Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.93K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.03K links
Download Telegram
ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ምንጩን ደብቆ ለሌሎች ግለሰቦች አስተላልፏል የተባለው ተከሳሽ በ13 ዓመት እስራት ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከባንክ ደንበኞች ሂሳብ ተቀንሶ ገቢ የተደረገለትን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ምንጩን ደብቆ ለሌሎች ግለሰቦች አስተላልፏል የተባለው ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ጌትነት አማረ በተባለው ተከሳሽ ላይ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ለ) እና ንዑስ ቁጥር 2 የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ምንጩን በመደበቅ ህጋዊ አድርጎ ማቅረብ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።

በዚህ ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው፤ በዚሁ መዝገብ ቀደም ብሎ ጉዳያቸው ታይቶ ቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞጣ ቀራንዮ ቅርጫፍ የባንኩ ሰራተኞች በነበሩ ሁለት ግለሰቦች አማካኝነት በርሔ ወልዴና ሸዊት አለማየሁ ከተባሉ የባንኩ ደንበኞች ፍቃድ ውጪ የአሰራርና መመሪያን በመተላለፍ በተለያዩ ቀናቶች 10 ሚሊየን 400 ሺህ ብር በመቀነስና በማጽደቅ ተሳትፎ በጥቅምት 26 ቀን በ2015 ዓ.ም በአዳማ ዲስትሪክት ሃዩ ቅርጫፍ በሀሰተኛ ማንነትና የነዋሪነት መታወቂያ በተከሳሹ ስም በተከፈተ ሂሳብ ገቢ እንዲሆን መደረጉ ተጠቅሷል።

ተከሳሹ ደግሞ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 8 በሀሰተኛ ማንነት ባወጣው ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ሃዩ ቅርጫፍ በከፈተው ሂሳብ ውስጥ ገቢ የተደረገለትን 10 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ወደ ተለያዩ ግለሰቦች ሂሳብ ማስተላለፉ በክሱ ላይ ተመላክቷል።

ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል።

የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 3 መሰረት የወንጀል አፈጻጸምና የደረሰውን ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ተከሳሹ ከለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 8 በሀሰተኛ ማንነት የነዋሪነት መታወቂያ በመውሰድ በአዳማ ሃዩ ቅርጫፍ የባንክ ሂሳብ በመክፈት 10 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ገቢ የተደረገለትና ገንዘቡን ወደተለያዩ ግለሰቦች ያስተላለፈ መሆኑን በመገንዘብ የወንጀል ደረጃውን መካከለኛ የወንጀል ደረጃ በመመደብ ተከሳሹ ያቀረበው የተለያዩ የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶች በመያዝ ከሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲቆጠብ ለማስተማር በሚል በሁለቱም ክስ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እና በዕርከን 8 መሰረት በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት እንዲያስፈጽም መታዘዙን ኤፍቢሲ ዘግቧል ።

ተከሳሹ የተጣለበትን የገንዘብ ቅጣት ለመንግስት ገቢ እንዲያደርግ የፍትህ ሚኒስቴር ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አልሻራዲ ጋር ውይይት አካሄዱ

****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አልሻራዲ ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡

ውይይቱ በአቅም ግንባታ ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሀብት ማስመለስ እንዲሁም በሙስና መከላከል ላይ በጋራ ለመስራት ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ በቀጣይ የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ጥፍጥፍ ወርቅ ይዞ ሲዘዋወር የተያዘው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በህገ-ወጥ መንገድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ጥፍጥፍ ወርቅ ይዞ ሲያዘዋውር በፍተሻ በተያዘው ግለሰብ ላይ በከባድ ሙስና እና የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ ማዕድን በተፈጥሮዓዊ ሁኔታዉ መያዝ ወንጀል ክስ መሰረተበት፡፡

በዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ አማረ ዮሃንስ በተባለው ተከሳሽ ላይ የወንጀል የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በ1ኛ ክሱ ላይ ተከሳሽ አንድ የመንግስት ሠራተኛ በኃላፊነቱ ወይም በሥራ ግዴታዉ ማድረግ የሚገባዉን እንዳያደርግ በማሰብ የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡40 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሀገር ዉስጥ በረራ በሚባለዉ ቦታ ተከሳሽ በብርበራ ከለበሰዉ ጃኬት ዉስጥ የተያዘዉን ሶስት የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉ የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ ሲያዘዋውር በፖሊስ አባላት ሲያዝበት በቦታዉ የነበረዉ የሻምበል አዛዥ የሆነዉን የዐቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑትን ንግድ ፍቃድም የለኝም፣ ነጋዴም አይደለሁም፣ የተያዘዉን ወርቅ ግማሹን ልስጥክ እና ልቀቀኝ በማለት የተያዘዉን ወርቅ ብዛት ግማሽ በጉቦ ያቀረበ በመሆኑ በፈፀመው ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡

በተመሳሳይ በ2ኛ ክሱ ተከሳሽ ከላይ በ1ኛ ክስ ዉስጥ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በቦታዉ በመደበኛ ስራቸዉ ላይ የነበሩት የፖሊስ አባላት ተከሳሽን አካላዊ ፍተሻ ሲፈትሹ ምንም አይነት የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ በለበሰው ጃኬት ዉስጥ ሶስት ጥፍጥፍ ወርቅ የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉን የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን ወርቅ የከበረ ማዕድን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ በፍተሻ የተገኘ በመሆኑ የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ ማዕድን በተፈጥሮዓዊ ሁኔታዉ መያዝ ወንጀል መከሰሱን ከፍትህ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ተከሳሽ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት መቃወሚያ የለኝም በማለት ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ ለማሰማት ለመጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የመታመን ባህልን በመገንባት ሙስናን ለመከላከል ሥነምግባራዊ የአመራርነት ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በየደረጃው ለሚገኙ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የሥነምግባራዊ የአመራርነት ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ኮሚሽኑ በከተማችን ሙስና የልማትና የሰላም ስጋት እንዳይሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፥ የፐብሊክ ሰርቪስ አመራርና ሰራተኞች በፀረ-ሙስና ትግሉ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የሙያ ሥነምግባር በማጎልበት የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀንበሩ ኢርኮ በሰጡት ስልጠና ሥነምግባራዊ አመራርነት በአራያነት መምራትን፣ ታማኝነትን፣ ግልፀኝነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን፣ መከባበርና ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥን የሚያበረታታ የአመራር አይነት መሆኑን ገልፀዋል። ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል በሥነምግባር የበለፀገ አመራርና ባለሙያ ማፍራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በስልጠናው የተሳተፉ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና ሥነምግባር ያለው አመራርና ፈፃሚ መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፥ መልካም ስብዕና ያለው አገልጋይ ለመፍጠር ከኮሚሽኑ ጋር በዘላቂነትና በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የባንክ አሰራር ሥርዓትን ለማስተካከል በሚል የግለሰቦችን ምስጢር ቁጥር በመውሰድ ገንዘብ ያጭበረበረው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የባንክ አሰራር ሥርዓትን ለማስተካከል በሚል በማታለል የግለሰቦችን ምስጢር ቁጥር በመውሰድ ገንዘብ ያጭበረበረው ተከሳሽ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት በተከሳሹ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎችን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ሜጋ ማንዴላ የተባለ ተከሳሽን በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ሚያዚያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኮምፒዩተር አማካይነት የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 10 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በተመሳሳይ ድንጋጌ 6 ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

በቀረበው ክስ ዝርዝር ላይ ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ 6 ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደተደወለ በማስመሰልና የንግድ ባንክ የአሰራር ሥርዓት በማስተካከል ሥራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ የግለሰቦችን የምስጢር ቁጥር እንዲነግሩት በማድረግ ከ370 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ማጭበርበሩ ተመላክቷል።

ተከሳሹ በዚህ መልኩ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው እና በችሎት በንባብ እንዲሰማ ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አልፈጸምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃ እና የሰው የምስክር ቃል ለችሎቱ አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሹ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየቶችን በመያዝ ተከሳሹን በ6 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራት እና በ6 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 165 ሚሊዮን ብር ከምዝበራ ማዳን ተችሏል - ኮሚሽኑ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሙስናን ለመከላከል በቅንጅት በተሰራው ሥራ ሊመዘበር የነበረ 165 ሚሊዮን ብር የህዝብና የመንግሥት ሀብትን ማዳን መቻሉን የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በቅንጅት የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፋሲካ ጌታቸው እንደገለጹት ሙስና የሚያደርሰውን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል በክልሉ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ እየተሰራ ነው።

ሥራውን የሚያግዙ 900 የሥነምግባር መኮንኖችን በየመዋቅሩ በመመልመል ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሙስና ዙሪያ ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ ለማጎልበት ለ700 ሺህ የማህበረሰብ ተወካዮች ስልጠና እንደተሰጠ ተናግረዋል።

ስልጠናውን ተከትሎ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአሰራር ጥሰት፣ የኦዲት ጉድለትና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ በርካታ ጥቆማዎች ከማህበረሰቡ መምጣታቸውንም የዘገበው ኢዜአ ነው።

ጥቆማውን መሰረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች ያለአግባብ ሊከፈል ከነበረ ደመወዝ፣ ከኦዲት ጉድለት፣ ከመሬትና ሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ ሊመዘበር የነበረ 165 ሚሊዮን ብር ማዳን መቻሉን አቶ ፋሲካ ገልጸዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ሙስናን የመከላከል ሥራዎችን በማጠናከር ክልሉን ከሙስና የፀዳ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ የሚኖሩት አቶ አብርሃም ሱጋቶ ሙስና ህዝብንና ልማትን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ በአንድነት መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

ክልሉ አዲስ እንደመሆኑ ለልማት ሥራ በግል እያደረጉት ካለው ድጋፍ ባለፈ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

ለማህበረሰቡ ተገቢ አገልግሎት የሚሰጥና ሙስናን የሚጸየፍ ዜጋን ማፍራት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ያሉት ደግሞ በከተማው የሄጦ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አቦሰጥ አየለ ናቸው።

ለዚህም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጠቁመው፣ ህብረተሰቡ በተለያዩ ተቋማት ጉዳዩን ያለእጅ መንሻ ማስፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡