ሌብነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ አቋም አለዉ - አቶ ጥላሁን ከበደ
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሌብነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለፁ፡፡
"ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ሀብት የመፍጠር ጉዞዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ዉይይት ተካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም እያጋጠመ ያለውን የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት እና የመንገድና የመብራት መሠረተ ልማት አለመሟላት፣ የሥራ አጥነትና የማህበራዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሠላምና ፀጥታ ችግሮች በጉልህ የተነሱ ሲሆን መንግስት ለችግሮቹ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ዉይይት መድረኩን የመሩት አቶ ጥላሁን ከበደ ከህዝቡ የተነሱት ችግሮች ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች በተለይም የመልካም አስተዳደር እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ችግሮች መሆናቸውን በመጠቀስ መንግስት እነዚህን ጥያቄዎች ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም እንዳለዉ ገልፀዋል።
የኑሮ ዉድነትና የሥራ አጥነት ችግሮችንም ለመፍታት መንግስት የጀመራቸው ተግባራት ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ የሕብረተሰቡ የሥራ ባህልን መቀየርና ፈጥኖ ወደ ተግባር መግባት ይጠበቃል ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃብታሙ ካፕትን ከሕዝቡ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተለይም የኢ-ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ችግር ለመፍታ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቤንች ማጂ ዞን ሚዛን አማን በተካሄደው ሕዝባዊ ዉይይት ላይ የክልሉ መንግስት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልሉ እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የተውጣጡ ከ500 በላይ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተሳታፊዎች መሆናቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

የቀድሞ የአ/አ ከተማ ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር እነ ኤልቤቴል ከ44 ሚሊየን ብር በላይ ግለሰቦችን በማታለል ከባድ የሙስና ክስ ቀረበባቸው
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የቀድሞ የአ/አ ከተማ ከንቲባ የፕሮቶኮል ዳይሬክተር እነ ኤልቤቴል ከ44 ሚሊየን ብር በላይ ግለሰቦችን በማታለል ከባድ የሙስና ክስ ቀረበባቸው።
ክስ ከተመሰረተባቸው 12 ተከሳሾች መካከል 1ኛ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የፕሮቶኮል ኃላፊ የነበረችው ኤልቤቴል ሃብቴ፣ 2ኛ ፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓ/ህግ ዘርፍ ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር ፍቅሩ ኦላኒ፣ 3ኛ የአ/አ አሽከርካሪ ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቂርቆስ ክ/ከተማ ጽ/ቤት የተሸከርካሪ መረጃ አጠናካሪ ባለሙያ ዘሪሁን ሞገስ እንዲሁም የዚሁ ተቋም የቴክኒክ ባለሙያ የሆኑት አላዩ ባሳዝን እና ቴዎድሮስ አበበ ይገኙበታል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ለመደበቅ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚሉት ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸዋል።
ክሱ የተመሰረተባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በአንደኛው ክስ ላይ 1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ በቀረበው ዝርዝር ክስ እንደተመላከተው 3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች የአሽከርከሪ ተሸከርካሪ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በ2010 ዓ.ም ያወጣውን መመሪያና አሰራር በመተላለፍ በሌላ ሰው ስም የተመዘገበ የተሽከርካሪ የሻንሲ ቁጥር በመቀየር ሊብሬ እና ሰሌዳ ቁጥር በህገ-ወጥ መንገድ 1ኛ፣ 6ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች እንዲወስዱ ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል።
1ኛ፣ 6ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ደግሞ የሻንሲ ቁጥሩን ያስቀየሩትና ሊብሬና ታርጋ በህገወጥ መንገድ የወሰዱበትን ተሽከርካሪን ለ3ኛ ወገን በማስያዥያነት በመስጠት የማይገባቸውን 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ብልጽግና በማግኘት በግል ተበዳዮች ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ በዋና የሙስና ወንጀል አድራጊነት እና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት በመሆን ስልጣን አላግባብ መገልገል ከባድ ሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በሁለተኛው ክስ ደግሞ በ1ኛ፣ በ2ኛ፣ 6ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ በቀረበው ክስ እንደተመላከተው የተጠቀሱት ተከሳሾች በግንቦት ወር 2014 ዓ.ም የግል ተበዳይ ከሆኑት ከ1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጋር በመተዋወቅ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ ሚካኤል አካባቢ ካፌ ውስጥ ከግል ተበዳይ ጋር በመገናኘት 1ኛ ተከሳሽ ከንቲባ ጽ/ቤት የምትሰራ መሆኑን እና " ቢ.ኢ.ኢ.ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ድርጅት በቤተሰብ አቋቁመን ከውጭ ሀገር እቃ እናስመጣለን " በማለት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ስም በመጥቀስ "ጨረታ ከነሱ ጋር እናመቻቻለን፣ ወንድሜ እቃ ከውጭ እያመጣ አትራፊ ነው ከኛ ጋር ስሩ" በማለት አሳሳች የማግባቢያ ቃላት መጠቀሟ በክሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም ተከሳሾቹ አሳሳች ፍሬ ነገር በመግለፅ የግል ተበዳይዎችን እምነት እንዲጨምር በማድረግ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የተጠቀሱ የግል ተበዳይ የሆኑ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች አዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሀዘን በመኖሪያ ቤታቸዉ ተቀምጠው እያለ 1ኛ ተከሳሽ ቤታቸው በመሄድ የጎማ ጨረታ ኤልሻዳይ የተባለ ድርጅት ለማቅረብ አሸንፈን ከፍተኛ ገንዘብ አስይዘን 14 ሚሊየን ብር የጎደለን ስለሆነ ያስያዝነዉን ከፍተኛ ገንዘብ ልንበላ ነዉ አብረን ስለምንሰራ ይሄንን የጎደለንን ገንዘብ ስጡን በማለት የጠየቀች መሆኑ በክሱ ተዘርዝሯል።
ለመተማመኛ በሚል ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር አ.አ የሆነ ኮድ 02-B81421 ተሽከርካሪ ገዝተን 200 ሺህ ብር የቀረብንን ከፍለን የራሳችን የምናደርገዉ ነዉ በማለት የሌላ ግለሰቦችን ንብረት የራሳቸው ለማስመሰል 3 ተሽከርካሪዎችን ለግል ተበዳዮቹ ያቀረቡ መሆኑ በክሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም 1ኛ፣ 2ኛ እና 12ኛ ተከሳሾች በ2015 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የ3ኛ እና 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን ልጅሽን አምጪ ወይም አድራሻዉን ንገሪን እና ያስመታዉን ቼክ ያምጣ ያለበለዚያ ችግር ይደርስበታል በማለት በማስፈራራት ቤት በር ላይ መኪና ውስጥ ሆነዉ በተደጋጋሚ እየተመላላሱ ሌሊቱን ሙሉ በማስፈራራት ያደሩ መሆኑ በክሱ ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የግል ተበዳይ የሆኑትን ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተገለፁትን የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የሆኑትን የግል ተበዳዮችን በማታለል፣ በማስፈራራት ጭምር የሌላ ሰው ንብረት የሆኑትን ተሸከርካሪዎች በማስያዝ በሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አታለዉ ከግለሰቦቹ በተለያዩ መጠኖች አጠቃላይ 14 ሚሊዮን ብር ገንዘብ በመውሰድ በግል ተበዳዮች ላይ ጉዳት ያደረሱ መሆናቸዉ ተጠቅሶ በከባድ የአታላይነት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
በ3ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ ከ6ኛ እስከ 12ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱተሰ ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሳቸዉ ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት በማሰብ የካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከ5ኛ እስከ 13ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱትን የግል ተበዳይ የሆኑ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን በተለያየ ቀን እና ቦታ በማግኘት 6ኛ ተከሳሽ የኬ.ኬ አስመጪና ንግድ ሥራ የተባለ ድርጅት ባለቤት ሆኖ ጀነሬተሮች፣ የህትመት እቃዎች፣ የኪችን እቃ፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ጌጣጌጦች ከውጭ ሀገር በማስመጣት ስራ እንደሚሰራ በሀሰት መናገሩ በክሱ ተጠቅሷል።
1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ደግሞ ከ6ኛ እስከ 12ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ጋር በመሆን የግል ተበዳይ የሆኑትን ግለሰቦችን የመኪና ጎማን ጨምሮ የተለያዩ እቃዎችን ከውጭ እናስመጣለን በማለት በማታለል ንግድ ፍቃድ በማሳየት፣ ያሳገዱትን እና ያዘጉትን የተለያዩ ቼኮችን ለመተማመኛ የሚል በመስጠት አታለዉ 30 ሚሊየን 689 ሺህ ብር የወሰዱ እና በግል ተበዳዮቹ መታለላቸውን አውቀው ገንዘባቸው ስጡን ብለው ሲጠይቁ ለውይይት በማለት በሆቴሎች በመጥራት ሲያስፈራሯቸው እንደነበር በክሱ የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ ከባድ የአታላይነት የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
በ 4ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ፣ 9ኛ እና 10ኛ ተከሳሾች የቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም ከግል ተበዳዮች በማታለል ያገኙትን 44 ሚሊዮን 689 ሺህ ብር በተለያዩ መጠኖች በተለያየ ግዜ ወጪ በማድረግ ለራሳቸዉ ጥቅም ያዋሉ በመሆኑ ምንጩ እንዳይታወቅ ወይም እንዲደበቅ ያደረጉ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አድርጎ ማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ተከሳሾቹ ችሎት ቀርበው ክሱ የደረሳቸው ሲሆን የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለየካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም መቀጠሩን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Telegram
Federal Ethics And Anti- Corruption Commission
Use This Link For More Information https://twitter.com/EthiopiaFeacc https://www.youtube.com/channel/UCO_WiCAiDIkMMwqsZGK47nw/?guided_help_flow=5/ https://www.facebook.com/feaccOfficial/
በአዲስ አበባ የፍርድ ቤት ዳኛ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተበት
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የኢንስፔክሽ ኃላፊ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙሰና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላክል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ዝርዝር ክስ አቅርቦበታል።
በዚህም ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ሀ/ማርያም ገ/መስቀል የተባለ የግል ተበዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ መከታተል በነበረበት ጊዜ ተከሳሹ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ተበዳይ ወደ ሚገኝበት የፌደራል ማረሚያ ቤት በመሄድ "እኔ በስራዬ ዳኛ ነኝ የአንተን ጉዳይ እያዩ የሚገኙትን 3 ዳኛዎች መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብሬያቸው ስለተማርኩኝ አውቃቸዋለሁኝ" በማለት ማግባባቱ በክሱ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም "ከዳኞቹ ጋር ተነጋግሬ በነፃ እንዲለቁህ አደርጋለሁ'' በማለት የግል ተበዳዩን ካናገረው በኋላ በድጋሚ ወደ ተበዳይ በመሄድ "ዳኞቹን አናግሬ በብይን በነፃ እንድትለቀቅ 1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር ጠይቀውኛል በማለትና "እኔ ተደራድሬ 600 ሺህ ብር አስደርጋለሁ" ማለት ማግባባቱም በክሱ ተመላክቷል።
ከዚህም በኋላ ደግሞ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ላይ "ዳኞቹ አሁን በቅድሚያ 400 ሺህ ብር ካልተከፈለን ምንም አናደርግም ብለዋል" በአስቸኳይ ብር አምጣ በማለት አሳሳች ነገር በመናገር እና የተበዳይን የተሳሳተ ዕምነት በመጠቀም አታሎ 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከሆነው የግል ተበዳይ ወንድም በሆነው ግለሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም 400 ሺህ ብር የተቀበለ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተከሳሹም ችሎት ቀርቦ ማንነቱን ካረጋገጠ በኋላ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው ተደርጓል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለፊታችን ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የኢንስፔክሽ ኃላፊ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙሰና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላክል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ዝርዝር ክስ አቅርቦበታል።
በዚህም ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ሀ/ማርያም ገ/መስቀል የተባለ የግል ተበዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ መከታተል በነበረበት ጊዜ ተከሳሹ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ተበዳይ ወደ ሚገኝበት የፌደራል ማረሚያ ቤት በመሄድ "እኔ በስራዬ ዳኛ ነኝ የአንተን ጉዳይ እያዩ የሚገኙትን 3 ዳኛዎች መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብሬያቸው ስለተማርኩኝ አውቃቸዋለሁኝ" በማለት ማግባባቱ በክሱ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም "ከዳኞቹ ጋር ተነጋግሬ በነፃ እንዲለቁህ አደርጋለሁ'' በማለት የግል ተበዳዩን ካናገረው በኋላ በድጋሚ ወደ ተበዳይ በመሄድ "ዳኞቹን አናግሬ በብይን በነፃ እንድትለቀቅ 1 ሚሊየን 200 ሺህ ብር ጠይቀውኛል በማለትና "እኔ ተደራድሬ 600 ሺህ ብር አስደርጋለሁ" ማለት ማግባባቱም በክሱ ተመላክቷል።
ከዚህም በኋላ ደግሞ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ላይ "ዳኞቹ አሁን በቅድሚያ 400 ሺህ ብር ካልተከፈለን ምንም አናደርግም ብለዋል" በአስቸኳይ ብር አምጣ በማለት አሳሳች ነገር በመናገር እና የተበዳይን የተሳሳተ ዕምነት በመጠቀም አታሎ 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከሆነው የግል ተበዳይ ወንድም በሆነው ግለሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም 400 ሺህ ብር የተቀበለ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ተከሳሹም ችሎት ቀርቦ ማንነቱን ካረጋገጠ በኋላ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው ተደርጓል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለፊታችን ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ ይገባል
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ8/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ ገለጸ።
የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ የስራ አመራሮች ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የቦርዱ ሊቀመንበር ሴናቡ ዲካቴ ህብረቱ እ.አ.አ በ2003 ሙስናን ለመዋጋት ያወጣው ስምምነት በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጉ የሚፈለገው ውጤት አለመምጣቱን አንስተዋል።
ቦርዱ የአፍሪካ ህብረት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላል ብሎ ያወጣውን ስምምነት አባል ሀገራት ፈርመው እንዲያጸድቁ ግፊት እያደረገ ነው ብለዋል።
ስምምነቱን ተቀብለው ያልፈረሙ ስድስት የህብረቱ አባል ሀገራት መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ሀገራቱን ለማስፈረምና ወደ ትግባራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ መሪዎች በአህጉሪቱ ትልቅ ፈተና የሆነውን ሙስና ለመከላከል በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የቦርዱ ዋና ፀሐፊ ቻሪቲ ቺሙኒ በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በህብረቱ አባል ሀገራት የወጣው ስምምነት 20 ዓመቱን የደፈነ ቢሆንም የሚፈለገው ውጤት አለመምጣቱን አንስተዋል።
ይህም በአህጉሪቱ የሚፈለገው መሰረተ ልማት እንዳይሟላ ከማድረግ ባለፈ ተጠያቂነት እንዳይሰፍንም አድርጓል ነው ያሉት።
በመሆኑም ህብረቱ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያወጣቸው ህጎችና ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑና የተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን የመሪዎቹ ቁርጠኝነት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
በመሰረተ ልማት የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካ እውን የምትሆነው አህጉሪቱ ያላትን ሀብት ለሚፈለገው ዓላማ እንዲውል በማድረግ ነውም ብለዋል።
በተለይም የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት እያንዳንዱ ሀገር በሙስና መከላከል ላይ ጠንካራ አቋም ሊይዝ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሙስናን የመከላከል ስራ በአንድ ተቋም ብቻ ሊሰራ የማይችል በመሆኑ በተለይም ዜጎች ሙስናን በማጋለጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ መጠናቀቁ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር የጋራ ጠላታችን በመሆኑ በጋራ እንታገል!
****
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@feac1993?_t=8jEyU0ouURa&_r=1