Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ለፍርድ ቤት ዘርፍ አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ ፈየራ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በተቋሙ ላይ የሰራተኞች ሥነምግባር ስለሚንፀባረቅ ሰራተኞች በሥነምግባራቸው መታነጽ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ በተለይ በአመራርነት ደረጃ በሥነምግባር የምንታማና በመልካም ሥነምግባር የማንታወቅ ከሆነ ከእኛ የሚማር አይኖርም ያሉ ሲሆን፣ መጀመሪያ መሰራት ያለበት በራሳችን ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው በበኩላቸው ሙስና ዜጎችን ለከፋ ድህነትና ስቃይ የሚዳርግና ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳለው ገልፀው፣ ሀገራችንም ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከሚስተዋልባቸው ሀገሮች አንዷ በመሆኗ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው ሥነምግባረዊ አመራርነት የሚለው ቁልፍ ጉዳይ በፍርድ ቤቶች እይታ ምን እንደሚመስልና እንዴት ይቃኛል የሚለውን በደንብ ለመረዳት የሚያስችል መሆኑንም አቶ ገዛኸኝ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ በአቶ ኪዳነ ምህረት እና በአቶ ካሳነው ጤናው የተሰጠ ሲሆን፣ በሥነምግባራዊ አመራርነት፣ ሥነምግባር ለአመራሩ ያለው አስፈላጊነት፣ የሥነምግባራዊ አመራርነት ክህሎቶች፣ መርሆዎች እና መገለጫ ባህሪያት እንዲሁም ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና በዘርፉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አኳያ የአመራሩ ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በክልሉ የተጀመረው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የማጣራት ሥራ ህዝብ በተደጋጋሚ ለሚያነሳቸው ቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጥ ነው - የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር)

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የማጣራት ሥራ ህዝብ በተደጋጋሚ ለሚያነሳቸው ቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፌደራል ፓርላማ እና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት ከወከላቸው ህዝብ ጋር ያደረጉት የውይይት ግብረ-መልስ ማቅረቢያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ መካሄዱ ተገልጿል፡፡

በክልሉ የሚኖሩ 20 ሺ ሰዎችን ማወያየት መቻሉን የተናገሩት በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ የተነሱ ሀሳቦችን፣ አስተያየቶችን፣ ጥያቄዎችንና ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ከህዝብ ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የሠላምና ፀጥታ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም፣ የሌብነት እና ብልሹ አሰራር እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች መነሳታቸውን አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ህዝብ ለሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር)ገልጸዋል::

ከሌብነትና ብሉሹ አሰራር ጋር ተያይዞ በተለይም የማዳበሪያ እዳ ጉዳይ ህዝብ በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚያነሳው ነው ያሉት የተከበሩ አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር)፣ አሁን ችግሩን ለመፍታት ወረዳዎችና ዞኖች የኦዲት ሥራ መጀመራቸው ጥሩ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተጀመረው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የማጣራት ሥራ ህዝብ በተደጋጋሚ ለሚያነሳቸው ቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጥ ነው ማለታቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የመጋዘን ኃላፊው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መድሃኒት በመሰወር የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበበት

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ ድርጅት የመጋዘን ኃላፊው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መድሃኒት በመሰወር የሙስና ወንጀል ክስ ቀረበበት።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመጋዘን ኃላፊ በነበረው እና በተመሳሳይ ወንጀል ተከሶ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ሚካኤል ዘዉገ ተሰማ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት ክስ አቅርቦበታል።

በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው፥ ተከሳሹ በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የሁለት መጋዘኖች ኃላፊ ሆኖ በሚያስተዳድርበት ወቅት የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ አገልግሎት አንቲ አርኤችኦ (ዲ) ኢሚዩን ግሎቡሊን (Anti-Rho (D) Immune Globulin 300 Mg in 2ml Vial- Injection) መድሐኒት መጠኑ በብልቃጥ 46 ሺህ 560 የሆነ ከበሀራት ሰሩም እና ቫሲን ኤልቲዲ (Bharat Serum and Vaccine LTD) ከተባለ አቅራቢ በግዥ ትዕዛዝ ከዉጭ ሀገር ያስመጣውን መድሐኒት መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ፈርሞ ከትራንዚተር ተረክቧል።

ከዚህ በኋላ መድሐኒቱን ወደ ሌላ "ሜይን 3"ወደ ተሰኘ መጋዘን አብሮ ገቢ ካደረገ በኋላ ከተረከበው አጠቃላይ 46 ሺህ 560 ብልቃጥ ውስጥ አጠቃላይ የዋጋ ግምቱ 1 ሚሊየን 114 ሺህ 857 ብር ከ87 ሳንቲም የሚያወጣ 900 ብልቃጥ መድሐኒት ሳያስረክብ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ያደረገ ወይም የሰወረ መሆኑ ተጠቅሶ በከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል መከሰሱን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ክሱን ለመመልከት ለመጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በሀገር አቀፍና በዓለምአቀፍ ተቋማት በሚቀጠሩበት ወይም ተቀጥረው እየሠሩ ባሉበት ጊዜ የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ይጣራልን ጥያቄዎችን እየተቀበለ የትምህርት ማስረጃ አጣርቶ በማረጋገጥ በተከታታይ ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት በ2015 ዓ.ም የቀረቡ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ በተደረገ የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያልተማሩባቸው ሀሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች ሆነው የተገኙ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በመሆኑም መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩና ወደ ፊትም የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል፡፡

ስለሆነም ከዚህ መግለጫ ጋር በፎቶ በተያያዘው የሀሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ስማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑን ጠቅሶ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መረጃውን በፌስቡክ ገፁ አጋርቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡