Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በሀገር አቀፍና በዓለምአቀፍ ተቋማት በሚቀጠሩበት ወይም ተቀጥረው እየሠሩ ባሉበት ጊዜ የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ይጣራልን ጥያቄዎችን እየተቀበለ የትምህርት ማስረጃ አጣርቶ በማረጋገጥ በተከታታይ ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት በ2015 ዓ.ም የቀረቡ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ በተደረገ የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያልተማሩባቸው ሀሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች ሆነው የተገኙ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በመሆኑም መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩና ወደ ፊትም የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል፡፡

ስለሆነም ከዚህ መግለጫ ጋር በፎቶ በተያያዘው የሀሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ስማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑን ጠቅሶ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መረጃውን በፌስቡክ ገፁ አጋርቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ተማሪዎች ግብረ ገባዊ እና ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሥነምግባራዊ እሴቶችን ማጎልበት ይኖርባቸዋል - ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአራዳ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማና ልደታ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የመንግስት ትምህርት ቤት የግብረ ገብና የፀረ-ሙስና ክበባት ስራ አስፈፃሚ ተማሪዎች ስልጠና ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በሀገራችን ብሎም በከተማችን እየተንሰራፋ የሚገኘውን የሥነምግባር ዝቅጠትና የግብረ ገብነት ችግሮችን ለመቅረፍ በትውልድ ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በከተማው የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ የግብረ ገብነና የፀረ-ሙስና ክበባትን በአዲስ አደራጅቶ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ም/ኮሚሽነር አሰፋ ገልፀው፥ ተማሪዎች ግብረ ገባዊና ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሥነምግባራዊ እሴቶችን እንዲያጎለብቱ ክበባቱ መቋቋማቸው የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።

የኮሚሽኑ የስልጠና ክፍል ኃላፊ አቶ ጀንበሩ ኢርኮ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፥ ትምህርት ቤቶች የትውልድ ሥነምግባር መገንቢያ ማዕከል እንደመሆናቸው ነገ ሀገር ሊረከቡ የሚችሉ ተማሪዎችን ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው ገለፃ አድርገዋል።

ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል የትምህርት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ በስልጠናው ማብራራታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ ከዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተወጣጡ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 30/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዘጠኝ ዩኒቨርሲቲ ለተወጣጡ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሥልጠናው ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ስልጠናው በኮሚሽኑ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና የስልጠና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፥ በመንግስት ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስናን መከላከል፣ በግዥ ስርዓት ውስጥ የሚፈጸም ሙስና የመከላከያ ስልቶች እና በሥነምግባራዊ አመራርነት ምንነትና አስፈላጊነት፣ ክህሎቶች፣ መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናው ከደብረ ብርሃን፣ ከሰላሌ፣ ከአምቦ፣ ከደምቢ ደሎ፣ ከአሶሳ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በክላስተር ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡