ሙስና የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅፋት የማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ሥርዓት ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ6/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ አበባ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በየደረጃው ከሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚ አካላት ጋር በ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርት እና በግማሽ ዓመቱ በተካሄደ ክትትልና ድጋፍ የተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ እንደገለፁት ኮሚሽኑ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን ገልፀው፥ አደረጃጀት፣ ደንቦችና መመሪያዎች አዘጋጅቶ ተቋሙን አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት በኩል ጠንካራ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
ተቋሙን በጥሩ ሁኔታ የተደራጀ ቢሆንም በሥነምግባር ግንባታና በሙስና መከላከል ላይ በርካታ ስራዎች የሚጠብቀን በመሆኑ አስፈፃሚዎች ዕውቀትን ከልምድ ጋር በማቀናጀት ተግባራትን መምራት ይጠበቃል ብለዋል።
የሥነምግባርና ሙስና መከላከል ስራዎች ሁሉንም ዜጋ የሚመለከት ጉዳይ ነው ያሉት ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ ሲሆኑ፥ አስፈፃሚ አካላት ራሳቸውን አርአያ ከማድረግ ባለፈ ማህበረሰቡን የትግሉ አካል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። አስፈፃሚ አካሉ ተደራሽነቱን በማስፋት የህዝቡን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ በበኩላቸው ጠንካራ የሆነ ተቋም ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት አስፈፃሚ አካሉ በመገንዘብ የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል። አክለውም የህዝቡን አቅም በመጠቀም ተቋማችንን የሚመጥን ትግል ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
የግማሽ ዓመቱ ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ኮሚሽኑ ተቋሙን በማደራጀት፣ በንቅናቄ መድረክ፣ የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠናዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በኩል ጠንካራ ስራዎች መከናወናቸው በሪፖርቱ መገለፁን ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በክትትልና ድጋፍ 198 ሴክተሮች፣ ኮሌጆች፣ ሆስፒታሎች፣ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። በተቋማቱ ከ50 በመቶ በላይ የሰው ኃይል መሟላቱን፣ በንቅናቄ ስራው፣ በስልጠና፣ በሃብት ምዝገባ እና የተሰሩ ስራዎች መረጃ በመያዝ በኩል አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን በሪፖርቱ ቀርቧል። በታችኛው መዋቅር ላይ በጀት፣ የሰው ኃይልና የግብዓት ችግር በስራዎች ላይ ጫና መፍጠራቸው ተመላክቷል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ መተግበሪያ፡- https://epfs.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ከ1 ሚሊዮን 967 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ የአፈር ማዳበሪያን በማጓጓዝ ላይ እያሉ የተያዙት ተከሳሾች ክስ ተመሰረተባቸው
****************
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት ዐ7/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ከ1 ሚሊዮን 967 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ የአፈር ማዳበሪያን እያጓጓዙ እያሉ በተያዙት ተከሳሾች ላይ ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን መገልገል እና የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ወንጀል ክስ መሰረተባቸው፡፡
በዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ደቻሳ አየነዉ፣ 2ኛ ተከሳሽ አደም ጀማል፣ 3ኛ ፀጋዘአብ ተክሌ እና 4ኛ ሃሚድ ጋሻዉ በተባሉት ተከሳሾች ላይ የእያንዳንዳቸው የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
1ኛ ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ሲሆን ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የዉጭ ሀገር ስሪት የሆኑ ብዛቱ በቁምጣ 900፣ በኩንታል 450፣ የዋጋ ግምቱ ብር 1 ሚሊየን 967 ሺ 850 ብር እና የቀረጥና ታክስ መጠኑ ደግሞ ብር 72 ሺ 259.14 ብር የሆነ ኤን ፒ ኤስ(NPS) የተባለዉን የአፈር ማዳበሪያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመበት ኮንትሮባንድ ሆኖ ሳለ፤ ዕቃዉ በህጋዊ መንገድ ገብቶ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የተረከቡ ለማስመሰል በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የምርት ማሳደጊያዎች ማስረከቢያ ሰነድ የወጪ ማዘዣ ቁጥር እና ቀን ተገልፆ በሀሰት የተዘጋጁ የምርት ማሳደጊያዎች ማስረከቢያ ሰነዶችን በመያዝ በሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ላይ በተጫነዉ ጌሾ ስር ደብቀዉ በመጫን 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች አሽከርካሪ በመሆን 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ ረዳት በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ በሚወስደዉ መንገድ ላይ በጋራ በመሆን እያጓጓዙ እያሉ በተደረገዉ ክትትል በቀን 15/05/2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 06፡00 ሰዓት ሲል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የካ ክፍለ ከተማ እስራኤል ኤምባሲ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ሲያጓጉዙ የተያዙ በመሆናቸዉ በፈፀሙት ሀሰተኛ መንግስታዊ ሰነዶችን መገልገል ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በተመሳሳይ 2ኛ ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ሲሆን ተከሳሾች የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀመባቸዉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸዉ ከላይ በ1ኛ ክስ ዉስጥ በተገለፀዉ ሁኔታ 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች አሽከርካሪ በመሆን 2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ ረዳት በመሆን ብዛቱ በቁምጣ 900፣ በኩንታል 450፣ የዋጋ ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 967 ሺ 850 ብር የቀረጥና ታክስ መጠኑ ደግሞ 72 ሺ 259.14 ብር የሆነ ኤንፒኤስ(NPS) የተባለዉን የአፈር ማዳበሪያ በጋራ በመሆን እያጓጓዙ እያሉ በተደረገዉ ክትትል የተያዙ በመሆኑ ተከሳሾች የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በማጓጓዝ ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን ተከሳሾች ክሱ ደርሷቸው መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅና ክስ ለመስማት ለየካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን ከፍትህ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡