚሽኑ ዋና ተልዕኮ የመንግስትና የህዝብን ሀብት ማዳን ስለሆነ ይህንኑ ተረድቶ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀዉ፥ በኮሚሽኑ የተሰሩ ስራዎች ያመጡት ዉጤቶች በጊዜዉ በጥናት እያረጋገጡ መሄድ ይገባል ብለዋል፡፡

ክብርት አፈ-ጉባኤ አክለውም በኮሚሽኑ በርካታ ተግባራት መሰራታቸዉን ገልፀዉ፥ በተለይ በትግበራ ሂደት ቅድሚያ መሰራት ያለባቸዉን አውቆ ችግሮችን በጥናት ለመለየት የተሞከረበት ሂደት ጥሩ ሆነዉ በተመሳሳይ ሌሎች ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ተቋማት ላይም መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ የከተማው የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የሆኑት አቶ አስፋ ቶላ የተቋሙን የስትራቴጂክ ግቦች አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፥ በተቋሙ የሙስና መከላከል፣ ግንዛቤ ፈጠራ እና የክትትልና የመረጃ ማጣራት ሂደቱም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማድረግም በርካታ ተግባራት እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራትን አድንቀው በቀጣይ በከተማችን በሚስተዋለው የሙስና ችግሮች በሚመጥን ልክ የግንዛቤ ፈጠራ እና ሙስና መከላከል ስራዎችን በስፋት ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል መረጃ ሰብስቦ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ከማስተላለፍ ባሻገር ሂደቱን እስከመጨረሻ መከታተል ላይ ቢተኮር፣ የሙስና ምንጭ የሆኑ ተቋማትን ለይቶ ማጥናት ላይ ጅምር ቢሆንም በጥልቀት ፈትሾ ማየት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ከሀብት ምዝገባና ከሙስና መከላከል ስራ ጋር ተያይዞ ከክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሥነምግባርና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ለምክር ቤት አመራርና ሰራተኞች፣ ለክፍለ ከተማ ምክርቤት አፈ ጉባዔዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በ6 ወራት በርካታ ተግባራት ሲሰሩ የሰራተኛው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ በሥነምግባር የታነፀ አመራርና ሰራተኛ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በሥነምግባር የታነፀ አመራርና ሰራተኛ ለመፍጠር እንዲህ አይነቱ ስልጠና አስፈላጊ በመሆኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰጥ ም/አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሪት ፋኢዛ ሙሀመድ ገልፀዋል።

ስልጠናው መልካም ሥነምግባርን የተላበሰ አመራርና ሰራተኛ በመፍጠር ለመልካም አስተዳደር መስፈን እና ሙስናን ለመታገል ያለውን ገንቢ አስተዋጽኦ የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጀ ግርማ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት መጥቀሳቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሀሰተኛ ሠነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሀሰተኛ ሠነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቦቹ የተለያዩ ሀሰተኛ የመንግስትና የግል ተቋማት ሠነዶችን እንደሚያዘጋጁ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና ሃሰተኛ ሰነዱን በሚያዘጋጁበት መኖሪያ ቤት በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ ልዩ ልዩ ሃሰተኛ ሠነዶች፣ ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው ሃሰተኛ ማህተም እና ቲተሮች እንዲሁም ሁለት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተይዘዋል፡፡

ሰነዶቹን በማዘጋጀት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት አራት ግለሰቦች ላይ በምርመራ የማጣራት ስራው መቀጠሉን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በህዝብና በሃገር ላይ የሚፈፀምና ዘርፈ ብዙ ጉዳት የሚያስከትል ወንጀል በመሆኑ ሃሰተኛ ሰነዶችን የሚያዘጋጁም ሆኑ በሃሰተኛ ሰነድ የሚገለገሉ ግለሰቦችን በህግ አግባብ ተጠያቂ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።
የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈፀሙ 114 ተፈታኞች ውጤት መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን ነው ሚኒስቴሩ ዛሬ ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ያስታወቀው፡፡

የፈተና ሥነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሰረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ ተመልክቷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119 ሺህ 145 ተፈታኞች መፈተናቸውን ከሚኒስቴሩ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡