ለውጭ ጉዳይ ዘርፍ አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
****************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 20/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሥነምግባራዊ አመራርነት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በስልጠናው ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን (ዶ/ር) እንዳሉት የስልጠናው አላማ የአመራሮችን የሞራል ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂን በተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ስልጠናው በፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግም አላምረው እየተሰጠ ሲሆን፣ በሥነምግባራዊ አመራርነት፣ ሥነምግባር ለአመራሩ ያለው አስፈላጊነት፣ የሥነምግባራዊ አመራርነት ክህሎቶች፣ መርሆዎች እና መገለጫ ባህሪያት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፤ በነገው ዕለትም ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና በዘርፉ ሙስና አና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አኳያ የአመራሩ ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ምንጩን ደብቆ ለሌሎች ግለሰቦች አስተላልፏል የተባለው ተከሳሽ በ13 ዓመት እስራት ተቀጣ
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ከባንክ ደንበኞች ሂሳብ ተቀንሶ ገቢ የተደረገለትን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ምንጩን ደብቆ ለሌሎች ግለሰቦች አስተላልፏል የተባለው ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።
የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ጌትነት አማረ በተባለው ተከሳሽ ላይ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 (ለ) እና ንዑስ ቁጥር 2 የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረትን ወይም ገንዘብን ምንጩን በመደበቅ ህጋዊ አድርጎ ማቅረብ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፏል የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።
በዚህ ክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው፤ በዚሁ መዝገብ ቀደም ብሎ ጉዳያቸው ታይቶ ቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞጣ ቀራንዮ ቅርጫፍ የባንኩ ሰራተኞች በነበሩ ሁለት ግለሰቦች አማካኝነት በርሔ ወልዴና ሸዊት አለማየሁ ከተባሉ የባንኩ ደንበኞች ፍቃድ ውጪ የአሰራርና መመሪያን በመተላለፍ በተለያዩ ቀናቶች 10 ሚሊየን 400 ሺህ ብር በመቀነስና በማጽደቅ ተሳትፎ በጥቅምት 26 ቀን በ2015 ዓ.ም በአዳማ ዲስትሪክት ሃዩ ቅርጫፍ በሀሰተኛ ማንነትና የነዋሪነት መታወቂያ በተከሳሹ ስም በተከፈተ ሂሳብ ገቢ እንዲሆን መደረጉ ተጠቅሷል።
ተከሳሹ ደግሞ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 8 በሀሰተኛ ማንነት ባወጣው ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ሃዩ ቅርጫፍ በከፈተው ሂሳብ ውስጥ ገቢ የተደረገለትን 10 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ወደ ተለያዩ ግለሰቦች ሂሳብ ማስተላለፉ በክሱ ላይ ተመላክቷል።
ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ዝርዝር ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል።
የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ እንዲከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።
ፍርድ ቤቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 3 መሰረት የወንጀል አፈጻጸምና የደረሰውን ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ተከሳሹ ከለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 8 በሀሰተኛ ማንነት የነዋሪነት መታወቂያ በመውሰድ በአዳማ ሃዩ ቅርጫፍ የባንክ ሂሳብ በመክፈት 10 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ገቢ የተደረገለትና ገንዘቡን ወደተለያዩ ግለሰቦች ያስተላለፈ መሆኑን በመገንዘብ የወንጀል ደረጃውን መካከለኛ የወንጀል ደረጃ በመመደብ ተከሳሹ ያቀረበው የተለያዩ የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶች በመያዝ ከሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲቆጠብ ለማስተማር በሚል በሁለቱም ክስ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እና በዕርከን 8 መሰረት በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ የተወሰነበትን የእስራት ቅጣት እንዲያስፈጽም መታዘዙን ኤፍቢሲ ዘግቧል ።
ተከሳሹ የተጣለበትን የገንዘብ ቅጣት ለመንግስት ገቢ እንዲያደርግ የፍትህ ሚኒስቴር ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አልሻራዲ ጋር ውይይት አካሄዱ
****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አልሻራዲ ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
ውይይቱ በአቅም ግንባታ ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሀብት ማስመለስ እንዲሁም በሙስና መከላከል ላይ በጋራ ለመስራት ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ በቀጣይ የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።

በህገ-ወጥ መንገድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ጥፍጥፍ ወርቅ ይዞ ሲዘዋወር የተያዘው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት
****
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 21/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በህገ-ወጥ መንገድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ጥፍጥፍ ወርቅ ይዞ ሲያዘዋውር በፍተሻ በተያዘው ግለሰብ ላይ በከባድ ሙስና እና የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ ማዕድን በተፈጥሮዓዊ ሁኔታዉ መያዝ ወንጀል ክስ መሰረተበት፡፡
በዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ አማረ ዮሃንስ በተባለው ተከሳሽ ላይ የወንጀል የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክስ ተመስርቶበታል፡፡
በ1ኛ ክሱ ላይ ተከሳሽ አንድ የመንግስት ሠራተኛ በኃላፊነቱ ወይም በሥራ ግዴታዉ ማድረግ የሚገባዉን እንዳያደርግ በማሰብ የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡40 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሀገር ዉስጥ በረራ በሚባለዉ ቦታ ተከሳሽ በብርበራ ከለበሰዉ ጃኬት ዉስጥ የተያዘዉን ሶስት የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉ የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ ሲያዘዋውር በፖሊስ አባላት ሲያዝበት በቦታዉ የነበረዉ የሻምበል አዛዥ የሆነዉን የዐቃቤ ሕግ ምስክር የሆኑትን ንግድ ፍቃድም የለኝም፣ ነጋዴም አይደለሁም፣ የተያዘዉን ወርቅ ግማሹን ልስጥክ እና ልቀቀኝ በማለት የተያዘዉን ወርቅ ብዛት ግማሽ በጉቦ ያቀረበ በመሆኑ በፈፀመው ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሷል፡፡
በተመሳሳይ በ2ኛ ክሱ ተከሳሽ ከላይ በ1ኛ ክስ ዉስጥ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በቦታዉ በመደበኛ ስራቸዉ ላይ የነበሩት የፖሊስ አባላት ተከሳሽን አካላዊ ፍተሻ ሲፈትሹ ምንም አይነት የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ በለበሰው ጃኬት ዉስጥ ሶስት ጥፍጥፍ ወርቅ የተለያዩ የክብደት መጠን ያላቸዉን የሶስቱ ጥፍጥፍ ወርቅ በድምሩ 1‚010.95 ግራም የሆነ ጥፍጥፍ ወርቅ የዋጋ ግምታቸዉ 3 ሚሊዮን 189 ሺ 506.32 ብር የሆነዉን ወርቅ የከበረ ማዕድን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ በፍተሻ የተገኘ በመሆኑ የፀና ፍቃድ ሳይኖረዉ ማዕድን በተፈጥሮዓዊ ሁኔታዉ መያዝ ወንጀል መከሰሱን ከፍትህ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ተከሳሽ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት መቃወሚያ የለኝም በማለት ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ ለማሰማት ለመጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡