Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
9.91K subscribers
10.3K photos
244 videos
32 files
3.04K links
Download Telegram
በአዲስ አበባ የፍርድ ቤት ዳኛ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተበት

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የኢንስፔክሽ ኃላፊ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙሰና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላክል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ዝርዝር ክስ አቅርቦበታል።

በዚህም ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ሀ/ማርያም ገ/መስቀል የተባለ የግል ተበዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ መከታተል በነበረበት ጊዜ ተከሳሹ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ተበዳይ ወደ ሚገኝበት የፌደራል ማረሚያ ቤት በመሄድ "እኔ በስራዬ ዳኛ ነኝ የአንተን ጉዳይ እያዩ የሚገኙትን 3 ዳኛዎች መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብሬያቸው ስለተማርኩኝ አውቃቸዋለሁኝ" በማለት ማግባባቱ በክሱ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም "ከዳኞቹ ጋር ተነጋግሬ በነፃ እንዲለቁህ አደርጋለሁ'' በማለት የግል ተበዳዩን ካናገረው በኋላ በድጋሚ ወደ ተበዳይ በመሄድ "ዳኞቹን አናግሬ በብይን በነፃ እንድትለቀቅ 1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር ጠይቀውኛል በማለትና "እኔ ተደራድሬ 600 ሺህ ብር አስደርጋለሁ" ማለት ማግባባቱም በክሱ ተመላክቷል።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ላይ "ዳኞቹ አሁን በቅድሚያ 400 ሺህ ብር ካልተከፈለን ምንም አናደርግም ብለዋል" በአስቸኳይ ብር አምጣ በማለት አሳሳች ነገር በመናገር እና የተበዳይን የተሳሳተ ዕምነት በመጠቀም አታሎ 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከሆነው የግል ተበዳይ ወንድም በሆነው ግለሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም 400 ሺህ ብር የተቀበለ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተከሳሹም ችሎት ቀርቦ ማንነቱን ካረጋገጠ በኋላ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው ተደርጓል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለፊታችን ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ ይገባል

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ ገለጸ።

የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ የስራ አመራሮች ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የቦርዱ ሊቀመንበር ሴናቡ ዲካቴ ህብረቱ እ.አ.አ በ2003 ሙስናን ለመዋጋት ያወጣው ስምምነት በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጉ የሚፈለገው ውጤት አለመምጣቱን አንስተዋል።

ቦርዱ የአፍሪካ ህብረት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላል ብሎ ያወጣውን ስምምነት አባል ሀገራት ፈርመው እንዲያጸድቁ ግፊት እያደረገ ነው ብለዋል።

ስምምነቱን ተቀብለው ያልፈረሙ ስድስት የህብረቱ አባል ሀገራት መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ሀገራቱን ለማስፈረምና ወደ ትግባራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ መሪዎች በአህጉሪቱ ትልቅ ፈተና የሆነውን ሙስና ለመከላከል በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የቦርዱ ዋና ፀሐፊ ቻሪቲ ቺሙኒ በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በህብረቱ አባል ሀገራት የወጣው ስምምነት 20 ዓመቱን የደፈነ ቢሆንም የሚፈለገው ውጤት አለመምጣቱን አንስተዋል።

ይህም በአህጉሪቱ የሚፈለገው መሰረተ ልማት እንዳይሟላ ከማድረግ ባለፈ ተጠያቂነት እንዳይሰፍንም አድርጓል ነው ያሉት።

በመሆኑም ህብረቱ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያወጣቸው ህጎችና ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑና የተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን የመሪዎቹ ቁርጠኝነት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በመሰረተ ልማት የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካ እውን የምትሆነው አህጉሪቱ ያላትን ሀብት ለሚፈለገው ዓላማ እንዲውል በማድረግ ነውም ብለዋል።

በተለይም የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት እያንዳንዱ ሀገር በሙስና መከላከል ላይ ጠንካራ አቋም ሊይዝ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሙስናን የመከላከል ስራ በአንድ ተቋም ብቻ ሊሰራ የማይችል በመሆኑ በተለይም ዜጎች ሙስናን በማጋለጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ መጠናቀቁ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና እና ብልሹ አሰራር የጋራ ጠላታችን በመሆኑ በጋራ እንታገል!

****

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ሙስና የሃገርን ሁለንተናዊ ዕድገት በመግታት ለውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳርግ በመሆኑ የፀረ-ሙስና ትግሉ ይበልጥ መጠናከር አለበት - ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና የስልጠና ባለሙያዎች ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ እንደገለፁት ሙስና በምንም መልኩ ይሁን ጠንክሮ መስራትን የሚያኮስስ፣ ሳይሰሩ መብላትን የሚያበረታታ፣ መረጋጋትን የሚፈታተን በጥቅሉ የሃገርን ሁለንተናዊ ዕድገትን በመግታት ለውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳርግ በመሆኑ የምናካሄደውን የፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ማጠናከር እንጂ በይደር የምናቆየው ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡

የፅ/ቤት ኃላፊዋ አክለውም ተቋማችን ከፍተኛ የሃገር ሃብት የሚፈስበት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችና የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን የሚመራ፣ የሚሰራ በመሆኑ ለሙስና በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ለመዋጋት የሚያሥችሉ የፀረ -ሙስና እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ተቋማችን ከሙስና በፀዳ መልኩ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲወጣ ለማስቻል በፍፁም ታማኝነትና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ፅ/ቤት ኃላፊዋ አሳስብዋል፡፡

ስልጠናውን የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ኪዳነ ምህረት እና የሥልጣና ባለሙያ አቶ ካሳነው ጤናው የሰጡ ሲሆን፥ በሥነ-ምግባራዊ አመራር ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ መልእክት ያሥተላለፉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱልጁዋድ መሀመድ እንዳሉት በኮሚሽኑ ዴስክ ኃላፊና ባለሙያ የተሰጠን ስልጠና ለፀረ-ሙስና ትግሉ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው፥ በተሰጠን ስልጠና በቂ ግንዛቤ አግኝተናል ብለዋል፡፡

በስነ-ምግባራዊ አመራር እና ውሳኔ አሰጣጥ አርዕስት የተሰጠን ስልጠና እራሳችንን እንድናይ አድርጎናል ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይም የአመራር እውቀታችንን በራሳችን ጥረት ማሳደግ፣ ራስን ማብቃት፣ አረዓያና ውጤታማ መሆን ይገባናል ማለታቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከአሁን በፊት የምናውቀውን እንድናስታውስ እንዲሁም ተጨማሪ እውቀት ያገኘንበት ስልጠና ነው፡፡ በቀጣይነት በፀረ-ሙስና ትግሉ የራሳችንን ሚና እንጫወታለን ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይ ስልጠናው የተሟላ እንዲሆን ለባለሙያዎችና ለሰራተኞች መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ ነው

****************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ9/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰሞኑን ገምግሟል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፥ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራው ከታሰበው በላይ ቁጥሩ የሰፋና ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ ነው ብለዋል።

ለትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሂደቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰብሳቢነት የሚሳተፍበትና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ዲግሪና ከዲግሪ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽነር ኃይሌ (ዶ/ር) አስታውቀው፥ ከዲግሪ በታች የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሠራተኞች ማስረጃ የማረጋገጡ ሥራ በቀጣይ የትግበራ አካል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ሥራው በአምስት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተሠራ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነር መኩሪያ (ዶ/ር)፥ የፌዴራል ተቋማትን፣ የሚኒስትሮችና የተጠሪ ተቋማትን ማስረጃ ማጥራት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሆኖ ቢሠራ የተሻለ እንደሚሆን በማመን ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።

እንደርሳቸው ማብራሪያ በሁለተኛ ምዕራፍ የመጨረሻው ደረጃ ሥራ ወደ መገባደዱ ሲጠጋ የሕግ አውጭ፣ ተርጓሚ አካልና የዴሞክራሲ ተቋማት መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ ነው። በመቀጠልም በሶስተኛ ምዕራፍ የክልል መንግሥታት የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ ለመተግበር በእቅድ ተይዟል።

ሦስቱ ምዕራፎች ሲጠናቀቁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስረጃ ማጣራት ይከናወናል። በተለይም ኮሚቴው የመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ማስረጃ ማጥራት እቅድ አውጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ ለመንግሥት ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል። ይህንን ራስ ምታት ለማስቀረት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በሲስተም የማገናኘት ሥራ መካተቱን አንስተዋል። በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣንም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ማስረጃዎች የሚቀናጅበት ሥራ መሠራቱን፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናም እንዲናበብ መደረጉን አመልክተዋል።

በኮሚሽኑ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍት ዌር እየለማ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መኩሪያ፥ ዋና ዋና የሲቪል ሰርቪስ ሥራዎችን ይዞ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲናበብ ተደርጎ ለትግበራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ጥራትና አስተማማኝነቱን አጣርቶ ማረጋገጡንም መጠቆማቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡