Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.03K links
Download Telegram
የሙያ ሥነምግባርን በማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጋር በሥነምግባር ግንባታና ሙስናን ለመታገል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የስምምነት ሰነዱ ዓላማ በሥነምግባር ግንባታ እና ሙስናን በመከላከል ረገድ ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሙያ ሥነምግባር ለማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለዉም ይህ ትብብር ሀብትን፣ ዕውቀትን እና ስልጣንን በማቀናጀት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሥነምግባራዊ አመራር እና ሰራተኛ በመፍጠር ለፀረ-ሙስና ትግሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያስችለናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ በበኩላቸዉ ቢሮዉ የሚሰራቸዉ ተግባራት በቀጥታ ከሥነምግባር ጋር የሚገናኙ እንደመሆናቸዉ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር መስራት ለቢሮዉ ያለዉ ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የብልሹ አሰራር ምንጩ የሥነምግባር ጉድለት መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊ፥ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት የተፈራረምነውን ሰነድ በተግባር ለማዋል አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለቱሪዝም ዘርፍ አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለቱሪዝም ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ አቶ ስለሺ ግርማ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ በአቶ ኪዳነ ምህረት እና በአቶ ካሳነው ጤናው የተሰጠ ሲሆን፣ በሥነምግባራዊ አመራርነት፣ ሥነምግባር ለአመራሩ ያለው አስፈላጊነት፣ የሥነምግባራዊ አመራርነት ክህሎቶች፣ መርሆዎች እና መገለጫ ባህሪያት፣ ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና በዘርፉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አኳያ የአመራሩ ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አባቶቻችን በጀግንነት ጠብቀው ያቆዩትን ሀገር የዛሬው ትውልድ በሥነምግባር በመገባት እና ሌብነትን በመፀየፍ ልማቷን ማስቀጠል ይገባል - የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዘዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀገርን ለመገንባት ከስግብግብነት የነፃና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ያስፈልጋል - ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽኑ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በቅንጅት በሰራቸው ተግባራት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 24/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በሰራቸው ቅንጅታዊ ስራዎች በቢሮው የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

ኮሚሽኑ በተለይ ክበባትን በየትምህርት ቤቶች እንዲቋቋሙና ተከታታይ የትውልድ ግንባታ ስራዎችን እንዲሰሩ ድጋፍ እያደረገ ሲሆን፥ በሥነምግባራቸው እና በውጤታቸው ምስጉን የሆኑ ተማሪዎችን ለማበረታታት ከየክፍለ ከተማው ለተመረጡ ተማሪዎች ሽልማት አበርክቷል።

በሌላ በኩል ተማሪዎች መልካም ሥነምግባርን እንዲያዳብሩ ተከታታይ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን፥ መምህራንም የሥነምግባር ግንባታ ስራው ላይ ያላቸውን የላቀ ሚና ተረድተው በበላይነት እንዲወጡ በኮሚሽኑ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።