Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ክስ ለኒውዮርክ ግዛት 355 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ተወሰነ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 10/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ክስ ለኒውዮርክ ግዛት 355 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንዲከፍሉ መወሰኑ ተገልጿል።

ትራምፕ ያላቸውን ንብረት በተመለከተ ለባንኮች ሐሰተኛ መረጃዎችን ሰጥተዋል የሚለውን ጨምሮ ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸው ነበር።

ብያኔውን ያስተላለፉት ዳኛ አርተር ኢንጎሮን ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም ትራምፕም ሆነ ድርጅታቸው ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኒውዮርክ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዳይጠይቁ እንዲሁም በኒውዮርክ በሚገኙ ኩባንያወቻቸው ዳይሬክተር ሆነው እንዳያገለግሉም እግድ አስተላልፈውባቸዋል።

ከሳቸው በተጨማሪም ሁለቱ ልጆቻቸው ኤሪክ ትራምፕ እና ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር በኒውዮርክ በሚገኙ በትራምፕ ድርጅቶች ላይ በሥራ ኃላፊነት እንዳይቀመጡም እግድ ተጥሎባቸዋል።

ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል ተደጋጋሚ ማጭበርበሮች፣ ሐሰተኛ የንግድ መዝገቦችን በማቅረብ፣ ሀሰተኛ የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማቅረብ እና የኢንሹራንስ ማጭበርበር ክሶች ይገኙባቸዋል።

በተጨማሪም ትራምፕ እና ኩባንያቸው ለባንኮች እና ኢንሹራንስ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የትራምፕ ንብረት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ያካተተ ተመን አቅርበዋል የሚልም ተካቶበታል።

በኒውዮርክ ሪል ስቴት ዘርፍ ከፍተኛ ሀብት ያፈሩት ትራምፕ በበኩላቸው በብያኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁም መናገራቸውን ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሲቪል ማህበራት የፀረ-ሙስና ትግሉ አጋር መሆን ይጠበቅባቸዋል!

****************

ሙስናን በመከላከል ረገድ የምክር ቤት አባላት አስፈፃሚ አካልን የመከታተልና የመቆጣጠር ሚናቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 11/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለከተማው ምክር ቤት አባላት "ሙስናን በመከላከል ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና" በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናዉ የአዲስ አበባ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ እንደገለፁት ሙስና በሞራል ድቀት ምክንያት የሚከሰት የአለምዓቀፍ ስጋትና የሰላም እጦት መነሻ ምክንያት እንደሆነ ገልፀዉ፥ ሙስና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳጣ ሁሉንም ሀገራት የሚጎዳ ወንጀል ነዉ ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለዉም የከተማው ምክር ቤት ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአስፈጻሚ አካላትን የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመመርመር ሚናቸዉን በመወጣት የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ስልጠናዉን የሰጡት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ በበኩላቸዉ ሙስና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግር የሚያስከትልና ሀገርን ወደኋላ የሚያስቀር ትውልድን የሚያመክን ወንጀል መሆኑን ገልፀዉ፥ የምክር ቤት አባላቱም የፀረ-ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው አመራር በመስጠትና የመንግስት ተቋማት ውስጥ ግልፀኝነትና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን ሚናቸውን አጠናክረዉ መቀጠል እንደሚገባ ገለፃ አድርገዋል።

የምክር ቤት አባላቱ የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን፣ የዲሞክራሲ ስርዓትና ባህል እንዲጎለብት የማድረግ፣ ተቋማትን እንደየባህሪያቸዉ መደገፍና አቅም የማሳደግ፣ የሙስና መረጃ ማግኛ መንገዶችን ማጠናከርና የፀ-ሙስና ትምህርቶች በስፋት ህብረተሰቡ ጋር እንዲደርሱ የማድረግ፣ የዜጎችን አመኔታ የሚያሳድጉ ተግባራትን ማጠናከርና አርአያ የመሆን ሚናቸዉን ለመወጣት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
በሙስና ወንጀል የተከሰሰው የፍርድ ቤት ዳኛ ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ታዘዘ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 12/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል የተከሰሰው የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛና የኢንስፔክሽ ኃላፊ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አዘዘ።

ተከሳሹ በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ የሰጠውን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ተከሳሹ የሙስና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህም በክሱ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ሀ/ማርያም ገ/መስቀል የተባለ የግል ተበዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ እየተከታተለ ባለበት ወቅት ማለትም በ2014 ዓ.ም ላይ ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ "እኔ በስራዬ ዳኛ ነኝ "የአንተን ጉዳይ እያዩ የሚገኙትን 3 ዳኞች መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብሬያቸው ስለተማርኩኝ አውቃቸዋለሁኝ" በማለት ማግባባቱ በክሱ ዝርዝር ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም "ከዳኞቹ ጋር ተነጋግሬ በነፃ እንዲለቁህ አደርጋለሁ'' በማለት የግል ተበዳዩን ካናገረ በኋላ በድጋሚ ወደ ተበዳይ በመሄድ "ዳኞቹን አናግሬ በብይን በነፃ እንድትለቀቅ 1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር ጠይቀውኛል በማለት እንዲሁም "እኔ ተደራድሬ 600 ሺህ ብር አስደርጋለሁ" በማለት የማግባባት ስራ ሰርቷል በሚል ዐቃቤ ሕግ በክሱ ዝርዝር ላይ አመላክቷል።

በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ላይ ደግሞ "ዳኞቹ አሁን በቅድሚያ 400 ሺህ ብር ካልተከፈለን ምንም አናደርግም ብለዋል" በአስቸኳይ ብር አምጣ በማለት አሳሳች ነገር በመናገር እና የተበዳይን የተሳሳተ ዕምነት በመጠቀም አታሎ 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከሆነው የግል ተበዳይ ወንድም ከሆነው ግለሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም 400 ሺህ ብር የተቀበለ በመሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሹም ችሎት ቀርቦ ማንነቱን ካረጋገጠ በኋላ የቀረበበት ክስ ዝርዝር ደርሶት በንባብ እንዲሰማ ተደርጓል።

ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ዛሬ የተሰየመ ቢሆንም ተከሳሹ ግን የክስ መቃወሚያ እንደሌለው ለችሎቱ ገልጿል።

ተከሳሹ የተከሰሰበት ድንጋጌ የዋስትና መብት የሚያስከለክል መሆኑን ተከትሎ የዋስትና መብቱ ተገድቦ በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ታዟል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን ጠቅሶ ለፍርድ ቤቱ የዕምነት ክህደት ቃል ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲሰሙለት ፍርድ ቤቱን መጠየቁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱም በተከሳሹ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለየካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ክልል ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ሌብነትን በሚመለከት ያስተላለፋት መልዕክት