Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
የመታመን ባህልን በመገንባት ሙስናን ለመከላከል ሥነምግባራዊ የአመራርነት ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በየደረጃው ለሚገኙ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የሥነምግባራዊ የአመራርነት ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ኮሚሽኑ በከተማችን ሙስና የልማትና የሰላም ስጋት እንዳይሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ የፐብሊክ ሰርቪስ አመራርና ሰራተኞች በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የሙያ ሥነምግባር በማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ በሰጡት ስልጠና ሥነምግባራዊ አመራርነት በአራያነት መምራትን፣ ታማኝነትን፣ ግልፀኝነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን፣ መከባበርና ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥን የሚያበረታታ የአመራር አይነት መሆኑን ገልፀዋል። ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል በሥነምግባር የበለፀገ አመራርና ባለሙያ ማፍራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በስልጠናው የተሳተፉ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና ሥነምግባር ያለው አመራርና ፈፃሚ መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፥ መልካም ስብዕና ያለው አገልጋይ ለመፍጠር ከኮሚሽኑ ጋር በዘላቂነትና በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የባንክ አሰራር ሥርዓትን ለማስተካከል በሚል የግለሰቦችን ምስጢር ቁጥር በመውሰድ ገንዘብ ያጭበረበረው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የባንክ አሰራር ሥርዓትን ለማስተካከል በሚል በማታለል የግለሰቦችን ምስጢር ቁጥር በመውሰድ ገንዘብ ያጭበረበረው ተከሳሽ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት በተከሳሹ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎችን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ሜጋ ማንዴላ የተባለ ተከሳሽን በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ሚያዚያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኮምፒዩተር አማካይነት የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 10 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በተመሳሳይ ድንጋጌ 6 ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

በቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ 6 ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደተደወለ በማስመሰልና የንግድ ባንክ የአሰራር ሥርዓት በማስተካከል ሥራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ የግለሰቦችን የምስጢር ቁጥር እንዲነግሩት በማድረግ ከ370 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ማጭበርበሩ ተመላክቷል።

ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው እና በችሎት በንባብ እንዲሰማ ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አልፈጸምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃ እና የሰው የምስክር ቃል ለችሎቱ አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሹ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየቶችን በመያዝ ተከሳሹን በ6 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራት እና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 165 ሚሊዮን ብር ከምዝበራ ማዳን ተችሏል - ኮሚሽኑ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሙስናን ለመከላከል በቅንጅት በተሰራው ሥራ ሊመዘበር የነበረ 165 ሚሊዮን ብር የህዝብና የመንግሥት ሀብትን ማዳን መቻሉን የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በቅንጅት የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፋሲካ ጌታቸው እንደገለጹት ሙስና የሚያደርሰውን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል በክልሉ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ እየተሰራ ነው።

ሥራውን የሚያግዙ 900 የሥነምግባር መኮንኖችን በየመዋቅሩ በመመልመል ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሙስና ዙሪያ ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ ለማጎልበት ለ700 ሺህ የማህበረሰብ ተወካዮች ስልጠና እንደተሰጠ ተናግረዋል።

ስልጠናውን ተከትሎ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአሰራር ጥሰት፣ የኦዲት ጉድለትና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ በርካታ ጥቆማዎች ከማህበረሰቡ መምጣታቸውንም የዘገበው ኢዜአ ነው።

ጥቆማውን መሰረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች ያለአግባብ ሊከፈል ከነበረ ደመወዝ፣ ከኦዲት ጉድለት፣ ከመሬትና ሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ ሊመዘበር የነበረ 165 ሚሊዮን ብር ማዳን መቻሉን አቶ ፋሲካ ገልጸዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ሙስናን የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ክልሉን ከሙስና የፀዳ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ የሚኖሩት አቶ አብርሃም ሱጋቶ ሙስና ህዝብንና ልማትን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ በአንድነት መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

ክልሉ አዲስ እንደመሆኑ ለልማት ሥራ በግል እያደረጉት ካለው ድጋፍ ባለፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

ለማህበረሰቡ ተገቢ አገልግሎት የሚሰጥና ሙስናን የሚጸየፍ ዜጋን ማፍራት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ያሉት ደግሞ በከተማው የሄጦ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አቦሰጥ አየለ ናቸው።

ለዚህም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጠቁመው፣ ህብረተሰቡ በተለያዩ ተቋማት ጉዳዩን ያለእጅ መንሻ ማስፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአብክ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአጋር አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአብክመ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በዛሬው እለት የምክክር መድረክ አካሄዷል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ባለሙያ አቶ ዘላለም ንጉሴ በመድረኩ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፥ ሰነዱ የሀገራችን ሥነምግባር ታሪካዊ ዳራ፣ የወጣቶች የሥነምግባር ነባራዊ ሁኔታ፣ የወጣቶች አሉታዊ ምኞትና ሥነምግባራዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም ጥሰቶች ተጠያቂ እነማን እነደሆኑና ለገጠሙን ችግሮች መፍትሄዎችን ጨምሮ ሰፋ ያሉ ችግሮችን የዳሰሰ ፅሁፍ አቅርበዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ በዚህ ሰዓት የወጣቱ ጉዳይ የኔም ጉዳይ ነው ብሎ ይህንን መድረክ አዘጋጅቶ ወቅቱንና ወጣቱ ያለበትን ደረጃ ተረድቶ ችግሩን በግልፅ የሚያሳይ ፅሁፍ አዘጋጅቶ ስልጠና መስጠት መቻሉ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል።

አክለውም ተሳታፊዎች ባሁኑ ሰዓት ከጦርነት በላይ ወጣቱን እየገደለና ወዳልተገባ የሥነምግባር ችግር እያስገባ ያለው አደንዛዥ እፅና ቁማር ነው። በመሆኑም የሚመለከተን ተቋማት በጋራ በመተባበርና በመቀናጀት ውጤት ያለው ስራ መስራት ይገባናል ብለዋል። ሁሉም ባለድርሻ አካላት ችግሮችን ለመፍታት ውይይቱ ትልቅ አቅም ስለሚፈጥር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ሀሳብ ማጋራታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በመድረኩም ከክልል እስከ ዞን ድረስ ያሉ የትምህርት ቢሮና የወጣቶችና ስፖርት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሙያ ሥነምግባርን በማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጋር በሥነምግባር ግንባታና ሙስናን ለመታገል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የስምምነት ሰነዱ ዓላማ በሥነምግባር ግንባታ እና ሙስናን በመከላከል ረገድ ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሙያ ሥነምግባር ለማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለዉም ይህ ትብብር ሀብትን፣ ዕውቀትን እና ስልጣንን በማቀናጀት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሥነምግባራዊ አመራር እና ሰራተኛ በመፍጠር ለፀረ-ሙስና ትግሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያስችለናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ በበኩላቸዉ ቢሮዉ የሚሰራቸዉ ተግባራት በቀጥታ ከሥነምግባር ጋር የሚገናኙ እንደመሆናቸዉ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር መስራት ለቢሮዉ ያለዉ ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የብልሹ አሰራር ምንጩ የሥነምግባር ጉድለት መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊ፥ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት የተፈራረምነውን ሰነድ በተግባር ለማዋል አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ለቱሪዝም ዘርፍ አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

****************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለቱሪዝም ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ አቶ ስለሺ ግርማ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ በአቶ ኪዳነ ምህረት እና በአቶ ካሳነው ጤናው የተሰጠ ሲሆን፣ በሥነምግባራዊ አመራርነት፣ ሥነምግባር ለአመራሩ ያለው አስፈላጊነት፣ የሥነምግባራዊ አመራርነት ክህሎቶች፣ መርሆዎች እና መገለጫ ባህሪያት፣ ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና በዘርፉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አኳያ የአመራሩ ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡