Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.92K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
ሙስና የሃገርን ሁለንተናዊ ዕድገት በመግታት ለውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳርግ በመሆኑ የፀረ-ሙስና ትግሉ ይበልጥ መጠናከር አለበት - ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና የስልጠና ባለሙያዎች ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ እንደገለፁት ሙስና በምንም መልኩ ይሁን ጠንክሮ መስራትን የሚያኮስስ፣ ሳይሰሩ መብላትን የሚያበረታታ፣ መረጋጋትን የሚፈታተን በጥቅሉ የሃገርን ሁለንተናዊ ዕድገትን በመግታት ለውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳርግ በመሆኑ የምናካሄደውን የፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ማጠናከር እንጂ በይደር የምናቆየው ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡

የፅ/ቤት ኃላፊዋ አክለውም ተቋማችን ከፍተኛ የሃገር ሃብት የሚፈስበት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችና የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን የሚመራ፣ የሚሰራ በመሆኑ ለሙስና በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ለመዋጋት የሚያሥችሉ የፀረ -ሙስና እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ተቋማችን ከሙስና በፀዳ መልኩ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ ለማስቻል በፍፁም ታማኝነትና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ፅ/ቤት ኃላፊዋ አሳስብዋል፡፡

ስልጠናውን የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ኪዳነ ምህረት እና የሥልጣና ባለሙያ አቶ ካሳነው ጤናው የሰጡ ሲሆን፥ በሥነ-ምግባራዊ አመራር ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ መልእክት ያሥተላለፉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱልጁዋድ መሀመድ እንዳሉት በኮሚሽኑ ዴስክ ኃላፊና ባለሙያ የተሰጠን ስልጠና ለፀረ-ሙስና ትግሉ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው፥ በተሰጠን ስልጠና በቂ ግንዛቤ አግኝተናል ብለዋል፡፡

በስነ-ምግባራዊ አመራር እና ውሳኔ አሰጣጥ አርዕስት የተሰጠን ስልጠና እራሳችንን እንድናይ አድርጎናል ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይም የአመራር እውቀታችንን በራሳችን ጥረት ማሳደግ፣ ራስን ማብቃት፣ አረዓያና ውጤታማ መሆን ይገባናል ማለታቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከአሁን በፊት የምናውቀውን እንድናስታውስ እንዲሁም ተጨማሪ እውቀት ያገኘንበት ስልጠና ነው፡፡ በቀጣይነት በፀረ-ሙስና ትግሉ የራሳችንን ሚና እንጫወታለን ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይ ስልጠናው የተሟላ እንዲሆን ለባለሙያዎችና ለሰራተኞች መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ ነው

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰሞኑን ገምግሟል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፥ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራው ከታሰበው በላይ ቁጥሩ የሰፋና ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ ነው ብለዋል።

ለትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሂደቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰብሳቢነት የሚሳተፍበትና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ዲግሪና ከዲግሪ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽነር ኃይሌ (ዶ/ር) አስታውቀው፥ ከዲግሪ በታች የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሠራተኞች ማስረጃ የማረጋገጡ ሥራ በቀጣይ የትግበራ አካል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ሥራው በአምስት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተሠራ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነር መኩሪያ (ዶ/ር)፥ የፌዴራል ተቋማትን፣ የሚኒስትሮችና የተጠሪ ተቋማትን ማስረጃ ማጥራት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሆኖ ቢሠራ የተሻለ እንደሚሆን በማመን ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።

እንደርሳቸው ማብራሪያ በሁለተኛ ምዕራፍ የመጨረሻው ደረጃ ሥራ ወደ መገባደዱ ሲጠጋ የሕግ አውጭ፣ ተርጓሚ አካልና የዴሞክራሲ ተቋማት መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ ነው። በመቀጠልም በሶስተኛ ምዕራፍ የክልል መንግሥታት የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ ለመተግበር በእቅድ ተይዟል።

ሦስቱ ምዕራፎች ሲጠናቀቁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስረጃ ማጣራት ይከናወናል። በተለይም ኮሚቴው የመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ማስረጃ ማጥራት እቅድ አውጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ ለመንግሥት ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል። ይህንን ራስ ምታት ለማስቀረት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በሲስተም የማገናኘት ሥራ መካተቱን አንስተዋል። በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣንም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ማስረጃዎች የሚቀናጅበት ሥራ መሠራቱን፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናም እንዲናበብ መደረጉን አመልክተዋል።

በኮሚሽኑ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍት ዌር እየለማ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መኩሪያ፥ ዋና ዋና የሲቪል ሰርቪስ ሥራዎችን ይዞ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲናበብ ተደርጎ ለትግበራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጥራትና አስተማማኝነቱን አጣርቶ ማረጋገጡንም መጠቆማቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያዎች ነፃና ገለልተኛ በመሆን የፀረ-ሙስና ህጎች እንዲከበሩ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተገለፀ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በየደረጃው ለሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች ለ4 ተከታታይ ቀናት ሲሰጠው የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያዎች ነፃና ገለልተኛ በመሆን የፀረ-ሙስና ህጎች እንዲከበሩ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

እያንዳንዱ ስራዎቻችን ትውልድ ግንባታ ላይ ማዕከል ያደረገ መሆን እንደሚገባውና የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎችም ከተለያዩ ተቋማት ጋር መስራት እንዳለባቸው ም/ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ ተናግረዋል። ከሰልጣኞች ከሰው ኃይል ማሟላት፣ ከግብዓትና ሌሎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ኮሚሽነሩ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው እንደ ኮሚሽን የውስጥ አቅምን መገንባት ስላለብን ቅድሚያ ለሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች አቅም ሊሆኑ የሚችሉ ስልጠናዎች መሰጠቱ አስፈላጊም፣ ተገቢም ነው ብለዋል።

የኮሚሽኑ ተግባራት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሙስናን መከላከል ስለሆነ ሙስና ሊፈፀምባቸው ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮችን በጥናት እየለየንና እየዘጋን መሄድ አለብን ሲሉ ም/ኮሚሽነር አሰግደው ተናግረዋል።

አክለውም ሙስና ተፈፅሞበታል ወይም ሙስና ሊፈፀምበት ነው ተብሎ በሚቀርብ ጥቆማ መሰረት በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ማስቆም ይኖርብናል ብለዋል።

ስልጠናው በሙስና ተጋላጭነት አሰራር ጥናት፣ ምንነትና አዘገጃጀት፣ በጥቅም ግጭት፣ በሥነምግባር ግንባታና መልካም አስተዳደር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ በሴክተር መ/ቤቶች፣ በኮሌጆች፣ በሆስፒታሎች፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ በክፍለ ከተሞችና በወረዳዎች ላይ የሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ዳሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የስልጠናው ተሳታፊ እንደነበሩ ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በስልጠናው የተሳተፉ ቡድን መሪዎችና ዳይሬክተሮችም ስልጠናው ለቀጣይ ስራዎቻቸው የተሻለ አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ክስ ለኒውዮርክ ግዛት 355 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ተወሰነ

****

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 10/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማጭበርበር ክስ ለኒውዮርክ ግዛት 355 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንዲከፍሉ መወሰኑ ተገልጿል።

ትራምፕ ያላቸውን ንብረት በተመለከተ ለባንኮች ሐሰተኛ መረጃዎችን ሰጥተዋል የሚለውን ጨምሮ ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸው ነበር።

ብያኔውን ያስተላለፉት ዳኛ አርተር ኢንጎሮን ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪም ትራምፕም ሆነ ድርጅታቸው ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኒውዮርክ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዳይጠይቁ እንዲሁም በኒውዮርክ በሚገኙ ኩባንያወቻቸው ዳይሬክተር ሆነው እንዳያገለግሉም እግድ አስተላልፈውባቸዋል።

ከሳቸው በተጨማሪም ሁለቱ ልጆቻቸው ኤሪክ ትራምፕ እና ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር በኒውዮርክ በሚገኙ በትራምፕ ድርጅቶች ላይ በሥራ ኃላፊነት እንዳይቀመጡም እግድ ተጥሎባቸዋል።

ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል ተደጋጋሚ ማጭበርበሮች፣ ሐሰተኛ የንግድ መዝገቦችን በማቅረብ፣ ሀሰተኛ የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማቅረብ እና የኢንሹራንስ ማጭበርበር ክሶች ይገኙባቸዋል።

በተጨማሪም ትራምፕ እና ኩባንያቸው ለባንኮች እና ኢንሹራንስ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የትራምፕ ንብረት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ያካተተ ተመን አቅርበዋል የሚልም ተካቶበታል።

በኒውዮርክ ሪል ስቴት ዘርፍ ከፍተኛ ሀብት ያፈሩት ትራምፕ በበኩላቸው በብያኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁም መናገራቸውን ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሲቪል ማህበራት የፀረ-ሙስና ትግሉ አጋር መሆን ይጠበቅባቸዋል!

****************

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡