Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በኮሚሽኑ አመራሮች የተመራ የልዑካን ቡድን እና የኢንዶኔዥያ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 26/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የሥነምነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች እና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ እውነቴ አለነ እንዲሁም የፍትህ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ተስፋዬ ዳባን ያካተተ ልዑካን ቡድን በኢንዶኔዥያ ጃካርታ ከተማ ከሚገኘው የሙስና መከላከል ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

በኢሲያ ሀገራት ውስጥ በፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንዱ ከሆነው የኢንዶኔዥያ የሙስና መከላከል ኮሚሽን/KPK/ እንደገና ከተቋቋመበት እ.ኤ.አ ከ2003 ጀምሮ ተጠሪነቱን ለኢንዶኔዥያ ህዝብ በማድረግ፣ ከማኛውም አካል ነፃና ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ( Type A) የራሱን አቅም በሰው ኃይልና በበጀት በማሳደግ ሶስቱን የሙስና መታገያ ስልቶችን ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በትስስር የሥነምግባር ግንባታን፣ የሙስና መከላከል እና የምርመራና ክስ ሥራዎችን ስትራቴጂ በመንደፍና በማከናወን ላይ የሚገኝ ኮሚሽን መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይህን የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ልምድና ተሞክሮ ከኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ትግል በሚጣጣም መልኩ በመቀመር ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻል በኮሚሽኑ አመራሮች የተመራ ልዑኳን ቡድን ኢንዶኔዥያ ጃካርታ ከተማ በሚገኘው የሙስና መከላከል ኮሚሽን/KPK/ የሥራ ኃላፊና ባለሙያዎች በተገኙበት ልምድና ተሞክሯቸውን መለዋወጥ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በኢንዶኔዥያ የሙስና መከላከል ኮሚሽን አደረጃጀት፣ የሚያከናውናቸው ስትራቴጂዎች፣ ውጤታማነትና ተግዳሮቶች ላይ ለልኡካን ቡድን አባላት ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ ልኡካን ቡድኑም የኢትዮጵያ አጠቃላይ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴን በማብራራት በቀጣይ ልምድና ተሞክሮ የሚወስድባቸው ጉዳዮችን ትኩረት በማስቀመጥ ለብሔራዊ ሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ፖሊሲ ዝግጅት የሚያግዙ የመነሻ ሀሳቦች መፀባረቃቸው ተመላክቷል፡፡

የኢንዶኔዥያ የሙስና መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነሮችም በተደረገው የተሞክሮና ልምድ ልውውጥ ሂደት በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ተሞክሮ ሊሆኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

እንዲሁም የሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ላይ የተሞክሮና ልምድ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን፤ የልኡካን ቡድን አባላት ባነሷቸው ጉዳዮች ላይ በቂ ማብራሪያ መሰጠቱና በቀጣይ ቀናትም የልምድ ልውውጡ የሚቀጥል መሆኑን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ልጆቼ ዳኞች በመሆናቸው የፍርድ ቤት ክርክራችሁን እኔ አስጨርስላችኃለሁ በማለት ጉቦ የተቀበለችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 26/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጉልሱም ወረዳ ሁኛን በሪ ከተማ ውስጥ ልጆቼ ዳኞች ስለሆኑ የፍርድ ቤት ክርክራችሁን እኔ አስጨርስላችኃለሁ በማለት ገንዘብ የተቀበለች ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የጉልሱም ወረዳ ዓቃቤ ህግ ፅ/ቤት አስታውቋል።

የጉልሱም ወረዳ ዓቃቤ ህግ ፅ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን በላከው መረጃ ተከሳሽ አስናቀች ወጋየው የተባለች ግለሰብ ልጆቼ በከፍተኛና በወረዳ ፍርድ ቤት ሰራተኛ ናቸው በማለት መረጃ ስትሰጥ ቆይታለች። በዚህም መሰረት አባትህን ከእስር አስፈታልኻለው በማለት 20 ሺ ብር ከአንድ ግለሰብ መቀበሏ ተገልጿል።

በተጨማሪም ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም 20 ሺህ ብር አይበቃም በማለት ተጨማሪ 10 ሺህ ብር በመቀበል በአጠቃላይ 30 ሺህ ከአንድ ግለሰብ መቀበሏን በማስረጃ ተረጋግጧል።

ተከሳሿ በልጆቿ ስም በመጠቀም ማጭበርበሯን ፖሊስ በተገቢው ማስረጃ በማረጋገጥ የምርመራ መዝገቡንም ለዓቃቤህግ ልኳል። ዓቃቤህግም የምርመራ መዝገቡን በመመልከትና አንቀጽ በመጥቀስ ክስ መስርቶባታል።

ክሱን የተመለከተው የጉልሱም ወረዳ ፍርድ ቤትም በፍትህ አካላት ስም የማጭበርበር ድርጊት የፈፀመችው ግለሰብን በ2 ዓመት እስርና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ መወሰኑን የጉልሱም ወረዳ ዓቃቤ ህግ ፅ/ቤት ጨምሮ ገልጿል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ጉቦ ሲቀበል ተይዟል የተባለ ዐቃቤ ሕግ ላይ ክስ ተመሰረተ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 27/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከግለሰብ ጉቦ ሲቀበል ተይዟል የተባለ የፌደራል ዐቃቢ ሕግ ላይ ክስ ተመሰረተ።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ናሆም ጌታቸው በተባለ ዐቃቤ ሕግ ላይ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10 (1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የተፈፀመ ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶበታል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው፤ ተከሳሹ በፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዐቃቤ ህግነት ተመድቦ በማገልገል ላይ እያለ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ የግል ተበዳይ አማኑኤል ገነሜ የተባለ ግለሰብ በወንጀል ተጠርጥሮ እና ክስ ተመስርቶ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩ በመታየት ላይ እያለ ተከሳሽ በስራ ግዴታው ማድረግ የማይገባውን ለማድረግ በማሰብ "ጉዳዩ በቀላሉ እንዲያልቅለትና ቅጣቱ በገንዘብ መቀጮ እንዲሆን አደርጋለሁ" በማለት የ60 ሺህ ብር ጉቦ እንዲከፍል ተበዳይን በመጠየቅ ድርድር ሲያደርግ ቆይቷል።

ድርድር ካደረገ በኋላም በጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ሰሜን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገናኘት 40 ሺህ ብር ለመቀበል በመስማማትና ከተስማሙት ገንዘብ ላይ በተከሳሽ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር በቅድሚያ 10 ሺህ ብር ተላልፎለት የተቀበለ በመሆኑ በቀረበበት ክስ ላይ በዝርዝር ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በየካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡10 አካባቢ በአራዳ ክፍለ ከተማ ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኝ ካፌ ውስጥ በመገኘት ብር 10 ሺህ ከግለሰብ ተቀብሎ ሲሄድ እጅ ከፍንጅ የተያዘ መሆኑ ተጠቅሶ ጉቦ በመቀበል የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሰነድ ገላጭና አስረጂ ማስረጃዎች መያያዛቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የክሱ ዝርዝር ለተከሳሽ እንዲደርስ በማድረግ ክሱን ለመመልከት ለመጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሚዲያ ተቋማት ህፃናትና ወጣቶች በመልካም ሥነምግባር ታንጸው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንዲችሉ ግንዛቤ የመፍጠር ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል!

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የተለያዩ ማታለያዎችን በመጠቀም ከ300 ሺህ ብር በላይ የወሰደው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 28/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የተለያዩ ማታለያዎችን በመጠቀም ወደ ግል ተበዳዮች ስልክ በመደወል የሚነገራቸውን ቁጥር በመንካት ገንዘብ እንዲያስተላልፉለት በማድረግ ከ300 ሺህ ብር በላይ የወሰደው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣቱ ተገልጿል።

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ ሜጋ ማንዴላ ማለቆ የተባለው ተከሳሽ በተለያዩ 6 ክሶች የተከሰሰ ሲሆን፤ በክሱ ዝርዝርም ተከሳሽ የሌላን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም ካልተያዙ ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን ከህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ 6 ቀናት ለተለያዩ ግለሰቦች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ በመደወል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደደወሉ በማስመሰል የተለያዩ ማታለያዎችን በመጠቀም እነሱ የሚነግሯቸውን ቁጥር በስልካቸው እንዲነኩ በማድረግ በ1ኛ ክሱ ላይ 11 ሺህ 10 ብር፣ በ2ኛ ክሱ ላይ 64 ሺህ 900 ብር፣ በ3ኛ ክሱ ላይ 8 ሺህ 300 ብር፣ በ4ኛ ክሱ ላይ 199 ሺህ 400 ብር፣ በ5ኛ ክሱ ላይ 68 ሺህ ብር፣ በ6ኛ ክሱ ላይ 19 ሺህ 600 ብር ከተበዳዮች ሂሳብ ቁጥር ላይ ተቀናሽ ሆኖ ተከሳሽ ሀሰተኛ ስም እና መታወቂያ ተጠቅሞ ወደከፈተው ሂሳብ ቁጥር እንዲያስተላልፉ አድርጓል።

ተከሳሽም የገባውን ብር ከአካውንቱ ላይ ያወጣው በመሆኑ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ መሰረት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ በፈፀመው በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለቱና በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠትና የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን በፍትህ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሴቶች ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ሚናቸው የጎላ ነው!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለኮሚሽኑ ሰራተኞች አቅማቸውን ሊገነባ የሚችል የስራ ላይ ሥነምግባር ስልጠና ተሰጠ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ለአብክመ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች በስራ ላይ ሥነምግባር አቅማቸውን ማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ በስራ ላይ ሥነምግባር ዙሪያ የመነሻ ጽሁፍ አዘጋጅተው ያቀረቡ ሲሆን፥ በሥነምግባር ምንነት፣ ከስራ ጋር ተያያዥ የሆኑ የሥነምግባር መገለጫዎች፣ ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ስልጠና መስጠት ችለዋል።

ወ/ሮ በላይነሽ በሥነምግባር ጉድለት ከሚደርሱ ጥፋቶችና ችግሮች ለመዳን በሥነምግባር መርሆች በመመራት፣ ተቋማዊ የሥነምግባራዊ ባህልን በመገንባት የተሰጠንን ስራ በመልካም ሥነምግባር ልናከናውንና ልናገለግል ይገባል ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና የሰራተኛውን አቅም ማጎልበት የሚችልና ክፍተቶችን ለማስተካከል አጋዥ ነው። በቀጣይ የሰራተኛውን አቅምና የሥነምግባር ክፍተት የሚሞላ ቀጣይነት ያለው ስልጠና ቢሰጥ መልካም እንደሆነ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በፀረ-ሙስና ትግል ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሁሉም ኃላፊት ነው!

****************

ሴቶች ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመፈፀም ረገድ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑን አለምዓቀፍ ጥናቶች ያመለክታሉ፤ ስለሆነም በፀረ-ሙስና ትግል ውስጥ የሴቶችን ሚና ማሳደግ ይገባል!

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የኮሚሽኑ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች አለምዓቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ፡፡

አለምዓቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች 8) "ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!" በሚል መሪ ቃል በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ113ኛ፤ በአገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን፣ በዓሉን አስመልክቶ የኮሚሽኑ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች መቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በማዕከሉ ድጋፍ፣ እገዛ እና እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ ተችሏል።