ተማሪዎች ግብረ ገባዊ እና ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሥነምግባራዊ እሴቶችን ማጎልበት ይኖርባቸዋል - ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ
****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአራዳ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማና ልደታ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የመንግስት ትምህርት ቤት የግብረ ገብና የፀረ-ሙስና ክበባት ስራ አስፈፃሚ ተማሪዎች ስልጠና ሰጥቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በሀገራችን ብሎም በከተማችን እየተንሰራፋ የሚገኘውን የሥነምግባር ዝቅጠትና የግብረ ገብነት ችግሮችን ለመቅረፍ በትውልድ ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በከተማው የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የግብረ ገብነና የፀረ-ሙስና ክበባትን በአዲስ አደራጅቶ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ም/ኮሚሽነር አሰፋ ገልፀው፥ ተማሪዎች ግብረ ገባዊና ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሥነምግባራዊ እሴቶችን እንዲያጎለብቱ ክበባቱ መቋቋማቸው የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።
የኮሚሽኑ የስልጠና ክፍል ኃላፊ አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፥ ትምህርት ቤቶች የትውልድ ሥነምግባር መገንቢያ ማዕከል እንደመሆናቸው ነገ ሀገር ሊረከቡ የሚችሉ ተማሪዎችን ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው ገለፃ አድርገዋል።
ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል የትምህርት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ በስልጠናው ማብራራታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ኮሚሽኑ ከዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተወጣጡ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዘጠኝ ዩኒቨርሲቲ ለተወጣጡ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የሥልጠናው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና የስልጠና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፥ በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል፣ በግዥ ስርዓት ውስጥ የሚፈጸም ሙስና የመከላከያ ስልቶች እና በሥነምግባራዊ አመራርነት ምንነትና አስፈላጊነት፣ ክህሎቶች፣ መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናው ከደብረ ብርሃን፣ ከሰላሌ፣ ከአምቦ፣ ከደምቢ ደሎ፣ ከአሶሳ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በክላስተር ተሰጥቷል።

በሀገሪቱ ሌብነትን በማጥፋት ብልጽግናን ለማምጣት ተባብሮ መሥራት ወሳኝ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር
***
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 1/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በሀገሪቱ ሌብነትን በማጥፋት ብልጽግናን ለማምጣት ተባብሮ መሥራት ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ሰሞኑን ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ በውይይታቸው ወቅት እንደገለጹት፥ በሀገሪቱ ሌብነትን በማጥፋት ብልጽግናን ለማምጣት ተባብሮ መሥራት ወሳኝ ነው። ለዚህ ደግሞ ሁሉም ሰው ሠርቶ የሚለወጥባትን ሀገር ለመገንባት ተባብረን ልንሠራ ይገባል።
እንደመንግሥት የምንፈልገው በሀገራችን ሌብነትን በማጥፋት ብልጽግናን ማምጣት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሁሉም ሰው ተከባብሮ በደስታ ሠርቶ የሚለወጥባትን ሀገር ለመገንባት መንግሥትና ሕዝብ ተባብረን ልንሠራ ይገባል ብለዋል።
ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቀጣይ ምን መሠራት አለባቸው የሚለውን በጋራ በመወያየት የመፍትሔ ሃሳብ ማስቀመጥ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
ብልጽግና ፓርቲ 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን አባላት ያሉት ቢሆንም በውስጡ ሌባ፣ አጭበርባሪና የማይሠሩ ስላሉ ከስር ከስር የማጥራት ሥራ ይሠራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 8 ሺህ አመራሮች ከኃላፊነታቸው መባረራቸውን መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም አዲስ አበባ ውስጥ ትምህርት ቤቶች የሀሽሽና የጫት መናኸሪያ መሆናቸውን ገልጸው፥ ተማሪዎች ጫትና ሀሽሽ የሚጠቀሙ ከሆነ መጨረሻቸው ሌብነት ሊሆን ስለሚችል ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አመልክተዋል።